አዳነች አቤቤ የጥናት ግኝቱ ለአቃቤ ህግ መመራቱ አስታወቁ

የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በተጠናው ጥናት መሰረት ህግ ፍርዱን እንዲሰጥ የጥናት ግኝቱ ለፌደራል አቃቤ ህግ መላኩን አዳነች አቤቤ አስታወቁ። ጥናቱ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ የኮተቤ ሜትሮ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ መስፈርቱን ያሟላ ብሎታል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተጠቀሱትና በጥናቱ የተካተቱት ጉዳዮች በህዝብ ዘነዳ ከፍተኛ ቅሬታ ሲስተናገድባቸው የቆዩ ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን አመልክተዋል። ከንቲባዋ በማህበራዊ ገጻቸው እንዳሉት በጥናቱ ግኝት መሰረት ማስተካከያ ተወስዶ ፍትሃዊ አገልግሎት ይሰጣል።

አገልግሎቱን ፍትሃዊ ከማድረግ በተጨማሪ በጉዳዩ የተሳተዱ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ይሆኑ ዘንድ ሰነዱ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ መላኩን ትፋ አድርገዋል። በተደጋጋሚ ሲነገር እንደነበረው ቀደም ሲል ከሌብነት ጋር በተያያዘ ስማቸው የሚነሳና ከፍተኛ ሃብት የሰበሰቡ የህግ ተጠያቂነትን ፍርሃቻ ስላለባቸው ለውጡን ጠልፈው ከሚጥሉ ጋር በሴራ ፖለቲካው ውስጥ ተሳታፊ ሆነው እንደቆዩ ሲዘገብ ነበር።

ለውጡ ከተረጋጋና መልክ ከያዘ ተጠያቂነት ሊነሳ ያችላል በሚል ስጋት አንድ እግራቸው ለውጡ አራማጆች ዘንድ፣ ሌላኛውን ከአደናቃፊዎቹ ጋር በማድረግ የሚነቀሳቀሱ መኖራቸውን መንግስት፣ ህዝብ፣ የሴራው ሰላባዎች፣ እንዲሁም የፍትህ አካላት በተደጋጋሚ ሲያስታወቁ ነበር።

አጋጣሚውን ጠብቀው በዝርፊያ የተሰማሩ ወፍ በረር ህገወጦች መኖራቸው በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደነበር፣ በቡድን መጥተው አንድን አካባቢ በመውረር በትሥሥር ህጋዊ የማድርገና ተግባር በፋት አዲስ አበባ ውስጥ መከናወኑ ቀደም ሲል ጀመሮ የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርብባቸው ሲሆን፤ መንግስት ህግ ሲያስከበር ማህበራዊ ቀውሱን በማጉላት መንግስትን የሚያወግዙ፣ አውሬ አድረገው የሚያሳዩ፣ እንዲሁም ህግ ማስከበሩን ከብሄርና ከቡድን ፍላጎት ጋር በማያያዝ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲሰጣቸው መደረጉ ለህገወጦች ከፍተኛ ድጋፍ እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ገጻቸው ይህንን ብለዋል።

May be an image of text that says 'Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ new photos. Album ህገወጥ የጋራ መኖሪያቤቶች added 4 የከተማችን ነዋሪ ዋነኛ የቅሬታ ምንጭ ሆኖ የቆየውን የጋራ መኖርያ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) እና የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ በተጠናው ጥናት መሰረት 21,695 የጋራ መኖርያ ቤቶች በተለያየ ህገ-ወጥ መንገድ መያዛቸውን አረጋግጠናል። በተጨማሪም ለጥናት እንዲለዩ ከተደርጉ የቀበሌ ቤቶች 14,641 ያለ አግባብ ለመኖርያና ለንግድ የተከራዩ፣ ውል የሌላቸው እና በሌላ በህገ-ወጥ ይዞታነት የሚገኙ መሆኑን አረጋግጠናል። በግኘቱ መሰረት ህጉን ተከትለን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን። በጉዳዩም የተሳተፉ አካላት ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ግኝቱን ወደ ፌደራል ዐቃቤ ህግ እና ፌደራል ፖሊስ መርተናል።'
See also  አሜሪካ ወጣች ታሊባን ገባ

Leave a Reply