ጥቂት የዘይት ነጋዴዎች ምርታቸውን ያሸሻሉ፤ መንግስት አርምጃ መውሰድ ጀምሯል

በዘይት ዋጋ ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡ጥቂት የዘይት ነጋዴዎች ምርታቸውን እነደሚያሸሹ መረጃ ያላቸው አየጠቆሙ ነው።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ አከበረኝ ውጋገን በቅርቡ በዘይት  ዋጋ ላይ የተከሰተው የዋጋ ጭማሪ ምክንያታዊ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎም  ዋጋውን ለማረጋጋት  የንግድ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ  ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡ ስምምነቱም የዘይት ዋጋ ከሁለት ወር በፊት ወደ ነበረበት የመሸጫ ዋጋ እንዲመለስ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ይሁን እንጂ በስምምነቱ መሰረት ዘይት ዋጋ ቅናሽ አለማሳየቱን በመዲናዋ ጉዳዩ ለመከታተል የተቋቋመው ግብረ ሃይል በዳረገው ቅኝት ማረጋገጡን አንስተዋል፡፡ በዚህ መሰረትም ቢሮው ባለ 5 ሊትሩን ዘይት ከ360 ብር በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጹት፡፡

በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 240 በሚደርሱ የንግድ ተቋማት ላይ በተደረገ አሰሳ 10 የሚሆኑት ከስምምነቱ ውጪ ሲሸጡ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት አቶ ወጋገን፣ ከዛሬ ጀምሮም  አምስት ሊትሩንን ዘይት 360  ብር በላይ  በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ የማሸግ እርምጃ ይወሰዳል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ጎን ለጎንም ነጋዴዎች ምርታቸውን ወደ ክልሎች ለማውጣጽ ሙከራ ያደርጋሉ የሚሉት ምክትል ሃላፊው ይህንን ለመቆጣጠርም ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል የዘይት አስመጪዎች እና አከፋፋዮች በተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ ብቻ እንዲሰሩ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም አውስተዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍም የአቅርቦት ፍላጎትን ማሳደግ ዋነኛ መፍትሄ መሆኑን የገለጹት አቶ አከበረኝ ለዚህም፣ በዘርፉ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ ተቋማትን ምርት ለመጨመር ይሰራል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከውጪ የሚያስገቡ ነጋዴዎች ጉምሩክ አካባቢ የሚያጋጥማቸውን ችግር በመቅረፍ በፍጥነት ወደ ተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ – (ኤፍቢሲ) – ethio 12 ዜናው ማሻሻያ ተደርጎበታል


 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
  ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸዉና ከምትከበርባቸዉ ሀገራዊ ልዩ እሴቶቿ ዉስጥ አንዱ የዘርፈ ብዙ ልዩነቶች የመቻቻል ምድር መሆኗ ሲሆን ህዝቦቿ በፈረሃ አምላክ የሚመሩ ናቸዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን የሀይማኖት ብዝሃነትን […]
 • Ethiopia tows 2.3bln USD remittance a year less
  ADDIS ABABA – Ethiopian Diaspora Agency disclosed that the country has secured 2.3 billion USD in remittance from the Diaspora over the past eight months. Agency Director-General Selamawit Dawit told the […]
 • Ethiopia, World Bank seal 200 mln USD loan agreement
  ADDIS ABABA—Ethiopia and World Bank signed 200 million USD loan agreements to support the implementation of Digital Foundation project. As to the information obtained from the Ministry of Finance and […]
 • የቆዳ ዋጋ መውደቅና አገራዊ ኪሳራው
  ድሮ ድሮ በደጋጎቹ ዘመን “ጮሌዎቹ” በግ ከአርሶ አደሩ በስሙኒ ገዝተው ቆዳውን መልሰው በስሙኒ በመሸጥ ስጋውን በነጻ “እንክት” አድረው ይበሉ ነበር ይባላል። ታዲያ የስጋን ያህል ዋጋ ያወጣ የነበረ የቆዳ ዋጋ ከቅርብ […]

Categories: SOCIETY

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s