… ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ …

Opinion.-

በወቅታዊ የአገራችን ችግር ምእራባውያን የሚያሳዝን አቋም ይዘዋል፣ እንደኔ አረዳድ የወያኔ ዲችሎማቶች ብቻ ሳይሆን የግብጽና አንዳንድ የሱዳን ዲፕሎማቶችም ከፍተኛ ዘመቻ እያደረጉ ነው ።

በአንተ መስሪያ ቤት አስተባባሪነት አዲስ አበባ ቢሰራ ትንሽም ቢሆን ውጤት ያመጣል ብየ ያሰብሁትን እየው እስኪ።

1ኛ ከምሁራንና ከተቃዋሚ ድርጅቶች የተውጣጡ የውይይት መድረክ አዘጋጅተው ስለ ወቅታዊ የትግራይ ህግ የማስከበር ዘመቻ ጥናታዊ መሰል ውይይት ቢያካሂዱ፣ ከተቻለ ከጅቡቲ ኬንያና ዩጋንዳ እንዲሁም ሌላ አፍሪካ አገር የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተሉና እኛን የሚደግፉ ምሁራን ስፖንሰር ተደርገው ቢመጡና ጽሁፍ ቢያቀርቡ፣

ተጋባዥ እንግዶች፣
 የውጭ ዲችሎማቶች  የእርዳታ ድርጅቶችና ምሁራን፣

የሚነሱ ነጥቦች፣
1.1 ወያኔ በህገወጥ የአገሪቱን ትጥቅ ሰርቆ ወስዶ አገር የማፍረስ ሙከራ ማድረጉና ጦርነቱን እራሱ መጀመሩ፣

1.2 መከላከያችንና ልዩ ሀይላችን ሲቪልያና ተቋማት እንዳይጎዱ በጥንቃቄ ጦርነቱን እንደጨረሱት፣ ከነበረው ችግር አኳያ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ፣ 

1.3 በተለያዩ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ (ሶርያ የመንና ሊብያ) በተደረገው ጦርነት ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ሙሉ ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ፣ ከተማዎቻቸውም እንደወደሙ ሳምፕል ዳታ ሰብስበው ማብራራት፣

1.4 የትግራይ ዘመቻ ከነዚህ ጋር ሲነጻጸር እጅግ በጣም አነስተኛ እንደሆነ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ በአለም ላይ ተደርጎ የማያውቅ በጣም የሚያስመሰግንና የሚያሸልም ሰብአዊነት የተሞላበት ጦርነት ማካሄዱን ማብራራት፣ 

1.5 የኤርትራን ጣልቃ መግባት ሁኔታ፣
ምእራባውያን በሊብያ ሶርያ ማሊ የመን በአየርና በምድር በግልጽ ጦርነት ውስጥ የተሳተፉት ህግ ለማስከበር ነው፣ ውጤቱ ግን ትቂት የነበሩትን ህገወጦችና ሽብርተኞች ብዙ አደረጓቸው፣ ሊቢያን ሶርያንና የመን በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝባቸው ያለቀው የተፈናቀለው ከተሞችና ተቋማት የፈረሱት በምእራባውያን ጣልቃ ገብነትና ወታደሮች መሆኑን በደንብ ማብራራት፣

1.6 ኤርትራ በትግራዩ ጦርነት ገብታም ከሆነ ይህ የኢትዮጵያውያን ህዝብ ፍላጎትና ችግር መሆኑን፣ ወያኔ የሰራው የሽብር ስራ እንኩዋን የተጠቃችውና ጎረቤታችን ኤርትራ ቀርቶ ሌላ ባእድ አገር ከአውሮፓም ሆነ እስያ ጣልቃ ቢገቡ ህጋዊነት እንዳለውና የሞራል ግዴታ መሆኑን ማብራራት፣

ምእራባውያን የተናደዱበትና የተሳሳተ አቋም የያዙት ጦርነቱ ቶሎ በመጠናቀቁና ውድመት ሳይደርስ በመቅረቱ ተናደው ነው፣ ውድመት እንዲደርስ የፈለጉበት ምክንያት የእርዳታ ድርጅቶቻቸውን አስገብተው አካባቢውን ለረጅም ግዜ የግጭት ቀጠና ለማድረግ ፈልገው መሆኑን በድፍረት ቢያብራሩ፣

See also  የሰሜኑ ጦርነትና የመላ ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነት !   እስክንድር ነጋ! ቂልንጦ አዲስ አበባ

በዚህ ውይይት ላይ የመንግስት አካላት ጥናት አቅራቢ ሆነው ባይገኙበት ጥሩ ነው፣ ውይይቱ በምሁራን ተነሳሽነት የተደረገ ቢመስል፣

ከምስጋና ጋር

ያረጋል ይማም

Leave a Reply