olf candidate

ነፃ መሬትና በቂ ሬሽን ለማግኘት ወደ ትግራይ እንድንሄድ ታዘናል – የኦነግ ሸኔ ታጣቂ

የህወሓት የጥፋት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጪሊሞ ጫካ ስልጠና ላይ የነበሩ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጁንታውን ለማገዝ ወደ ትግራይ መጓዛቸውን በተሃድሶ ስልጠና ላይ የሚገኘው ወጣት ተናገረ።ከህወሓት የጥፋት ቡድን ጎን ተሰልፎ የነበረውና አ

አሁን በደቡብ ዕዝ የማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና እየወሰደ የሚገኘው ወጣት ዕድሜው ከ20ዎቹ መጀመሪያ አይዘልም።ወጣት ፈይሳ ተካ ግንደበረት አካባቢ ተወልዶ ማደጉን፤ ከአንድ ዓመት በፊት በኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን በአባልነት መመልመሉንና ለስድስት ወራት ገደማ በጪሊሞ ጫካ ወታደራዊ ስልጠና መውሰዱን ይናገራል።

የህወሓት ቡድን ጦርነት መክፈቱ በተነገረበት ሰሞን 26 አባላት ካካተተው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ጋር ‘ነጻ መሬትና በቂ ሬሽን ለማግኘት’ በሚል ወደ ትግራይ እንዲሄዱ እንደተነገራቸው ገልጿል።በኋላም ‘የኦሮሚያ ልዩ ኃይል’ የሚል መታወቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ደቡብ ትግራይ ራያ ግንባር መጓዛቸውን ተናግሯል።

May be an image of 5 people, people standing, outdoors and crowd

በራያ ግንባር ‘ብሶበር’ በሚባል ስፍራ ከጁንታው ታጣቂ ኃይል ጋር በመሆን ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ውጊያ መግጠማቸውንም እንዲሁ።በዚሁ ግንባር የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከትግራይ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ሲቪሎችም ተሰልፈው መዋጋታቸውን ወጣት ፈይሳ ተናግሯል።ጦርነቱ እየጠነከረ በመሔዱ የጁንታው ታጣቂዎች ሲያፈገፍጉና ሲበታተኑ ፈይሳን ጨምሮ የተቀሩት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችም መበታተናቸውን ገልጿል።በራያ ግንባር የመከላከያ ሰራዊት ጠንካራ እርምጃ ወስዶ አካባቢውን ሲያስለቅቅ ሁሉም መበታተናቸውንና አብረውት የነበሩትም የት እንደሆኑ እንዳማያውቅ ነው የተናገረው

See also  ህይወታቸው ካለፈ ሰባት ዓመት በሁዋላ የፕሬዚዳንቱ ሰምንት ቤተሰቦቻቸው ተገደሉ ? ትህነግን ለማንገስ ስንት ኦሮሞ ይገደል?

Leave a Reply