ከተዋጊነት ወደ ተራ ተፈላጊነት – የትህነግ ፈጣኑ ሞት?

NEWS

ኢትዮ 12 ዜና – አሁን “ጦርነት” ሲባል የነበረው የመንግስትና የትህነግ ትንቅንቅ ወደ ፈላጊና ተፈላጊ ጨዋታ ተዛውሯል። ይህም ይፋ የሆነው መንግስት “ጁንታ” የሚላቸውን አካላት ” እንኳን ሊዋጉኝ የት እንዳሉም አላውቅምና አድራሻቸውን ለነገረኝ ወሮታ እከፍልስለሁ” በሚል ማስታወቂያ ካስነገረ በሁዋላ ነው። ይህ በአገር መከላከያ በኩል የተሰማው የዎሮታ ጥሪ መንግስት አስቦበትና ጥናት የተሰራ ይመስላል። ነውም።

መከላከያ አስር ሚሊዮን ብር መድቦ ” ለጠቆመኝ” ሲል ሽልማት ማዘጋጀቱን ይፋ ሲያደርግ ጉዳዩ በዓለም የፖለቲካ መድረክ ላይ ታላቅ የሚዲያና የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚያስከትል ብለሙያዎች ይናገራሉ። ከወር በፊት በእኩል ወይም ከዚያ በላይ በሚባል ደረጃ መንግስትን ሲገዳደልና ሲያስፈራራ፣ ሃይሉን አሰልፎ ሳንጃ ወድር ሲልና ደጋፊዎቹን ” አይዞን” ሲል የነበረ ሃይል፣ ከወር በሁዋላ ዱካ የማይታወቅ፣ ሞቱና ህይወቱ ያለለየለት ሃይል ሆኖ ” የገባበትን ስርቻ የምታውቁ” በሚል አዋጅ ሲተላለፍ ትህነግ እንደ ድርጅት ሞቷል።

ትህነግ ሊያብብ የሚችልበት አማራጭ እንዳለ የሚጠቁም ክፍሎች ” ትህነግ የሚያብበው በሌሎች ድሉን ተስማምቶ የማጣጣምና፣ ከፉከራ በመውጣት ሰክኖ ባለመመራት በሚመጣ ጣጣ” እየጠቆሙ ነው። ቀደም ሲል ሲፈጸም በነበረው የከፋ ችግር ሳቢያ ያቄሙ ክፍሎች አካሄዳቸው ትህነግን ዳግም ደጋፊ እንዲያገኝ የሚያስችል አካሄድ መስሎ እንደሚታያቸው እነዚሁ ወገኖች ይገልጻሉ።

ህገወጥነትን በማስወገድ ለህግ መከበር በተከፈለ ዋጋ ” ድልን በባለቤትነት ለመውሰድና፣ ድሉ የቀድሞውን ህገወጥነት ከህጋዊው መስመር ውጭ እንዲከበር ያደርገዋል” የሚለው የጭፍራ አስተሳሰብ፣ ለትህነግ አዲሱ ፕሮፓጋንዳ ያመቻል። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ” ከሁለት ሚሊዮን በላይ ደጋፊ ያለው ደርጅት በቀላሉ ሊከስም ስለማይችል ሰክኖ ነገሮችን መመርመር፣ ፖለቲካውን ከስሜት ወጥቶ ማስኬድ፣ ህዝብ ሲሰክር መሪዎች ማርጋጋትና የመሪነት ሚና መጫወት ካልቻሉ ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ” ሲሉ ይመክራሉ። ያስጠነቅቃሉ።

ይህ አይነቱ አጋጣሚ ከተዘጋ ትህነግ የትኛውም ዓይነት እድሜ መቀጠያ ቢሰጠው ሊያንሰራራ እንደማይችል እነዚሁ ወገኖች ያስታውቃሉ። ለሁሉም ግን ትህነግ በአንድ ወር ውስጥ ከዛ ሁሉ የትኩሳት ማማ ወርዶ በየጥሻው ውስጥ ያለበትን ለሚጠቁም ወሮታ እንደተዘጋጀ መገለጹ ፖለቲካዊ ድል ነው።

Related posts:

ዋር ኮሌጅ ከፍተኛ መኮንኖችን አበቃ፤ መከላከያ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በቁ አቋም አለው
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Leave a Reply