ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ማህበራዊ አንቂዎችን ” አደብ ግዙ” ሲል አስጠነቀቀ

በተያያዘ ዜና ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ያሳውቃል።

ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በሀገር ላይ የሚቃጡ የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በማስቀረት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከማንኛውም ጊዜ በላይ ከሁሉም የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጫው አመልክቷል።

በሌላ የተቋሙ ዜና የብሔራዊ መረጃ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅን በኢንተለጀንስና በደህንነት መስኮች የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው የለውጥ ትግበራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ::👉 አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በአገልገሎት መሥሪያ ቤቱ ሥር የሚገኘውን የብሄራዊ መረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሥራ እንቅስቃሴን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

አገልገሎት መሥሪያ ቤቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመሰገን ጥሩነህ በጉብኝታቸው ወቅት በሥልጠና ማዕከል ደረጃ የነበረው ተቋም ወደ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ደረጃ ማደጉ አስደሳች መሆኑን ገልፀው ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ከዚህ በላይ የመሥራት እምቅ አቅም እንዳለው ተናግረዋል።

ዩኒቨርስቲ ኮሌጁን በአፍሪካ በኢንተለጀንስና በደህንነት መስኮች የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው የለውጥ ትግበራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተቋሙ አመራሮች ድጋፍ እንደማይለየውም አመልክተዋል፡፡አዲስ አበባ የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ተቋማት የዲፕሎማሲ መቀመጫ መሆኗን የጠቆሙት ዳይሬክተር ጀነራሉ፤ የብሔራዊ መረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሎጁ በዘርፉ የማሰልጠን አቅሙን ከፍ ወዳለ ደረጃ ካደረሰ አፍሪካውያንን በማስልጠን በአፍሪካ የልህቅት ማዕከል መሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁን አቅም ይበልጥ ለማሳደግ፣ ለማዘመንና በቴክኖሎጂ ታግዞ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ ተልዕኮውን እንዲወጣ ለማስቻል አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን የፋይናንስና የሎጀስቲክስ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። የብሄራዊ መረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባለፈው ዓመት ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በደህንነት ፣ በኢንተለጀንስ፣ በስትራቴጂክ ጥናትና በቋንቋ የትምህርት መስኮች በዲግሪና በዲፕሎማ ስልጠና ለመስጠት እውቅና ማግኘቱ ይታወሳል፡፡

 • ኢትዮጵያ እንደገና አንድ ሆና ተሰፋች፤ ደስም አለን!
  ዛሬ ሁሉም ዜጋ ” አገሬ” አለ። ያለ ልዩነት ” ማን እንደ አገር” ብሎ ጮኸ። በራሱ ተነስቶ ” እኔም ወታደር ነኝ ” አለ። ከባህር ማዶ ያሉ ከሃጂዎች አገር ለማፍረስ ሲማማሉ፣ የስልጣን ክፍፍል ሲያደርጉ፣ ግማሾቹ በስተርጅና ሲቀሉ፣ ትርፍራፊ የሚጣልላቸው ሚድያዎች አገራቸው ላይ አድማ ሲጠሩ፣ አንዳንድ ባለሃብት ነን ባዮች ቀን ቀን ቤተ ክርስቲያን፣Continue Reading
 • ለትግራይ ጄኔራሎች- “አይ” ካላችሁ ግን ውርድ ከራሴ ብያለሁ
  የምትከተሉት የውጊያ ስልት ያረጀና ያፈጀ ነው። የመጨረሻ ውጤቱም ትግራይን ትውልድ አልባ የሚያደርግ ነው። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ አፋር ላይ “ክተት” ብላችሁ ልካችሁት እንደ ቅጠል ረግፎ የቀረው ወጣት ነው። የሰው ማዕበል ስትራቴጂ በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን የሚያስገኘው ውጤት ኢምንት ነው። የሰው ማዕበል በአንድ ድሮን፣ በአንድ የአውሮፕላን ቦንብ ወይም በዘመናዊ አውቶማቲክ መሳሪያ ይበተናል። አፋርContinue Reading
 • “አሸባሪው ትህነግ”በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል
  የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በአውደ ዉጊያ ዉሎው ጠላትን እያንበረከከ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን አስታወቁ። በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል ዋና ዳይሬክተሩ በቅጥረኛ የትህነግ ተቀጣሪ አክቲቪስቶች በሀሰት እንደሚነዛው መረጃ ሳይሆን በማይጠብሪ፣Continue Reading
 • አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅጥፈት መግለጫ አወጣ፤ ቡድኑንን እየበጠበጠ ነው
  “ሕዝባችንና መንግስታችን” የሚል ተደጋጋሚ ሃረግ በመጠቀም መገልጫ ያሰራጨው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል እንዲወዳድር መደረጉ አግባብ እንዳልሆነ አስታወቀ። በመግለጫው የሰጠው ምክንያትና ቀደም ሲል ያቀረበው ሪፖርት አይሰማማም። ፌዴሬሽኑ በቶኪዮ ኦሊምፒክ አጠቃላይ ሂደት ላይ ያሰራጨው መግለጫ ” ከውዲሁ የለሁበትን” ዓይነት ሲሆን ውጤቱን አብዝቶ ሊጎዳ የሚችልና ኢትዮ 12 ባደረገው ማጣራትContinue Reading

Leave a Reply