ፀረ ዘረኝነት አዋጅ ቁጥር —2013 ዓም

መግቢያ – በኢትዮጵያ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በወያኔ ህወሀት የተተከለው የዘረኝነት አስተዳደር መዋቅር እልቆ መሳፍርት ጉዳት ስላደረስ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በጎጥ ተበታትኖ “ህዝቦች” የሚል ከፋፋይ መጠርያ ተሰጥቶት በድህነት አረንቋ እንዲማቅቅ ስለተደረገ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በጎጥ ተከፋፍሎ የጎጥ ቡድን አቋቁሞ በመከፋፈል እርስ በርስ ተጠላልቶ በመቶሺዎች ህይወት ስለጠፋ፣ የአገር ንብረት ስለወደመ፣ ህዝቡ በድህነት አረንቋ መኖሩ አልበቃ ብሎ እድገት ብልፅግና ማምጣት ይቅርና በድህነት ህዝብ እየተራበም፣ እየተጠማም አብሮ መኖር የማይችልበት ሁኔታ ስለተፈጠረ፣ ማንም ሰው ከቤቱ ወጥቶ በሰላም መግባት የማይችልበት ሁኔታ እየተባባሰ ስለመጣ ዘጠና ጎሳ ባለበት ሀገር ዘጠኝ የጎሳ ክልል አዋቅሮ ሰማንያ አንዱን በዘጠኝ ክልል በመጠቅለል እኩልነትን ሆነ ርትዕ ወይም ፍትሐዊነት ማምጣት ያለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ጎሳ ሙሉ ምንነቱ ከቋንቋ እና ባህል ማዳበር ስለማያልፍ የሁሉንም ጎሳ ቋንቋ እና ባህልን በሚመለከት አንድ ኢንስቲቱት በማቋቋም ፋንታ ከአንድ መቶ አስር በላይ የዘር ወይም የጎሳ የፖለቲካ ቡድን ማቋቋም ህዝባችን እና አገራችን በዓለምአቀፍ ሕብረተሰብ እምነት እንዳይጣልብን ከሚያደርግ በቀር ለህዝብ እና ሀገር ጥቅም ስለሌለው በፋሺስት ጥልያን ብሉፕሪንት ተመስርቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ በየትኛውም ክፍለ ሀገር እኩል ባለቤት እና ባለመብት እንዳይሆንና ከጎሳው ውጭ ባለው የአገሪቱ ክፍሎች ባይተዋር ሆኖ የኢትዮጵያዊነት ስሜቱ እንዲዳከም ስላደረገ፣ አገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝባችንን ለመታደግ ህዝቡ በሪፈረንደም የሚፈልገውን ስርዓት እስኪወስን ድረስ በጊዜያዊነት ይህንን የፀረ ዘረኝነት አዋጅ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ — መሰረት ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል።

አንቀፅ አንድ መጠርያ ———– ይህ አዋጅ የፀረ ዘረኝነት አዋጅ ቁጥር —–2013 ዓም ተብሎ ሊጠራ ይችላል።

አንቀፅ ሁለት ትርጓሜ ————– ሌላ ትርጓሜ ካልተሰጠው በቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ያሉ ቃላትና ሐረግ የሚከተለውን ትርጉም ይዘዋል

1. ዘር :- ማለት ጎሳ፣ ነገድ፣ ወይም የግራ ዘመም ፖለቲከኞች ስያሜውን ለማሳመር Sanitized version አውጥተው “ብሔር’ ፣ “ብሔረሰብ” የሚሉትን ይጨምራል

2. የዘር ፖለቲካ ቡድን:- ማለት አንድን ጎሳ፣ ዘር፣ ነገድ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ መሰረት አድርጎ የተደራጀ እንደ አብን፣ ኦነግ የመሳሰሉትን የሚጨምር ሆኖ አንድ የፖለቲካ ቡድን ከአስራ አምስት በመቶ በላይ የአንድ ጎሳ አባላት ካሉት የዘር የፓለቲካ ቡድን ይባላል

3. ሚኒስቴር :- ማለት ይህን አዋጅ ለማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው የሰላም ሚኒስቴር መ/ቤት ነው

4. ዘረኝነት :- ማለት በዘር፣ ነገድ፣ ጎሳ፣ ብሔር ብሔረሰብ ላይ ተመስርቶ ዘመድ አዝማድ መጠቃቀም ሌላውን መጉዳት ወይም ማግለል ነው

5. የጥላቻ ወንጀል፣ ማለት በጥላቻ ወንጀል አዋጅ ከተሰጠው ትርጉም በተጨማሪ ዘር ተኮር ስድብ አካላዊ ጥቃት ማድረስ ሲሆን በካርቱን፣ በፅሁፍ፣ በምልክት መሳደብን ይጨምራል አንቀፅ ሶስት የአፈፃፀሙ ወሰን —-

1. ይህ አዋጅ በፓለቲካ ቡድኖች ብቻ ሳይሆን እቁብ፣ እድር፣ የስፓርት ቡድኖች በመሳሰሉ ማህበራዊ እና ባንክ ፣ ኢሹራንስ በመሳሰሉ የኤኮኖሚ ተቋማትም ላይ ተፈፃሚ ይሆናል

2. ከላይ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከቱት ተቋማት ላይ የዚህን አዋጅ አፈፃፀም እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን በሚመለከት የሚኒስቴር መ/ቤቱ ዝርዝር መመርያ ያወጣል አንቀፅ አራት የተቋቋሙ የዘር ቡድኖች –

1 . ይህ አዋጅ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በዘር ላይ የተቋቋሙ የዘር የፖለቲካ ቡድኖች ፈርሰዋል

2. በዚህ አዋጅ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት የፈረሱ የፓለቲካ ቡድኖች ቋሚ ንብረት በባንክ ያለ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ስራ ይውላል ።

አንቀፅ አምስት ኦዲት —-

1. ከላይ በአንቀፅ 4/1/ በተመለከተው መሰረት የፈረሱ የፓለቲካ ቡድኖች ንብረት መንግስት በሚመድበው ኦዲተር ምርመራ ይደረግበታል

2. ኦዲት እስኪደረጉ ሚኒስቴሩ መ/ቤት ያሽገዋል አንቀፅ ስድስት ዕዳ እና እገዳ —————– በፍርድ ቤት የታዘዘ ዕዳ እና እገዳ በሚኒስቴሩ መ/ቤት ይስተናገዳል አንቀፅ ሰባት የተሻሩ ሕጎች —————— ከዚህ አዋጅ ጋር የሚጋጩ አዎጆች ፣ ደንቦች፣ መመርያዎች እና የሕገ መንግስቱ አንቀፅ —— እና —— በሞላ ይህንን አዋጅ በሚመለከት የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ አዋጅ ከፀደቀ ከሶስት ዓመታት በኋላ በሪፈረንደም እስኪውስን ድረስ በጊዜያዊነት ተፈፃሚ አይሆኑም አንቀፅ ስምንት ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆንበት ጊዜ ———————- ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል። አዲስ አበባ፣ —– —–ቀን 2013 ዓም

Guangul Teshager J እንዲዳብርና ይበልጥ በስሎ ለመንግስት እንዲቀርብ ያቀረቡት ነው። በፊስ ቡክ ገጻቸው ማግነት ይቻላል


  • በሀሰተኛ ሰነድ ህጋዊ ባለቤቱ ሳያውቅ ቤት በሸጠውና በተባበረው ላይ ከባድ የሙስና ክስ ተመሰረተ
    በሀሰተኛ ሰነድ ህጋዊ ባለቤቱ በማያውቅበት ሁኔታ የራሱ ያልሆነን ቤት በሸጠው እና በተባበረው ግለሰብ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀልና በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ክስ ተመሰረተ በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ሀሰተኛ ስምና ሰነዶችን በመጠቀም ህጋዊ ባለቤቱ በማያውቅበት ሁኔታ 72 ካ.ሜContinue Reading
  • የታዳጊዉ ወጣት በጎነት -በህግ ማስከበር ዘመቻ
    ታዳጊዉ ወጣት ተመስገን ጥጋቡ ይባላል፡፡ተወልዶ ያደገዉ በሰቆጣ ከተማ ነዉ፡፡አባቱ መቶ አለቃ ጥጋቡ አማረ ይባላል የመከላከያ ሰራዊት አባል ሲሆን ለሀገሩ ሰላም መከበር ሲል መስዋእትነት ከፍሏል፡፡ እናቱ ወይዘሮ በላይነሽ ዳዊት ትባላለች ህፃን እያለ በህይወት እንዳጣት ታዳጊዉ ወጣት ተመስገን ተናግሯል፡፡ አባቱ መቶ አለቃ ጥጋቡ አማረ የመከላከያ ሰራዊት አባል ሆኖ ሀገሩን ሲያገለግል ከቆየ በኋላContinue Reading
  • “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በበጀት ዓመቱ 7.5 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል” የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
    የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘንድሮ በ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት የሚመዘግብበት መሆኑን የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም እንደሚያመላክት ተጠቆመ። የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተካሂዷል። በመድረኩም የበጀት ዓመቱ የስድስት ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። ሪፖርቱን ያቀረቡትContinue Reading

Leave a Reply