“ትህነግ መጀመሪያ ቃል ነበር – ማሌሊትን ለብሶ በእኛ አደረ “

እስኪ መለስ ይቀስቀሱ። እስኪ መለስ ፊት ብዙ የድምጽ መቅጃ ይደርደር። ድምጸ ወያኔ ይጠይቅ። ሁሉም ባይሰማ የትግራይ ሕዝብ፣ ከትግራይ ሕዝብም በተለይም ” አምላክ ትግራይን ፈጠረ፣ ትግራይም ፖለቲካ ነበረች፣ ፖለቲካ ቃል ነበር፣ ቃሉም ትህነግ ነበር፣ ትህነግም በኛ ውስጥ ነበር። እኛም ትህነግ ነበርን። ትህነግ በኛ ውስጥ አድሮ ህያው ሆነ፣ ማሌሊትን ለበሶ ስጋና ደም ሆነ። ከትህነግ ውጭ ማንም አልነበረም … ” የሚሉት ተመርጠውም ቢሆን እንዲሰሙ ይደረግ። መልሱ አንድ ነው ” ዘበኛም ቢሆን የትህነግን ዓላማና ሃሳብ ተግባራዊ ካደረገ ይሾማል፤ ይሸለማል” የሚል ነው። መቼም ያን እሳት አይቶ የተቀሰቀሰ አይዋሽምና!!

እንዴት ከረማቹህ? አጀንዳ ከፍርስራሽ ላይ የምትለቅሙትን አይመለከትም። ያበደው ነኝ። ሰው ለምትረሱ የቦሳና ባልተ ቤት፣ የደጎል ውሻዬ አባት። ድመት የምጠየፍ፣ የቅድመ አያቴ አፈ ዶማ ምትክ። ያበደው ዛሬ በቀኙ ይነሳ በግራው አያውቅም። ግን ሙታን አስነስቶ ምስክር ሊያደርግ ወስኗል። መለስን የቀሰቀሰው ያለ ምክንያት አልነበረም።

የሰሞኑ ልቅሶ መልከ ብዙ ነው። ያሸነፉ ለመባላት አሰፍሰፈዋል። የተሸነፉትም መልካቸውን እየቀያየሩ አሸናፊዎችን አባልቶ ለመነሳት ጋዝ እያርከፈከፉ ነው። አስር ላይክ ያገኘ የፌስ ቡክ አባል ኮሎኔል፣ መቶ ላይክ ያለው ጀኔራል፣ አንድ ሺህ ላይክ ያለው ጠቅላይ የሆኑ ያህል መመሪያ ያወርዳሉ። አማራ ከብልጽግና እንዲወጣ የሚጮሁ ተቀላቢ አንደበቶችን ማወቅ ተስኗቸው አጃቢዎች ይደግሙታል። አይ እውቀት!! አይ ምርምር!! ያበደው አልተናደደም ግን አዘነ። እስኪ አማራ ከብልጽግና ይውጣና ተጠቃሚ ይሁን? ከሆነ ደግ!! ትህነግም ይህ ትዕቢቱ ልቡናውን አደፈነው። የአማራውን ለየት የሚያደርገው መሪዎቹ መስከናቸው ነው። እንተወው…

ያበደው እንደወትሮው ወደ ቸርችል ጎዳና አልሄደም። ይልቁኑ ያዘገመው ወደ አራት ኪሎ ነበር። ባተሌዋን ቀዳማዊ እምቤት ለማግኘት። ያበደው ተሳክቶለት አግኝቷቸዋል። ባለቤትዎ በፈቃዳቸው ይልቀቁና ቀሪውን ዘመናቸውን በሰላም ይኑሩ። “ሽንፍላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምሱ ስለማይታወቅ ለባለቤትዎ ምስ ፈልጉ።ይህ ሽንፍላ የሆነ ፖለቲካ ክንፍ የቀጠለ መላክ ቢመራውም አይቃናም። እርስዎ ባጭር ጊዜ ያስገነቡት ትምህርት ቤቶች ይበቁናል። እርስዎን በዚያ እናስባለን” ያበደው መክሮ ወጣ። ምላሻቸውን አልሰማም። መስማትም አልፈለገም። ወደ ስላሴ አግረ መንገዱን ጎራ አለ ፤ ሃውልት እያየ አንዱ ጋር ሲደርስ “አዎ የሚበጀው  አይነት መሪ ነው!!” አለው።

See also  አሜሪካ ከሳይበር ጥቃት ጋር በተያያዘ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ልትጥል ነው

Related stories   ጭካኔ ኩያሳ ሲሰራና ጥላቻ አናት ላይ ሲቀነዝር …Powered by Inline Related Posts

ወያኔ አቅም አልባዎችን፣ ተላላኪዎችን፣ ሞራል የሌላቸውን፣ በ – ገበያዎችን፣ ለሰፈር ያስቸገሩ ዱርዬዎችን፣ መንታፊዎችን፣ ሰው ሃክ ያላቸውን … ሲሰበስብ ” ተው” ተብሎ ነበር። ወያኔ በጥላቻ ፖለቲካ ህዝቡን ሲያባላ ” ተው ይቅር” በሚል ተለምኗል። ወያኔ በዘር አገር ሲያናቁር ” አይጠቅምም ይቅር” እያሉ የመከሩትን መቀመቅ አውርዷል። አዋርዶ ገሏል። ከኤርትራ ጋር ፍቺ ሲፈጸም ” በወጉ አድርገው” ሲባል ” አሃዳዊያን” በሚል አኮላሽቷል።  ያበደው እምባው ቀረረ። “ፕሮፌሰር አስራት ነብስዎን ይማር” እየለ ተንቆራጠጠ። ከዛ ተፋ፤ ምራቁን አጠራቅሞ ለደፈበት። ” እርጉም” አለና ጮክ ብሎ ተሳደበ። ዘወር ሲል ሃውልት ጠባቂዎቹ አሉ። ሙት ጠባቂ ህያዋን!! ሙት ለመተበቅ የተሰማሩ ነዋሪዎች!!

ቦሰና ያልተማረች ምሁር ናት። የትምህርት ደረጃ ስትጠየቅ ” ልበ ብርሃን” ነው መልሷ። እውነትም ልበ ብርሃን ናት። በየሰፈሩ የሚሆነውን ስታይ ” እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን የሚበላ ሰይጣን እያመረቱ እንደሆነ አልገባቸውም” ትል ነበር። በረከት እንዴት ይሄ ይጠፋዋል? ቦሰና ቦነሰችው።

ወያኔ ትውልድ አነተበ። ሽማግሌ አጠፋ። መካሪና የሚገስጽ አመከነ። አገሪቱን ወደብ ብቻ ሳይሆን ታላላቅ አልባ አደረጋት። እዛ ትልቁ ቤት የተሰበሰቡት ምስለኔዎች ደግሞ ” ይዞ መገኘት” የሚለውን የአፈንዳጅ መርህ ጨመሩበት። የሚገኝበት ከሆነ ማፈንደድ፣ ጆንያ ውስጥ ግብቶ እንደ ቆጮ መታሰር ክብር እንደሆነ አለማመዱ። ከተገኘበት ሚስትን ውብ አድርጎ አልብሶና አሽቀርቅሮ እዛ ትልቁ ቤት ወስዶ ማስረከብ ሁሉ ኩራት እንደሆነ አስተማሩ። አፍንድደው ማፈንደድ አስተማሩና አፈንዳጅ አራቡ። ዛሬም ድረስ ያፈንዳዳሉ። አግኝተውም አይጠግቡም። ዘርፈውም አይሞላላቸውም። ማፈንደድ … በህግ ቢከለከልም እዛ ይቻላል። ያበደው ሲነሳበት ይቀባጥራል።

ድሮ ያሌለ ሞራል ከየት ይምጣ? ያበደው ጠየቀ። ድሮ ያላስቀመጡት፣ ቀድሞ ያልዘሩት፣ አስበው ያላዘጋጁት የጭንቅ ጊዜ ከየት ይምጣ? ጨዋታው እንዲህ ሆነ። ትግል ነበር። ትግሉም በትህነግ ነበር። ትግሉ ከልብ ነበር። ትግሉ ተጓዘ … ትግሉ ተጠለፈ። ትግሉን የጠለፉት በረዙት። ትግሉ ቤተመንግስት ገባ። ትግሉን የመሩት ሚስት ቀየሩ… ውድቀት ተጀመረ። የችግር ጊዜ ሚስቶች ጭጎጊት ሆነው ታዩ። ተሰናበቱ። በትግሉ ቋንቋ ተንጠባተቡ… አብዮት ሳትሆን ባሎች የበረሃ አካሎቻቸውን አዲስ አበባ ሲገቡ አረከሱ!! ዛሬ እኒህ ሴቶች ምን ብለው ይሆን?

See also  ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች

Related stories   ጭካኔ ኩያሳ ሲሰራና ጥላቻ አናት ላይ ሲቀነዝር …Powered by Inline Related Posts

ምሳ አዲስ አበባ የአፍታ ወሲብ ዱባይ ሆነ። ” የተሰው ሰማዕታት” ምናምን የሚባለው መዝሙር ቃል እንደሆን ቀረ። ይህ ገበያ የፈጠረላቸው ወሲብ ማቅረብ ጀመሩ። ወሲብ በስልክ ይታዘዝ ጀመር። ድህነት የጠበሳቸው ቆንጆዎች ማገገሚያና ይዋባሉ። እንደ ዶሮ በሽሮ ተፈትገው እየታጠቡ፣ ስቲም እየገቡ ተኩለው ለአያቶቻቸው ገበያ ይቀርቡ ገባ … ያበደው ብዙ መረጃ አለው። በየቦታው በዝግ ቤት፣ አለያም መከረኛ ዱባይ ይዞ መብረር … እዛም እዚህም መረከስ ሆነ። ይዞ ለመገኘት ማፈንደድ ወይም ማስፈንደድ … ወይም ሁለቱንም ማድረግ… ያበደው የሚያውቃቸውን ባይነ ህሊናው እያየ ፈገገ። እንደ ልማዱ ምራቁን ጢቅ አደረገና ተላወሰ።

ቦሰና ” ምን ዋጋ አለው” ስትል አልቅሳ ነበር። ሻሸመኔ ሰው ተገድሎ፣ መሞት በቂ ባለመሆኑ ተሰቀለ። ሲሰቀል እንደተለመደው አናቱ ወደላይ መሆን አልነብረበትምና የዘመኑንን መስፈርት እንዲያሟላ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ። ይህም በቂ አልነበረም። በድንጋይ ተወገረ። ይህም በቂ አልነበረም በቪዲዮ መቀረጽ ነበረበት። ይህም በቂ አልነበረም ሁሉም ትዕይንት ሆኖ ለህዝብ መሰራጨት ነበረበት። እናት፣ አባት፣ ዘመድ፣ ዘመዶች፣ ባልደረቦች፣ ልጆች ካሉም ልጆሽና የትምህርት ቤት ጓደኞች ማየት አለባቸው። ቦሰና ” ራሳቸውን የሚበላ ትውልድ እያመረቱ …” ያለቸው የነብይ አይነት ንግግር ያበደውን አናቱን መታው።

ያበደው ጮኸ ገደሉት፤ ዘቅዝቀው ሰቀሉት፤ ሰቅለው በድንጋይ ወገሩት። እንደ ጀግንነት ይህን እያደረጉ ቪዲዮ ተቀረጹ … አራስ ሆድ ቀደዱ። አረዱ። ጨፈጨፉ … አቃጠሉ፣ ዘረፉ … ምን ቀረ? ይህ ሁሉ በአንዴ አልሆነም። ይህ ሁሉ የሆነው እንዲሆን ስለተፈለገ ነው። እንዲሆን የተፈለገው በሌሎች ላይ ነበርና የሚያዝኑ ያሉትን ያህል የሚደሰቱ ነበሩ። እዚህ ውርደት ውስጥ ተርመጥምጠው ዙፋን ሊይዙ ያኮበኮቡ ” ጀግና” ሲባሉም ነበር… ያበደው ዞረበት

“ምን እየሆነ ነው? ምን ውስጥ ነን” ያበደው ጠየቀ። መልስ የለም ብቻ የምርቱ ዓይነት ነው። ምርቶቹ ራሳቸውን በቪዲዮ እየቀረጹ ሰቅለው በድንጋይ ይወግራሉ። አምራቾቹ መከለካያ ሰራዊትን በ45 ደቂቃ ” አደባየነው” ብለው በኩራት ይነግሩናል። ያበደው አሁን አናቱ ጋለ። የት ጋር እንደሳትን ሊገባው አልቻለም።

See also  "የሀገር ሉዓላዊነትን አደጋ ላይ የሚጥል የጥፋት ተልእኮ የያዘ ጥምረት ፍፁም ተቀባይነት የለውም" የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

Related stories   ጭካኔ ኩያሳ ሲሰራና ጥላቻ አናት ላይ ሲቀነዝር …Powered by Inline Related Posts

ትህነግ ሲመከርና ሲዘከር እምቢ ብሎ  ካመረተው ጭንግፍ ምርት ውለታ ፈላጊ ሆነ። ” ድረሱልኝ” ሲል ተጣራ። እጁን የቻለውን ያህል ሰደደ አልሆነም። የጣር ድምጽ አሰማ። በብሄር ብሄረሰቦች ስም እየማለ ተማጸነ። የሚያዝንለት ሞራል ያለው ወዳጅ አላገኘም። ከአዲስ አበባ ወደ መቀለ መርዝና በሽታ ተሸክሞ ሄደ። በሰላም ከነችግሩ ላይ ታች እያለ የሚኖረውን ህዝብ በሽታውን ረጨበት። መርዙን እንደወረርሺኝ አጋባ። የትግራይ ህዝብ የልብ ወዳጅ የሆነውን መከለከያን ተነኮሰ። የጁን ሲያገኝ ጩኸቱን አሁንም አበረከተ። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ብሎ አለቀሰ … መልስ አልነበረም። ያበደው ተቆጣ።

ዛሬ ሌላ ቀን ነው፤ ብዙ የሳቱ ነገሮች አሉ። ብዙ ቀዳዳዎች አሉ። ሁሉንም ቀዳዳ ደፍኖ አይቻልም። ያልተደፈኑትን ቀዳዳዎች ፈልጎ መድፈን የሁሉም ድርሻ ነው። ሴራ በመፈልፈል ሽንቁሮቹን ማስፋት … ያበደው አይስተነቀቀ እንደ አዋጅ ነጋሪ ወደ ሃዲድ አቀና።  ” ስሙ እናነት እርኩሶች፣ ስሙ እናንተ የሴራ አምራቾች፣ ስሙ እናንተ የደም ስር ተዋናዮች፣ ስሙ እናንተ አፈንዳጆች፣ ስሙ እናንተ አደራ በሊታዎች፣ ስሙ እናንተ የማይገባቹህ…” ጮክ ብሎ እየተጣደፈ ” ልበ ብርሃን ሁኑ፣ ላብችሁን አጽዱ፣ አገሬ ነፈረች፣ አገሪ ተሞሸለቀች፣ አገሬ ተፈናቀለች፣ የትግራይ ህጽናት ፍቅር ይሻሉ … ጥፋትን የምትደግሙ አቁሙ። አታፈናቅሉ…” ሳያስበው ደጎል መቶ ዘሎ ደረቱ ላይ ቆመበት።

ደጎል አዋቂ ነው። መልስ ሲናገር ቲቪ ላይ ካየው አናቱን እያወዛወዘ ከቤት ይወጣል። ቦሰና ” ሰውየው” ነው የምትለው እንጂ ደጎል አትለውም። ለደጎልና ቦሰና ጊዜ መስጠት ግድ ነው። ትውልድ አታርክሱ። ዱርዬ ትውልድ ስላለ ” መልካም ወጣት” እንዲፈጠር እናስብበት። “ቃልም ፖለቲካም፣ የፖለቲካ ድርጅትም ትህነግ ነው የምትሉ አይሆንም። ብዙ አማራጭ አለ” ….  ቦሰና ተቀባብታለች። ቦሰና አርብ ቀኗ ነው። ቦሰና ከተቀባባችና ቡናዋን ፏ አድርጋ ከተበቀች ግጥሚያ ፈልጋለች ማለት ነው። ይለይልናል። ቦሰና ፍቅር ናት። አሁን ከሷ ጋር ነኝ። እሷ ውስጥ እገባለሁ። እሷም ታስገባኛለች። ሃሽቃሮ!! ኸምምምምም “እስይ” በሉ ባላችሁበት። ሰላም ሻሎም !!

Leave a Reply