የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጣኛ የነበረው ዳዊት ከበደ በስም ካልተጠቀሰ ጓደኛው ጋር በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን የጀርመን ድምጽ ዘግቧል። ዘገባው ሙሉ መረጃ ባያቀርብም በመቀለ ባለ ዘጋቢው አማካይነት ማረጋገጫ ሰጥቷል። የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አክቲቪስቶች በበኩላቸው ” የትግራይ ተወላጅ የብልጽግና አመራር ቀብራቹህ በቅርብ ገሃድ ይሆናል” የሚል ሃረግ ያለበት ወርቀት የሰዓት እላፊ በመጣስ በተሽከርካሪ ሆነው ሲበትኑ እንደነበር እየገለጹ ነው።
የጀርመን ድምጽ የመቀለ ዘጋቢ አክቲቪስቶቹ የጠቀሱትን ሃሳብ በዜናው አላካተተም። ይሁን እንጂ ” የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሚያስተዳድረው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ እና ጓደኛው ትናንት በመቐለ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ። ቤተሰቦቻቸው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው እንደተናገሩት ዳዊት እና ጓደኛው የተገደሉት የሰዓት ዕላፊ በታወጀባት ከተማ በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀሱ ከጸጥታ ኃይሎች በተከተኮሰ ጥይት ነው” ሲል ነው ዜናውን የጀመረው።
መለስ ብስራት የሚባለው አክቲቪስት የሚከተለውን በፌስ ቡክ ገጹ ያሰፈረ ሲሆን ዞባ ተምቤን Tembien Province በበኩሉ ሰፋ ያለ መረጃ አስፍሯል።
“የጀርመን ድምጽ እንዳለው በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ታስረዋል። በመቐለ ከተማ የሰዓት ዕላፊ ታውጇል። ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ያነጋገርኩት ሚሊዮን እንደነገረኝ ኩነቱ የተፈጸመው በከተማው መንቀሳቀስ በተከለከለበት ወቅት ነው። የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከጊዜያዊው አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሚሊዮን ያደረገው ጥረት እንዳልሰመረ በስልክ ነግሮኛል” የጀርመን ድምጽ ዘገባውን ያተቃልላል።
ዞባ ተምቤን Tembien Province ከጀርመን ድምጽ ጋር ተመሳሳይ መረጃ ያቀረበ ሲሆን ልዩነቱ ያለው ከሰዓት እላፊ ተላልፈዋል የተባሉት ሟቾች ምን ሲያደርጉ እንደነበር ማብራራቱ ላይ ነው። ዞባ ተምቤንም ሆነ ጀርመን ሬዲዮ እንዳሉት በመቀለ ሰዓት እላፊ ታውጇል። ከምሽቱ አንድ ሰዓት በሁዋላ የንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ዳዊትና ጓደኞቹ በምግምት 2:30 አካባቢ በተሽከረካሪ ውስጥ ሆነው ጎዳና ላይ ይነዱ ነበር።
የጀርመን ድምጽ ቤተሰቦች አነጋግሮ በሰዓት እላፊ ምን ይሰሩ እንደነበር አላብራራም። ዞባ ተንቤን የሚከተለውን በከፊል ከፌስ ቡክ ገጹ ላይ ወስደናል።
ዞባ ተምቤን Tembien Province· የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ እና ሶስት ጓደኞቹ ትላንት በመቐለ ከተማ ከምሽቱ 2 30 አከባቢ የበተኑት ወረቀት ቃል በቃል የሚለውን ይዘን ቀርበናል።
“ህዝቢ ትግራይ ንክፀንት ብዝከኣለኩም ትረባረቡ ዘለኹም ኸደምቲ ስርዓት ኣብይን ብልፅግናን ዝኾንኩም ተወለድቲ ትግራይ ናይ ብልፅግና መራሕቲ ቀብርኹም ኣብ ቀረባ እዋን ክገሃድ ‘ዩ።
የአማርኛው ትርጉሙ – “የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ በምትችሉት እየተንቀሳቀሳቹህ ያላአቹህ የአብይ እና የብልፅግና አገልጋዮች የሆናቹህ የትግራይ ተወላጆች የብልፅግና አመራሮች ቀብራቹህ በቅርቡ ገሃድ ይሆናል።
በትግራይ ክልል ማታ ከአንድ ሰአት ቦሃላ ማንኛውም አካል መንቀሳቀስ እንደማይቻል ኮማንድ ፖስቱ ህግ አውጥቷል። ሲልም ዞባ መረጃ ይሰጣል። ኢትዮ 12 ዜናውን በራሱ መነግድ ለማጣራት አልቻለም። ይሁን እንጂ የሶስት ወገኖችን መረጃ ጨምቀን አቅርበናል። ከዚህ የዘለለ መረጃ ማግኘት ከቻልን እንመለስበታለን። አስገድዶ ማስቆም ያልተቻለበትን ምክንያት ለማወቅ ግን ጥረታችን ይቀጥላል።
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- የዜናው ሰም፣ ወርቅና “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የትህነግ ዜናውን አጣጣለለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ… Read more: የዜናው ሰም፣ ወርቅና “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የትህነግ ዜናውን አጣጣለ