በኢትዮጵያ ሰበር ዜና ሞት፣ውድመት፣ ሽብር፣ ሴራ፣ አሽሙር፣ ስድብ፣ ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው። እንደ አዜብ መስፍን ዓይነት ሴት ከሁለት አስርት ዓመት በላይ በተመሳሳይ ሃላፊነት፣ አንጻራዊ ሰላም ባለበት፣ ሁሉንም እንዳሻው የሚነዳ ሃይል እያላቸው እንኳን እነደዚህ ያለ ትምህርት ቤት ሊገነቡ፣ በቦርድ ሊቀመንበርነት ይመሩት የነበረውን የአምኑኤል አዕምሮ ታማሚዎች ሆስፒታል አንሶላ መቀየር፣ ማላታይል አስረችቶ ሀመምተኞቹን ከቱሃን መታደግ አልቻሉም ነበር።ወይዘሮ ዝናሽ ግን በተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች፣ የአዛውንት መኖሪያዎች፣ የአካል ጉዳተኞችን የሚረዱትና የሚያግዙት ቢቀር ዘንድሮ 12ኛውን ትምህርት ቤት አስገንብተው አስረክበዋል።

የመሰረት ድንጋይ እየተተከለ ሲቀለድ እንዳልነበር፣ በዓመት ውስጥ አስራ ሁለት ትምህርት ቤቶችን አስገንብቶ ማስረከብ የድል ጉዳይ ሆኖ በኢትዮጵያ ሰበር ዜና አይደለም። አይናችንና ሃሳብቸን በመልካም ነገር ላይ ስለማያተኩር ዘወትር፣ ለመልካም ዜና ያለን አመልካከት ዝቅተኛ ነው። ሁሉም ሆኖ ግን ቀዳማይ እመቤት ዛሬ ማለዳ ፅ/ቤታቸው ያስገነባውን 12ኛው ትምህርት ቤት በምዕራብ ጉጂ አስመርቀዋል።በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ሱሮ ቡርጉዳ ወረዳ የተገናበው ኢፋ ሱሮ ቡርጉዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።

ግንባታው ጥራቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ሌሎቹ ትምህርት ቤቶች ወደፊት ሊስፋፋ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ፣ መሰረታዊ የመማሪያ ላቦራቶሪና ውብ መቀመጫ ያለው ነው።በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የአሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በርሶ ፣ አባገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንደተገኙ የመንግስት መገናኛዎች ዘግበዋል።

ትምህርት ቤቱ 20 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን አካተዋል።ፅህፈት ቤቱ በዛሬው ዕለት ያስመረቀው ኢፋ ሱሮ ቡርጉዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 12ኛው ነው። በሁለት ፈረቃ 2 ሺህ 600 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለው።የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በትምህርት ቤቱ አካባቢ እና አዋሳኝ ቀበሌዎች የሚገኙ ተማሪዎች እና ወላጆች ይህን ልጆቻቸውን ወደትምህርት ቤቱ እንዲልኩ ተማጽኗል። አሳስቧል።

Leave a Reply