ትህነግ – ሚስጥሩ “ሚስጥር” የሆነበት ተዋጊ!! የፕላኔቱ ሆቴል ሚስጢር ዜሮ ብዜት!!

ኢትዮ 12 ዜና – “ ሚስጢር ነበር” ይላል የኢትዮ 12 መረጃ አቀባይ። ሚስጥሩ በሚስጢር የተቆለፈ መሆኑንን የማያውቁ ሚስጢረኞች ሲል ተንደርድሮ ፓርላማ ይገባል። ፓርላማ ገብቶ ከትንታኔው ይቆነጥርና ማብራሪያውን አለት ያደርገዋል። በዚሁ ማብራሪያ “መብረቃዊ ጥቃት” ይልና፤ “ቁንጫ” ሲል ትዝብቱን ያክላል።

“ ወታደራዊ እውቀት የሌላቸው፤ ዘመናዊ ጦርነት የማያውቁ” ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ ላላመኑና ተራ ፉከራ ለመሰላቸው ትህነግ ተረት የሆነበትን ቁልፍ ጉዳይ ያብራራሉ።

ትህነግ ወደ ጦርነት የሚገባበት ቀናት ሲቃረብ በመቀለ ያሉ የአየር ሃይል የጦር ጀት አብራሪዎች ፕላኔት ሆቴል ይጠራሉ “ የትም እንዳትሄዱ፣ በቅርቡ ትፈለላላችሁ …” የሚል መመሪያና አደራ ይነገራቸዋል። አብራሪዎቹና ሃላፊዎቹ በነገሩ ግራ ቢጋቡም የተባሉትን ተቀብለው ወደ ስፋራቸው ይመለሳሉ። የደብረዘይት አየር ሃይል ድግሱን ይወቅ አይወቅም ቢያውቅ ጥቅሙ ምን እንደሆነ … የገባውም ያልገባውም ሚስጢር ይዞ፣ ሚስጢር ላይ ተኝቶ፣ በሚስጢር … የፕላኔት ሆቴል ሚስጢር ድምር ዜሮ ብዜት እንዲህ ነው።

የትግራይ አየር ሃይል ጀቶችና ቀለባቸው

መቀለና አክሱም የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሰባት ተዋጊ ጀቶቹ በተጠንቀቅ ነበሩ። አስፈላጊው የቴክኒክ ብቃትና ትጥቃቸው አስተማማኝ፣ ለኦፕሬሽን ዝግጁ የሆኑ፣ የሚጫኑት ቀለባቸው የተደራጀ፤ እንደ መረጃው መቀለ ያለው የመሳሪያ ግምጃ ቤት ለጀቶቹ ስንቅ ሞልቶታል። እንደውም ደብረዘይት ካለው ይበልጣል።

ሚስጢር አንድ

በፕላኔት ሆቴል አብራሪዎቹም ሆኑ የቅርብ አለቆችና የቴክኒክ ሰዎች የትም እንዳይሄዱ፣ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ በድጋሚ ተነገራቸው። የተፈልጉበት ጉዳይ ዝርዝር ባይቀርብም “ አለቃችሁን በቅርብ እናስተዋውቃችኋለን” ተብለዋል። ነገሩ ግራ የሚያጋባ ቢሆንም መመሪያውን ተቀብለው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ መጡበት ተመለሱ። ይህ ሲሆን የትግራይ መከለከያ “ ኤታማዦር ሹም ” ጀነራል ታደሰ ወረደና የአይቲ መሃንዲስ የሚባሉት ደብረጽዮን ነበሩ። አንጋፎቹን ጨምሮ።

ሚስጢር ሁለት

ሁለተኛው ሚስጢር አንደኛውን ሚስጢር የገደለው “ ረቂቁ ሚስጢር” መሆኑን ከመግለጽ ውጪ የሚባል ነገር የለም። የመርዳሳን ልጅ ሲናገሩም የሰማቸው ያለ አይመስልም። ወይም ለግብጽ ሲናገሩ ጉዳዩ ለአገር ውስጥ እንደማይሰራ ተደርጎ ታስቧል። እና ምን ሆነ?

See also  በአሸባሪው ህወሃት የወደሙ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የቻይና መንግስት ድጋፍ ተጠየቀ

የመጨረሻዋ ሰዓት

“ ጦርነቱ ሲጀመር አለቃችሁን እናስተዋውቃችኋለን” በተባለው መሰረት የትግራይ ምድብተኛ የአየር ሃይል አባላት ፕላኔት ሆቴል አመሻሹ ላይ ይገኛሉ። አዲሱ አለቃም ቁጭ ብለዋል። መንግስት “ ህግ ማስከበር” የሚለው ዘመቻ መከላከያ ሰራዊት ከተመታ በሁዋላ ተጀምሯል። በሁመራ ግንባር ከአየር ማረፊያው ጀርባ የተገነባው ከባዱ ምሽግና ሃይል በመድፍ እየተነረተ ነው። ዋናው የጦርነቱ ብልት እዛ በመሆኑ ድብደባው አላቋረጠም። ድብደባው መልስ መመለስ እንዳያስችል ተደርጎ ጠንክሮ ሲካሄድ … ስለ ሁመራ ግንባር ጀግነንት አገር የሚጠቅም ሲሆን የመረጃ ምንጩ ይመለሱበታል።

የአየር ሃይሉ አባላት የጀት ጥቃት እንደሚጀመርና በማንኛውም ሰዓት መመሪያ ሲሰጥ የጀት ድብደባ ለማድረግ ዝግጁ እንዲሆኑ ተነገራቸው።

ደብረዘይት – የሚስጥር ቋት

“ ሰውየው” ነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስም። መረጃውን እንደወረደ ያቀረበው የትግራይ ባለስልጣናት የቅርብ ሰው፣ ሰውየው አየር ሃይሉን ኪሳቸው ይዘውት እንደሚዞሩ ያህል አዲስ ቴክኖሎጂ መታጠቃቸውን ያስረዳል።

ፕላኔት ሆቴል ከተጠሩት የአየር ሃይል ጀት አብራሪዎችና ሹሞች መካከል አንድ ኮሎኔል “ ለምን እስካሁን ሚስጢር አደረጋችሁት” ሲሉ መርዶውን ጀመሩት።ቀጠሉና “ ሚሽን የምንቀበለው እኮ ከደብረዘይት ብቻ ነው” አሉ። ሌሎች ጣልቃ ሳይገቡ “ ጦርነቱ በተጀመረ ሰዓታት ውስጥ የሚስጢር ቁልፉ ተቆልፏል። ጀቶች ማንቀሳቀስ አይቻልም ” አሉ። ፕላኔት ሆቴል ያልታሰበ ፕላኔት ወደቀ!! ዝምታ!!

ይልማ መርዳሳ – ብ/ጄነራል

የህዳሴውን ግድብ ግንባታና የጸጥታ ሁኔታ ለሕዝብ ሲያስታውቁ “ አየር ሃይላችን ምንም አይፈለጭበትም። አንድ ሰው ሃያ አራት ሰዓት የሚቆጣጠረው ተቋም ነው። ዓለም ላይ ያለውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታጥቀናል” ብለው የአየር ሃይል አዛዡ ሲናገሩ ሰሚ ጆሮ አልነበረም። የዛሬን አያድርገውና “ እነዚህ ሰዎች ምላስ እንጂ ጆሮ የላቸውም” ሲሉ ዶክተር መራራራ ተናግረው ነበር።

ከለውጡ ማግስት “ ሽርሽር ያበዛሉ፣ ሰው እየሞተ አረብ አገር ይዞራሉ፣ ፈረንሳይን ቤታቸው አደረጉት” ሲሉ የነበሩ መኖራቸውን የመረጃው ሰው አስታውሰው “ የሁሉም ቦታዎች ምልልስ ዓላማ ነበረው” ሲሉ የአየር ሃይሉ መዘመን ሆን ተብሎ የተደረገ፣ ልክ ከኤርትራ ጋር እንደተደረገው ስምምነት ልዩ ትርጉም የነበረው ነበር። እናም ኢትዮጵያ አየር ሃይሏን በአንድ ክሊክ መቆላለፍ የምትችል አገር ተደርጋለች። ይህ ሁሉ ሲሆን በስለላ አናት ላይ መቆሙን የሚናገረው ትህነግ አያውቅም።

See also  የሶማሊያ ድርቅ፡ "አሁኑኑ እርምጃ ካልተወሰደ 350 ሺህ ሕፃናት ይሞታሉ"

ሰውየው

ሰውየው የዋዛ አለመሆኑ አስቀድሞ የገባቸው “ እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መርህ የዲጂታልና የውክልና ዘመቻ በማለዳ ቢጀመሩም፣ “ እሱ መሪ መሆን የለበትም” በሚል ለቀናት ያነታረከው ጉዳይ እዚህ ላይ ግልጥ ብሎ ይታያል። በኮድ ግንኙነት፣ በተናበበ ስም ማጥፋት፣ ስኬታቸውን በማጠልሸት፣ ኦሮሞ አይደሉም ተብሎ እስከመሰደብ የደረሱት ሰውዬ፣ ተንጠልጥለው ለፍርድ እንደሚቀርቡ፣ ጦላይ ወይም ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ይከረቸምባቸዋል የተባሉት ሰውዬ፣ ቤተ መንግስት ከገቡባት ሰዓት አንስቶም አሳራቸውን ሲያዩ የከረሙት የበሻሻው ሰውዪር “ ኢትዮጵያን እየመሩ ነው”

ጦርነቱን በጀት አግዞ ሊያስኬደው የነበረው ትህነግ ሳይሆንለት የቀረው “ ‘ሚስጥር’ የሆነበት ተዋጊ!! የፕላኔቱ ሆቴል ሚስጢር ዜሮ ብዜት” ባለቤት ባይሆንና ጀት ቢያስነሳ ብለን አናስብ፣ ጀት ቢነሳ እነማን ከተሞች ቀድመው ይደበደባሉ? እልቂቱ ምን ይሆን ነበር? ደግነቱ አምላክ ከተገፉት ጋር ነው። ቁልፉ ሰውየው እጅ ነው።

Leave a Reply