የተባበሩት አረብ ኢምሬት በአገሯ ሰራተኞችን ከተለያዩ የዓለማችን አገራት መቅጠር የሚያስችሉ ሶስት አይነት የአሰሪ እና ሰራተኛ ህጎች አሏት።

ከነዚህ ሶስት አይነት ህጎች ውስጥ በኤጀንሲዎች የሚፈጸሙ የአሰሪ እና ሰራተኛ ህጓን ባሳለፍነው ሳምንት መሰረዟ ይታወሳል።

በዚህ የስራ ዘርፍ 250 ቀጣሪ ተቋማት ሰራተኞችን ከተለያዩ የዓለማችን አገራት ይቀጥሩ የነበሩ ሲሆን አሁን ሁሉም ስራቸውን ከአንድ ወር በኋላ ያቆማሉ።

ይህ የሰራተኞች ቅጥር ከተለያዩ አገራት የቤት ሰራተኞችን ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በቀጣሪ ኤጀንሲዎች አማካኝነት በማምጣት ለሰራተኛ ፈላጊ የአገሬው ዜጎች የሰው ሃይል ይቀርብ ነበር።

አገሪቱ ይሄንን በኤጀንሲዎች አማካኝነት የሚፈጸም ቅጥርን የሚተካ መንግስታዊ ተቋም በማደራጀት ቅጥሩን እንደምታከናውን አስታውቃለች።

በዚህ የቅጥር አይነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ዱባይ እና ሌሎች የአገሪቱ ከተሞች በማምራት በመስራት ላይ ይገኛሉ።
በርካቶችንም ወደዚያው ለማምራት የኮቪድን መጥፋት በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም ይህ የተሰረዘው ህግ ኢትዮጵያዊያንን ይጎዳ ይሆን ሲል? የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠይቋል።

በሚኒስቴሩ የህገወጥ ሰራተኛ ምልመላ መከላከያ ቡድን መሪ አቶ ዘሪሁን የሺጥላ እንዳሉት የተባበሩት አረብ ኢምሬት የሰረዘችው ህግ ላለፉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያዊያን ሲጠቀሙበት የነበረ ህግ ነው ብለዋል።

ይሁንና በኤጀንሲዎች አማካኝነት የሚፈጸመው የሰራተኛ ቅጥር ብዙ ኢትዮጵያዊያንን ለእንግልት እና ለጉዳትም የዳረገ በመሆኑ ህጉ መሻሩ ኢትዮጵያዊያንን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም ሲሉ አቶ ዘሪሁን ተናግረዋል።

የተባበሩት አረብ ኢምሬት ይሄንን ህግ በመሻር ስራውን ከኤጀንሲዎች ይልቅ በመንግስት ተቋም እንዲፈጸም አቅጣጫ ማስቀመጧ ኢትዮጵያዊያንን የበለጠ ደህንነቱ የተረጋገጠ ስራ እንዲሰሩ ያደርጋልም ብለዋል።

ችግሮች ሲፈጠሩም የኢትዮጵያ መንገስት በቀጥታ ከተባበሩት አረብ ኢምሬት አቻ ተቋማት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንዲፈልጉ እንደሚያደርግም አቶ ዘሪሁን ተናግረዋል።

በሳሙኤል አባተ
ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም – via Ethio FM 107.8

 • በሀሰተኛ ሰነድ ህጋዊ ባለቤቱ ሳያውቅ ቤት በሸጠውና በተባበረው ላይ ከባድ የሙስና ክስ ተመሰረተ
  በሀሰተኛ ሰነድ ህጋዊ ባለቤቱ በማያውቅበት ሁኔታ የራሱ ያልሆነን ቤት በሸጠው እና በተባበረው ግለሰብ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀልና በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ክስ ተመሰረተ በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ሀሰተኛ ስምና ሰነዶችን በመጠቀም ህጋዊ ባለቤቱ በማያውቅበት ሁኔታ 72 ካ.ሜContinue Reading
 • የታዳጊዉ ወጣት በጎነት -በህግ ማስከበር ዘመቻ
  ታዳጊዉ ወጣት ተመስገን ጥጋቡ ይባላል፡፡ተወልዶ ያደገዉ በሰቆጣ ከተማ ነዉ፡፡አባቱ መቶ አለቃ ጥጋቡ አማረ ይባላል የመከላከያ ሰራዊት አባል ሲሆን ለሀገሩ ሰላም መከበር ሲል መስዋእትነት ከፍሏል፡፡ እናቱ ወይዘሮ በላይነሽ ዳዊት ትባላለች ህፃን እያለ በህይወት እንዳጣት ታዳጊዉ ወጣት ተመስገን ተናግሯል፡፡ አባቱ መቶ አለቃ ጥጋቡ አማረ የመከላከያ ሰራዊት አባል ሆኖ ሀገሩን ሲያገለግል ከቆየ በኋላContinue Reading
 • “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በበጀት ዓመቱ 7.5 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል” የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
  የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘንድሮ በ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት የሚመዘግብበት መሆኑን የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም እንደሚያመላክት ተጠቆመ። የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተካሂዷል። በመድረኩም የበጀት ዓመቱ የስድስት ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። ሪፖርቱን ያቀረቡትContinue Reading
 • በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል
  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ለማስገንባት ላቀዳቸው የኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው የተቋሙ የስትራቴጂ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ተሾመ የተቋሙ የሦስት ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ለውይይት ሲቀርብ እንደገለፁት አስር የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ከንፋስ እና ከፀሐይ ኃይል ለመገንባትContinue Reading

Leave a Reply