የደብረጽዮን ድምጽ ተሰማ ከተባለ በሁዋላ በፓልቶክ የትህነግ ወዳጆች ውይይት ላይ ” የአብይ መንግስት አንድ እገሩ አፋፍ ላይ ነው። ቶሎ ቶሎ ከኦሮሞና ከሲዳማ ጋር የኮንፌደሪሽን ግንኙነት ማድረግ አለብን፤ እነሱም እኛም ነጻ አገር ሆነን መቀጥል የምንችልበትን ትብብር ማስፋት አለብን” ሲሉ የድል ብስራት ሲያሰሙ ነበር። በዚሁ የፓልቶክ ውይይት ሱዳን ወደፊት እንደምትገፋ፣ሌላም የሚከተል ሃይል እንዳለ፣ ቤኒሻንጉል ላይም ጥያቄ እየተነሳ እንደሆነና የህዳሴውም ግድብ የሱዳን መሬት ላይ እንደተገነባ አንስተዋል። በውይይቱ አንዳንድ አስቀድመው በጭምጭምታ ይሰሙ የነበሩ ጉዳዮች ይፋ የሆኑ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ ለማስጣል የተጀመረው ዘመቻ ውጤት እንደሚያስመዘግብ በሙላት ይነገሩ ነበር። ጌታቸው አሰፋን በማድነቅም አበባ ሲረጭ ታይቷል።

ኖርዌይ ኦስሎ ባቡር መሳፈሪያ ውስጥ ሁለት አበሾች ብትር ቀረሽ ክርከር ያደርጋሉ። የክረከሩ አጀንዳ ጌታቸው አሰፋ የሚባሉት የትህነግ ትልቁ ሰው፣ የአገር ደህንነት ዋና ዳይሪክተር የነበሩት፤ አንደኛው ተከራካሪ ” አደገኛ፣ ዓለምን ያስደመመ ጀግና” ሲላቸው፣ ሌላኛው ድሮ መሸዋውዱን ጠቅሶ ” እሱ ደንቆሮ ምሁር ነው” ይላል።

ይህን ሪፖርት ያዘጋጀው ተከራካሪዎቹን ባቡር እየተበቀ ከመስማት ውጭ አስተያየት አይሰጥም። ግን ክርክሩን እንዲሰማ የተፈቀደለት ያህል እስኪለያቸው አድምጧቸዋል። የክርከሩ ጭብጥ መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ ባይታውቀም፣ ጌታቸው አሰፋ ሊያዙ ወይም ሊገደሉ ይችላሉ የሚለው ጉዳይ ላይ ነበር ሁለቱም የበኩላቸውን ሲሉ የነበሩት።

ክርክሩ ብስለትና ቀልብ የሚስብ አመክንዮ ባይኖረውም ” ደንቆሮ ምሁር” የምትለዋና ” እድሜ ለሚዲያ ሰውየውን ቆልሎ ተራራ አሳከለው” የምትለዋ ሃሳብ የሪፖርት አቅራቢውን ቀለብ ገዛች። ከዛ ውጪ የነበረው ምልልስ ግን ያው የተለመደ ” ሙሌት” የሚባለው ዓይነት ነበር።

መለስ የሞቱ ሳምንት የዚህ ሪፖርት አቅራቢ አንድ አቶ ጊታቸውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው አጋጥሞት ነበር። በወቅቱ ሪፖርት አቅራቢው በድንገት የብሄራዊ ባንክን ፎቶ ሲያነሳ በቅጽበት ከየት እንደመጡ የማያውቃቸው ሲቪል ደህንነቶች እንደወረሩትና ካሜራው ተነጥቆ መሰበሩን ሲያጫውተው፣ ጨዋታውን ጨዋታ አነሳውና ወደ ጌታቸው አሰፋ ሹመትና ችሎታ መጫወት ጀመርን።

የውጭ ደህነት ጉዳይ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት ጌታቸው አሰፋ በአቶ ክንፈ ሞት በጊዚያዊነት የደህንነት ቁንጮ ሆኑ። በዛው ውንበራቸው ተደላድሎ ኢህአዴግ እውስጡ የተነሳው ማእበል እስከበላው ደረስ በቦታቸው ነበሩ። ወደ መቀለ በአዲስ ሙድና ሃላፊነት ለመስራት ሲሄዱም የተለያዩ የምርመራ ውጤቶችና ሃላፊዎች ይፋ እንዳደረጉት የአገር ደህነነት የሚባለውን ተቋሙን ጥርሱንም ድዱንም፣ አገጩንም አወላልቀውት ነበር።

ታዲያ ይህ እሳቸውን በተመሳሳይ ተቋም ውስጥ እየሰራ ያውቃቸው የነበረ ሰው ” ጌታቸው ደንቆሮ ነው። የሚወራለትን ያህል አይደለም። ሚዲያ ነው የሰቀለው። በተለይ ኢሳት ነው መንፈስ ያደረገው” አለ። ነገሩ አዲስና ለማወቅ የሚያጓጓ በመሆኑ ” እንዴት? ማለት…?” በማለት ተናጋሪውን አስቀጠለው። ብዙ የማውራት ፍላጎት እንደሌለውና ጨዋታው የግልና የጓደኛነት መሆኑንን አስታውቆ ብዙ አለ።

” ጌታቸው ማንም የማይክደው ችሎታው ጭካኔ ነው” ሲል ጭካኔውን የሚያሳይ ማብራሪያዎችን አቀረበ። አስከትሎም ” ስለላ ገንዘብ ሲደመር ጭካኔ ነው” ብሎ እንደሚናገርና በተግባርም ይህንኑ እንደሚያደርግ ገለጸ። በሁለቱ መርሁ ከሃላፊነት እስከተነሳበት ድረስ ከፍተኛ ሃብት ያፈስ እንደነነር፣ ማሰሰ ሳይሆን ይረጭ እንደነበር የሚያውቀውን ያህል ዘረዘረ። ማሳረጊያው ” እውቀት የለውም፤ በእውቅት የተደገፈ ስራ በመስራት የሚበልጡት ሌሎች አሉ፤ ምስሉ በፎቶ ስለማይወጣ፣ በሚዲያ ስለማይቀርብ ዝም ብሎ ገነነ” ነበር ያለው።

አቶ ስብሃት ነጋ ከዋሻ ውስጥ በመከላከያ ሃይል እቅፍና ጀርባ ተንተላጥለው መውጣታቸው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ” ሽማግሌ፣ ጡረተኛ ይዞ ፉከራ” በሚል የትህነግ ወዳጆች ሲያታጥሉ የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ስለ ጌታቸው አሰፋ አስቀድሞ የነገረው ሰው ጋር ደወለ።

አውሮፓን ለቆ ወደ ካናዳ ያመራው ይህ ሰው ” ባክህ ተወኝ” ሲል ሳቀ። እጅግ አሽካካ። ” ሰውየው ደንቆሮ ነበር ብዬህ ነበር እኮ” ሲል አስተጋባ። ማብራራት ነበረበትና ሳቁን አቁሞ ” ስብሃት” ሲል ብረዥም ተንፍሶ የሚከተለውን አለ። እንደወረደ

ስብሃት ነጋ ማለት የትህነግ ዊክፒዲያ ማለት ነው። ስብሃት የማያውቃት አንዲት ነገር የለችም። ስለ ህወሃት ከስብሃት በላይ የሚያውቅ አንድም አካል የለም። ሊኖርም አይችልም። እናም ስብሃትን በህይወት ማግኘት ማለት ሁሉንም መረጃ ማወቅ ማለት ነው። ሲያዝ በቲቪ እንደታየው ሽንፈቱን አምኗል። መቀለ እያለም ደስተኛ አልነበረም። “እንዴት እዚህ እንደመጣን አይገባኝም” ብሏል።

ጌታቸው አዋቂና በስለላው መርሃ የበሰለ ተኩላ ሰላይ ቢሆን ስብሃትን ከአጠገቡ አይለየውም ነበር። ስብሃትን ተሸክሞ እስከመጨረሻው መሄድ ወይም ካልሆነ ሌሎች ላይ ተደረገ እንደተባለው ማድረግ ነበረበት። ( ማስወገድ ማለቱ ነው) ምክንያቱም የድርጅቱን ሰነድ የያዘውን ዋና ቁልፍ ሰው አስረክበህ አዋቂ ልትሆን አትችልም። አሁን በስሜት የሚጮኸው ጩኸት ሲረግብ ከስብሃት የተገኘው ሰነድ ይፋ ይሆናል። የዛኔ ስብሃት መያዙ አያስፈነድቅም ለሚሉ ወገኖች ምላሽ ይሆናል።

በግል ስብሃት ተይዞ ሳይ የህወሃት ጉዳይ እንዳለቀ አምኛለሁ። ጉዳዩ ሽምግልና ላይ አይደለም። ጉዳዩ መረጃ ላይ ነው። ስብሃት ከተያዘ በሁዋላ ኦፕሬሽኑ ምን ላይ ደረሰ? ምን ያህል መኮንኖች እጅ ሰጡ? ምን ያህል ተደመሰሱ? የወደፊቱ እቅድና ከትህነግ ጎን የተሰለፈው ሃይል መዋቅር እንዴት ይሆናል? ስብሃት ይህንን ሁሉ ይደብቃል? መኖር ስለሚያጓጓው ራሱን አሳልፎ ለህግ የሰተ ሰው መሆኑንን መዘነጋት አይገባም። የድርጅቱ በውጭ አገር የተቅመጠ ሃብት እንዲመለስ የተጀመረው ዘመቻ ምን ያህል እየተቀላጠፈ ነው? ስብሃት እሱ እስር ቤት ተቀመጦ ” የኔ” ሲለው የነበረው የኤፈርት ሃብት ማንም ሲበላው ዝም ብሎ ያያል?

በርካታ ጉዳዮች በማንሳት አስተያየቱን የሰጠው ዜጋ ሲጨርስ ” ጨካኝ የሚባሉ ሰዎችን መጨረሻ መዘንጋት አይስፈልግም” በማለት ነው። በሌላ ወገን ግን ጌታቸው አሰፋን ዛሬ ድረስ መንፈስ አድርገው የሚመለከቱ አሉ። በተለይም ትህነግን የሚወዱና ከትህነግ ሌላ ፓርቲና ድርጅት ሊኖር ይችላል ብለው የማያስቡ በጌታቸውና በደብረጽዮን ዛሬ ድረስ ያምናሉ። በተለይም የደብረጽዮን ድምጻቸው በድምጸ ወያኔ አማካይነት ከተሰማ በሁዋላ ትግሉ ተመልሶ እንደጎመራ ያመኑ አሉ። ተስፋቸው ለምልሞ የደስታ መግለጫው ዛሬ ድረስ እየጎረፈ ነው።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ ከመከላከያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ” ሩቅ አያስቡም፤ እውቅት የላቸውም፤ሲያስቡ የነበረው ሁሉ ግራ የሚጋባ ነው” ሲሉ እሳቸው ቸምሮ የተሳተፉበትን የህግ ማስከበር ዘመቻ ድል ሚስጢርና የተጨናገፈውን ወጥመድ ይፋ አድርገዋል። የትግራይ ሕዝብን ከልባቸው አመስግነው ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት ጀነራሉ ” መሰረታዊ እሳቤዎችን ሳይቀር የሳቱ” ብለዋቸዋል።

የደብረጽዮን ድምጽ ተሰማ ከተባለ በሁዋላ በፓልቶክ የትህነግ ወዳጆች ውይይት ላይ ” የአብይ መንግስት አንድ እገሩ አፋፍ ላይ ነው። ቶሎ ቶሎ ከኦሮሞና ከሲዳማ ጋር የኮንፌደሪሽን ግንኙነት ማድረግ አለብን፤ እነሱም እኛም ነጻ አገር ሆነን መቀጥል የምንችልበትን ትብብር ማስፋት አለብን” ሲሉ የድል ብስራት ሲያሰሙ ነበር። በዚሁ የፓልቶክ ውይይት ሱዳን ወደፊት እንደምትገፋ፣ሌላም የሚከተል ሃይል እንዳለ፣ ቤኒሻንጉል ላይም ጥያቄ እየተነሳ እንደሆነና የህዳሴውም ግድብ የሱዳን መሬት ላይ እንደተገነባ አንስተዋል። በውይይቱ አንዳንድ አስቀድመው በጭምጭምታ ይሰሙ የነበሩ ጉዳዮች ይፋ የሆኑ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ ለማስጣል የተጀመረው ዘመቻ ውጤት እንደሚያስመዘግብ በሙላት ይነገሩ ነበር። ጌታቸው አሰፋን በማድነቅም አበባ ሲረጭ ታይቷል።

 • በ”ገዳዩ” የትህነግ የትምህርት ፖሊሲ “ትውልድ ላሽቋል”፤ ብርሃኑ ነጋ ታዩ
  በጦርነት እንዳይሆን ሆኖ ከተቀጠቀጠ በሁዋላ ትዕቢቱን በውርደትና ተዘርዝሮ በማይጠቃለል ኪሳራ ዘግቶ የፍርድ ቀኑንን የሚጠብቀው ትህነግ፣ ዛሬ በድጋሚ ድል መደረጉ ይፋ ሆኗል። “ኢትዮጵያ ትህነግን በገሃድ ድል አደረች። ልጆቿንም ከመንጋጋው ነጠቀች” ሲሉ የገለጹ ” ለምን ድንጋይ ወርዋሪና በመንጋ የሚነዳ ትውልድ እንድተፈጠረ አሁን ገባን” ሲሉም ተደምጠዋል። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ውጤት ይፋContinue Reading
 • “የወደቁት ተማሪዎቻችን  ብቻ ሳይሆኑ የወደቅነው እንደሃገር ነው”
  ከ50 በመቶ በታች ያመጣ ማንኛውም ተማሪ ዩንቨርስቲ አይገባም ሲሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ በቀጣይ በቀረበው የመፍትሄ አቅጣጫ የተዳከውሙባቸውን ትምህርቶች በዩንቨርስቲ ዳግም እንዲማሩ ተደርጎ በአመቱ መጨረሻ እንዲፈተኑ በማድርረግ ያለፉት የዩንቨርስቲ ስርዓቱን እንዲቀላቀሉም ይደረጋልም ብለዋል ። ሚኒስትሩ ጨምረው የወደቁት ተማሪዎቻችን  ብቻ ሳይሆኑ የወደቅነው እንደሃገር ነው ያሉ ሲሆን ተማሪዎች በሚገባው ስነ ምግባር ትምህርታቸውን አለመከታተላቸው Continue Reading
 • ዓለም ባንክ 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረ
  የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ745 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ745 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ዑስማን ዳዮኔ ፈርመዋል። በድጋፍ የተገኘው ገንዘብም ለጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና ለጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ተግባር የሚውልContinue Reading
 • “በትግራይ ክልል ከኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ውጭ በግዳጅ ላይ ያለ ሌላ የፀጥታ ሀይል የለም”
  በትግራይ ክልል ከኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ውጭ በግዳጅ ላይ ያለ ሌላ የፀጥታ ሀይል የለም፦ ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ለተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ፤ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ፤ ከቀይ መስቀልና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለተውጣጡ አመራሮች በሰላም ስምምነቱ ትግበራ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ማብራሪያውን የሰጡት የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊContinue Reading

Leave a Reply