ከንቲባ አዳነች የአዲስ አበባን ጉድ ለሚመሩት ሕዝብ ይፋ አደረጉ፤ ሪፖርቱን በርካቶች ከሳቸው ሲጠብቁት ነበር

ኢትዮ12 ዜና – – በሄዱባቸው ተቋማትና የአስተዳደር ከባቢዎች ማጽዳት ይወዳሉ። በቅርብ የሚያውቋቸው እንደሚመሰክሩት፣ እሳቸው በመሯቸው ተቋማትና ከተማ አስተዳደር አገልግሎታቸውን ያዩ እንደሚሉት ከንቲባ አዳነች የተርመጠመጠ ነገር አይወዱም። አዲስ አበባን እንዲመሩ ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ሲረከቡ ውስብስብ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ቢገመትም በኖረው ባህሪያቸው ይወጡታል የሚል እምነት ከፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን በበርካቶች ዘንድ ነበር።

ከመከረኛው የጎሳ እሳቤ ጋር ተዳምሮ ነጻነት የሌለውና ብዙ ፍላጎት የምንገዋለልባት አዲሰ አበባ ነገሯን ሁሉ ከሽንፍላ ጋር የሚያያዙ እንደሚሉት ታከለ ታከለ ኡማ በርካታ ለውጥ ያስመዘግባሉ ተብሎ ቢጠበቅም በነበራቸው ቆይታ ጥርስ ውስጥ ከመግባት የዘለለ የመሰረታዊ ለውጥ ፍንጭ አላሳዩም ተብለዋል።  እንደውም ሃሜቱ በዝቶባቸው ነው ከስፍራው የተነሱት። “ይህንን የቆሸሸና ሽንፍላ የሆነ አስተዳደር ማን ይምራው” የሚለው ጉዳይ አገሪቱን እየመራ ላለው ብልጽግና ፈተና ነበር። በመጨረሻ አዳነች ተገኙ። አዳነች ገና አዲስ አበባን እንዲመሩ ሲሾሙ ” በዚህ አይቀጥልም” ሲሉ ዙሪያውን አስጠንተው የማቅኛ እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገቡ። ሹመታቸውን የተቃወመም አልነበረም።

የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ከመከታተል፣ የውስጥ አደረጃጀትን ከማስተካከል ጀምሮ ሰፊ ስራ እየሰሩ ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳች አዲስ አበባን ከ1997 ጀምሮ ታከለ ኡማ እስከለቀቁበት ድረስ እንዴት እንዳለፈች በባለሙያዎች የሚመራ ግብረሃይል አቋቁመው አስጠኑ። አስመረመሩ። አስፈተሹ።

ይህንኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ወረራና ባለቤት አልባ ህንጻዎች፣ እንዲሁም ኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቢቶች ዙሪያ የተደረገ የማጣራት ውጤት ዛሬ ይፋ አድርገዋል። ከንቲባዋ ይፋ ያደረጉት ሪፖርት እጅግ ማንም ያልደፈረውና የተድበሰበሰ በመሆኑ ሪፖርታቸው አስገራሚ፣ አስደንጋጭ፣ እንዲሁም ጥናቱ እንዲጠና በግል የወሰዱት አቋም ” አዳነች ከዛስ” የሚያሰኝ ሆኗል።

ዛሬ መግለጫ የሰጡት ከንቲባዋ እንዳሉትና በሰነዱ እንደቀረበው ጥናቱ ከ1997 እስከ 2012 ያሉ ህገ ወጥነ ተግባራትን ነቅሶና ለይቶ በየፈርጁ ያካተተ ነው። በመሬት ዘርፊያ፣ በኮንዶሚኒየም ቤቶች እደላ፣ ስርቆት፣ ዝርፊያ፣ ባለቤት አባል ስለሆኑ ህንጻዎች፣ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም በህገወጥ ወስደው ጥለው ስለጠፉና በቀበሌ ቤቶች ዙሪያ በዝርዝር የተሰሩ ሸፍጥና ድራምዎችን ” ጉድ በል አዲስ አበቤ” እንዲሉ ይፋ አድርገዋል። ጥናቱ ማለባበስ አይሰራም አይነት ይመስላል።

See also  መንግስት ትግራይ እንደሚይዝ አስታወቀ፤ "...እርዱን ወይም ለድርድር አስገድዱልን" ትህነግ

በዚሁ መሰረት ጥናቱ አዲስ አበባ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከ13 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት በወረራ ተዘርፋለች። ይህ ለወትሮ በድብቅ የሚሰማ፣ መረጃና ማስረጃ በአግባቡ የማይቀርብበትን ሃሜትብ ገሃድ ያደረጉት ከንቲባዋ የሚያስተዳድሯት አዲስ አበባ 332 ባለቤት አልባ ህንጻዎች ቆመውባታል።

32 ሺህ የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች እጣ ሳይወጣላቸው  ተያዘዋል። ያለ እጣ ባለቤት የሆኑት ግለሰቦች ህጋዊ ካርታና ሰነድ ተዘጋጅቶላቸዋል። 15 ሺህ 891 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሰው ይኖርባቸዋል። ግን ሰነድ አልባ ናቸው። የወይዘሮ አዳነች አቤቤ መግለጫ ጥናቱ እያጣቀሰ እንዳለው 4530 ኮንዶሚኒየም ቤቶች በአንድ ወቅት ነዋሪዎች ነበሩባቸው። ይሁን እንጂ ዛሬ ነዋሪዎቹ ለቀዋቸው  ጠፍተዋል።

በኮንዶሚኔየም ቤቶች ዙሪያ ያለውን አስገራሚ ድራማ በገሃድ ለሚመሩት ህዝብ ይፋ ያደርጉት ከንቲባዋ ጥናቱን አጣቅሰው እንዳሉት 424 የኮንዶሚኔየም ቤቶች ሰብረው በገቡ ህገወጦች ተያዘዋል። ወደ ቀበሌ ሲወርድ  7723 ቤቶች ማስረጃ የላቸውም።

የቀበሌ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ላይ በተደረገው የማጥራት ስራ ደግሞ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች 138,652 ቤቶች በጥናት እንዲለዩ ተደርጎ 10,565  በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች መገኘታቸውን በከንቲባዋ መግለጫ ቀርቧል።የጥናቱ ውጤቱ በዝርዝር ሲታይ 7,723 መኖርያ ቤቶች ውል በሌላቸው ህገወጥ ነዋሪዎች የተያዙ፣ 265 ቤቶች በሶስተኛ ወገን የተያዙ፣ 1,164 ቤቶች ኮንዶሚኒየም በደረሳቸው ግለሰቦች እንደተያዙ፣ 1,243 መኖሪያ ቤቶች ታሽገው የተቀመጡ፣ 234 የጠፉ ቤቶች፣ 180 ቤቶች አድራሻቸው የማይታወቅ፤ 54 ቤቶች ግን በምን ምክንያት እንደፈረሱ በጥናቱ መለየት ያልተቻሉ መሆናቸውን የጥናቱን ግኝት ተንተርሰው መግለጫ የሰጡት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡537 በህገወጥ መንገድ ወደ ግል ቤትነት የዞሩ የቀበሌ ቤቶች መኖራቸውን ያመለከቱት ምክትል ከንቲባዋ፣ 4,076 በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ የንግድ ቤቶች መገኘታቸውንም ወ/ሮ አዳነች የጥናቱን ግኝትን ዋቢ አድርገው ገልጸዋል፡፡

265 የቀበሌ ቢቶች ለ3ኛ ወገን ተላልፈዋል።1243 ቤቶች የራስቸው ቤት ወይም ኮንዶሚኒየም ባላቸው ነዋሪዎች  የተያዙ ናቸው። 1243 የቀበለኤ ቤቶች በተለያዩ ምክንያቶች የታሸጉ ሲሆኑ 180 ጠፍተው የነበሩ የቀበሌ ቤቶች ሊገኙ እንደቻሉ ከመግለጫቸው ለመረዳት ተችሏል።

See also  መንግስት እንዲገለብጡ ትህነግ ያደራጃቸው ከነሚስጢራዊ ሰነዳቸው ተያዙ፤ ከፍተኛ ባለስልጣናትን መግደል የዕቅዱ መጀመሪያ ነበር

የአዲስ አበባ ተባባሪያችን እንዳለው ከንቲባዋ አዲስ አበባን በተረከቡ አጭር ጊዜ ውስጥ ለሚመሩት ሕዝብ እንዲህ ያለ ግልጽ መረጃ ባለተለመደ መልኩ ማቅረባቸው በይፋ ምስጋና ሊያስቸራቸው ይገባል። ይህ አቋም መግለጫውን ሲሰሙ ከነበሩ የተደመተ ሲሆን፣ ከዚህ ሪፖርት በሁዋላ ምን የማስተካከያ እርምጃ ይወሰድ ይሆን? የሚለውም በተመሳሳይ ተሰምቷል። ታከለ ኡማ አዲስ አበባን ከለቀቁ በሁዋላ የሪፖርተር ጋዜጣን አቋምና ደረጃ ጥያቄ ውስጥ ባስገባ መልኩ የማስተባበያ ቃለ ምልልስ እንዳዘጋጀላቸው ይታወሳል።

ሙሉ  የወይዘሮ አዳነች የጥናት ሪፖርት  እዚህ ላይ ይንብቡ

    Leave a Reply