ኢትዮ 12 ዜና – አሁን “ጦርነት” ሲባል የነበረው የመንግስትና የትህነግ ትንቅንቅ ወደ ፈላጊና ተፈላጊ ጨዋታ ተዛውሯል። ይህም ይፋ የሆነው መንግስት “ጁንታ” የሚላቸውን አካላት ” እንኳን ሊዋጉኝ የት እንዳሉም አላውቅምና አድራሻቸውን ለነገረኝ ወሮታ እከፍልስለሁ” በሚል ማስታወቂያ ካስነገረ በሁዋላ ነው። ይህ በአገር መከላከያ በኩል የተሰማው የዎሮታ ጥሪ መንግስት አስቦበትና ጥናት የተሰራ ይመስላል። ነውም።
መከላከያ አስር ሚሊዮን ብር መድቦ ” ለጠቆመኝ” ሲል ሽልማት ማዘጋጀቱን ይፋ ሲያደርግ ጉዳዩ በዓለም የፖለቲካ መድረክ ላይ ታላቅ የሚዲያና የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚያስከትል ብለሙያዎች ይናገራሉ። ከወር በፊት በእኩል ወይም ከዚያ በላይ በሚባል ደረጃ መንግስትን ሲገዳደልና ሲያስፈራራ፣ ሃይሉን አሰልፎ ሳንጃ ወድር ሲልና ደጋፊዎቹን ” አይዞን” ሲል የነበረ ሃይል፣ ከወር በሁዋላ ዱካ የማይታወቅ፣ ሞቱና ህይወቱ ያለለየለት ሃይል ሆኖ ” የገባበትን ስርቻ የምታውቁ” በሚል አዋጅ ሲተላለፍ ትህነግ እንደ ድርጅት ሞቷል።
ትህነግ ሊያብብ የሚችልበት አማራጭ እንዳለ የሚጠቁም ክፍሎች ” ትህነግ የሚያብበው በሌሎች ድሉን ተስማምቶ የማጣጣምና፣ ከፉከራ በመውጣት ሰክኖ ባለመመራት በሚመጣ ጣጣ” እየጠቆሙ ነው። ቀደም ሲል ሲፈጸም በነበረው የከፋ ችግር ሳቢያ ያቄሙ ክፍሎች አካሄዳቸው ትህነግን ዳግም ደጋፊ እንዲያገኝ የሚያስችል አካሄድ መስሎ እንደሚታያቸው እነዚሁ ወገኖች ይገልጻሉ።
ህገወጥነትን በማስወገድ ለህግ መከበር በተከፈለ ዋጋ ” ድልን በባለቤትነት ለመውሰድና፣ ድሉ የቀድሞውን ህገወጥነት ከህጋዊው መስመር ውጭ እንዲከበር ያደርገዋል” የሚለው የጭፍራ አስተሳሰብ፣ ለትህነግ አዲሱ ፕሮፓጋንዳ ያመቻል። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ” ከሁለት ሚሊዮን በላይ ደጋፊ ያለው ደርጅት በቀላሉ ሊከስም ስለማይችል ሰክኖ ነገሮችን መመርመር፣ ፖለቲካውን ከስሜት ወጥቶ ማስኬድ፣ ህዝብ ሲሰክር መሪዎች ማርጋጋትና የመሪነት ሚና መጫወት ካልቻሉ ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ” ሲሉ ይመክራሉ። ያስጠነቅቃሉ።
ይህ አይነቱ አጋጣሚ ከተዘጋ ትህነግ የትኛውም ዓይነት እድሜ መቀጠያ ቢሰጠው ሊያንሰራራ እንደማይችል እነዚሁ ወገኖች ያስታውቃሉ። ለሁሉም ግን ትህነግ በአንድ ወር ውስጥ ከዛ ሁሉ የትኩሳት ማማ ወርዶ በየጥሻው ውስጥ ያለበትን ለሚጠቁም ወሮታ እንደተዘጋጀ መገለጹ ፖለቲካዊ ድል ነው።
- Ethio-China Relations in Light of One-China PrincipleChina is an emerging giant at the global scale. A country that was wrestling with poverty forty years ago has… Read more: Ethio-China Relations in Light of One-China Principle
- “አማራን እንወክላለን” የሚሉ ሁለት ቡድኖች ለድርድር ጥያቄ አቀረቡበተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ መቅረቡን ተከትሎና ሕዝብ በግጭቱ ሳቢያ የሚያሰማው ምሬት እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት ” የአማራ ክልል ህዝብ ወኪል ሆነን… Read more: “አማራን እንወክላለን” የሚሉ ሁለት ቡድኖች ለድርድር ጥያቄ አቀረቡ
- በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ላይ አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ ነውበወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን የመከላከልና መቆጣጠር ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ የተዘጋጀ የግብዐት ማሰባሰቢያ መድረክ… Read more: በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ላይ አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው
- በትግራይ የወጣቶችና ታዳጊዎች ስደት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ነው“የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪና ብቸኛ አማራጭ ነኝ” የሚለው ትህነግ ለህዝቡ እያበረከተ ያለው ገጸ በረከት እያደር ገሃድ እየሆነ ነው። በተለይም ከጦርነቱ… Read more: በትግራይ የወጣቶችና ታዳጊዎች ስደት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ነው