በአማራ ክልል የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ችግርአለ፤ የጥቁር ገቢያ ሽያጭ አንዱ ፈተና ነው

 • 100 የነዳጅ ማከፋፈያ ቦታ ከክልሉ መንግስት ተጠይቆ እስካሁን 10 የነዳጅ ማከፋፈያዎች

በአማራ ክልል በተደጋጋሚ የሚታየውን የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እጥረት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር የአማራ ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ውይይት አካሄደ ።

በውይይቱ  የክልል የንግድና ገቢያ ልማት ሀላፊዎች፣ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊዎች የነዳጅ  ማደያ ባለቤቶች፣ የዞን የየንግድና ገቢያ መመሪያ  ሀላፊዎች  ተሳትፈዋል።

የክልሉ የንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ተዋቸው ወርቁ እንደገለፁት በክልሉ የነዳጅ አቅርቦትና የስርጭት   ችግር መኖኑን በፅሁፍ አቅርበዋል ።

ከዚህ ባለፈ የጥቁር ገቢያ ሽያጭ እና የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ በፌድራል  ሊፈቱ የሚችሉ የህግ ማቀፍ፣ የፍትሃዊነት እና ሌሎችም ችግሮች  በምክንያትነት  ተጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ  የነዳጅ ማደያዎች  ቁጥር ማነስ እና የነዳጅ ማስፋፊያ  በክልሉ አለመኖር  ዋናዎቹ ችግሮች  መሆናቸውን  አቶ ተዋቸው አንስተዋል።

ተሳታፊዎች  በበኩላቸው  ለነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት  እጥረት ዋናው ችግር መንግስት የአቅርቦት  ችግሩን  መፍታት  አለመቻሉ ነው ብለዋል ።

ተሳታፊዎች አክለውም  የመንግስት  ህገወጥነትን  በመቆጣጠር  በኩል ደካማ መሆኑን ተናግረዋል ችግሩን  በረጅም እና በአጭር ጊዜ ለመፍታት  ,እየተሰራ  መሆኑን አቶ ተዋቸው ገልፀዋል።

በረጅም  ጊዜ ውስጥም  በክልሉ  በአዲስ 812 ነዳጅ ማደያዎች  ለመግባት  እየተሰራ ሲሆን እስካሁን 119ቱ ቦታ ተሰጥቷቸው  ለመገንባት በዝግጅት  ላይ መሆናቸውን  አስረድተዋል።

100 የነዳጅ ማከፋፈያ ቦታ ከክልሉ መንግስት ተጠይቆ እስካሁን 10 የነዳጅ ማከፋፈያዎች መገንባታቸውንም ገልፀዋል።

ከአጭር ጊዜ አኳያም የጥቁር ገቢያ ሽያጭን ለመቆጣጠር  ከምሽቱ 1 ስአት እስከ ጧቱ 12 ስአት የነዳጅ  ሽያጭ እንዲቆም እና የቀን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

የነዳጅ አቅርቦት እና የስርጭት እጥርት ችግር  የሚቆጣጠር  ግብር ሀይልም ከአጋር አካላት ጋር መቋቋሙ ተጠቅሷል።

በናትናኤል ጥጋቡ – fbc


 • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
  የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
 • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
  “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
 • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
  አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading
 • የሽብርተኛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሠራዊታችንን የድል ግስጋሴ አይገታውም !
  ሽብርተኛው ከሚታወቅባቸው ስልቶቹ መሀል አንዱ ቅጥፈቱ ነው ፡፡ ጉልበት ሲያንሰው ምላሱ ይረዝማል ፤ ያልሆነውን ሆንኩ ፣ ያላደረገውንም አደረኩ…ይላል ፡፡ ይህ ደግሞ ጥርሱን የነቀለበት እና ተወልዶ ያረጀበት ባህሪው ነው ፡፡ አንድም ቀን ከአፉ እውነት ተገኝታ የማታውቀው ይህ ሽብርተኛ ፣ ሽንፈቱን የሚሸፍነው የሠራዊታችንን ስም በማጠልሸት ነው ፡፡ ደጋፊዎቹ ኪሳራውን እንዳያወቁ ፣ ሰላማዊውContinue Reading

Leave a Reply