ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የክልል ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስፈልጉ ትብብሮች እንደደረጉለት ለክልል መስተዳደሮች በድጋሜ ጥሪ አቀረበቦርዱ በተለያዩ ወቅቶች ከክልል መስተዳድር ሃላፊዎች ጋር ውይይቶችን በማከናወን የክልል መስተዳድሮች የሚጠበቅባቸውን ሚና በዝርዝር አቅርቧል።

ከዚህ በፊት በተደረጉ ውይይቶቹ መሰረት ቦርዱ የሚከተሉትን ዋና ዋና ትብብሮች ጠይቋል፡-

1. የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር- 33 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ሶስት የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የስልጠና ቦታዎች

2. ድሬደዋ ከተማ መስተዳድር- 47 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 1 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮና የስልጠና ቦታ

3. ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት -72 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣11 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች

4. ጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 14 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 3 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮወና የስልጠና ቦታዎች

5. ደ/ብ/ብ/ህ ክልላዊ መንግስት እና ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 132 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 17 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የስልጠና ቦታዎች

6. ሃረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 3 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣1 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የስልጠና ቦታዎች

7. አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት -32 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 5 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የስልጠና ቦታዎች

8. አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 138 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 12 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች የስልጠና ቦታዎች

9. ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 179 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 20 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የስልጠና ቦታዎች ናቸው። ቦርዱ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ለቢሮ መከፈት የሚያስፈልግ ዝግጅት በደብዳቤ ጥር

10 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲያሳውቁ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም እስከአሁን ድረስ ይህንን ዝግጅት አስመልክቶ ምላሽ ያቀረበ የክልል መስተዳድር አለመኖሩን አስታውቋል። የተገለጹት አስፈላጊ የምርጫ ክልል ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስፈልጉ ትብብሮች ለምርጫው ሂደት አስፈላጊነታቸውን በመገንዘብ ክልሎች ትብብራቸውን እንዲፋጥኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 161 የተቀመጠውን የመተባበር ግዴታቸውን እንዲወጡም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል፡፡ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የሚያደርገውን ዝግጅት አስመልክቶ የጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱ እንዲሁም የተለያዩ ተግባራትን ለማከናውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል

Leave a Reply