ሌ/ጄ አበባውና ባጫ ተገደሉ ያለው፤ ከንግሊዝ የሚደጎመው አሸባሪ ከባልደረቦቹ ጋር ተያዘ

የመከላከያ ሰራዊቱንና የጦር አመራሮችን ስም በማጠልሸት የአገርን አንድነት አደጋ ውስጥ የሚጥል የጥላቻና የሃሰት መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ለመውጣት ሲሞክር ደቡብ ዕዝ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ሌሎች ከአገር ሊወጡ የነበሩና በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ጭምር መያዛቸውን ኦፕሬሽኑን የመሩት ሌ/ኮ ግርማ አየለ አረጋግጠዋል::‘ የጦር ሃይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰን ጨምሮ ፣ ጄኔራል መኮንኖችንና ከፍተኛ የጦር አዛዦች በትግራይ ልዩ ሃይል ተገድለዋል’ የሚልና ሌሎችንም የሀሰት መረጃ “የትግራይ ልዩ ሃይል ድል” በሚል ፍሪደም ቲቪ በተባለ የዩቲዩብ አድራሻ በተለያ ጊዜ ያልተጨበጠ መረጃ ያሰራጭ የነበረው ሃጎስ ሰልጠነ ፍስሃዬ የተባለው ግለሰብ ከአዲስ አበባ በመነሳት ኬንያ ከዛም ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ለመውጣት ሲሞክር ነው ሃዋሳ ላይ በደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር የዋለው::

ስራውን እንዲሰራ የቀጠረው እንግሊዝ አገር የሚኖረው ዳዊት አብርሃ ዘረዝጊ የተባለ ሰው መሆኑንና ለአገልግሎቱም 6 መቶ የአሜሪካን ዶላር ይከፍለው እነደነበር ገለሰቡ ተናግሯል::የሚያሰራጨውን የሃሰት መረጃም እንግሊዝ አገር ሆኖ ዩቲዩቡን ከሚያስተዳድረው ዳዊት አብርሃ እንደሚሰጠውና እሱም በውጭ ካሉ አፍራሽ እንቅስቃሴ ካላቸው ከተለያዩ የቴሌቪዝን ጣቢያዎችና ከግለሰቦች ማህበራዊ ገፅ የሚያገኘውን ያልተጣራ መረጃ አሰሪውን በማስፈቀድ ይጠቀም እንደነበርም በተለይ ለደቡብ ዕዝ ሚዲያ ቡድን ተናግሯል

ይህንን ስራ ከአመት በፊት እንደ ጀመረ የሚናገረው ግለሰቡ፣ መንግስት በትግራይ የህግ ማስከበር ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ያልተጨበጠ የበሬ ወለደ መረጃ ማሰራጨት እንደጀመረና “እየቆየሁ ስሄድም እየሰራሁት ያለው ወንጀል የደህንነት ስጋት ላይ ስለጣለኝ፣ ከአገር ለመውጣት ስንቀሳቀስ ነው በመከላከያ በቁጥጥር ስር የዋልኩት” ሲል ገልፀጿል::

ደቡብ ዕዝ የሃሰት መረጃ አሰራጭውን ሃጎስ ሰልጠነን ጨምሮ ከአገር ሊወጡ የነበሩ 8 ሰዎችን እና 4 በህገ ወጥ ዝውውሩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸውን ለፌዴራል ፖሊስ ማስረከቡን ሌ/ኮ ግርማ አረጋግጠዋል ፡፡ ህገ ወጦችን በመያዙ ሂደት የደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት የነበራቸው ተሳትፎ የሚደነቅ ነበር ሲሉም ተናግረዋል:: አየሰው ድልነሳ ፎቶግራፍ መልካሙ ሁነኛው

See also  ትህነግ በ"ዝርፊያ ፖለቲካ" ችጋር እያመረተ ነው

Leave a Reply