“ሱዳን ምንጊዜም የሚቆጫትን ስህተት ሰርታለች”

-ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በአ.አ.ዩ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ

ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሀይል በመዝለቅ ምንጊዜም ቢሆን የሚቆጫትን ስህተት መስራቷን በአ.አ.ዩ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ አስታወቁ። እየሄደችበት ያለው መንገድ ብሄራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ እና ዘላቂ ጥቅሟን የሚያሳጣት እንደሆነም አመለከቱ።ፕሮፌሰር ያእቆብ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ሱዳን በመንግስትነት ሳትቋቋም በፊት በኢትዮጵያ እና በቅኝ ገዥዎች መካከል የተጀመረ ነው።

ችግሩን ለመፍታት የጋራ ኮሚሽን ተቋቁሞ የተለያዩ ልዑካን እና ኤክስፐርቶች ሐሳብ እየተለዋወጡ እንደሆነ አመልክተው፣ ውይይቱ ድንበሩ የት ይሁን የሚለውን ሳይቋጩ ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ወስዳ የእኔ ነው ማለት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

የሰራችው ስህተት ምንግዜም ቢሆን የሚቆጫት እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡ከብዙ አቅጣጫ ሲታይ እና ሲመዘን ሱዳን ዛሬ የድንበር ጉዳይ የምታነሳበት ወቅት እንዳልሆነ ያመለከቱት ፕሮፌሰሩ፤ የድንበር ጉዳይ ቢነሳ እንኳ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት አለኝ ብላ በጉልበት ለመውሰድ የምትንቀሳቀስበትም ጊዜ አይደለም ብለዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

See also  ከ370 ቢሊዮን ብር በላይ በባንኮች ላይ የማጭበርበር ወንጀል ሙከራ ተደርጓ ከሽፏል፣1.8 ቢልዮን ተዘርፏል

Leave a Reply