በአንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት መጓደል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

አንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሕግ ውጭ በመንቀሳቀስ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደሩ መሆኑ ተመለከተ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትምህርት ጥራት ላይ ተወያይተዋል።  

ተቋማቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ራሳቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ፣ የጥናትና ምርምር ስራዎችንስ በምን መልኩ መስራት ይኖርባቸዋል የሚሉትና ሌሎችም በውይይቱ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።  

በውይይቱ እንደተመላከተው ተቋማቱ ባለፉት ዓመታት በቁጥር ደረጃ ቢጨምሩም፤ ጥራትና አግባብነት ላይ ውስንነት ይታይባቸዋል። ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት አጀንሲ የተገኘው መረጃ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 278 መድረሱን ያሳያል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ እንደተናገሩት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው ትምህርት የጥራት መጓደል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።   “አንዳንድ ተቋማት ከ10ኛ ክፍል ላቋረጡ ተማሪዎች ዲግሪ ይሰጣሉ፤ ማንበብና ማጻፍ የማይችሉ ሰዎችም እንዲሁ ወረቀት እየወሰዱ ነው” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። 

መቁረጫ ነጥብ ሳያሟሉ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ መኖራቸው መረጋገጡን ያነሱት ዶክተር አንዱዓለም እውቅና ሳይሰጣቸው እንደሚያስተምሩና ከተፈቀደው ተማሪ ቁጥር በላይ እንደሚመዘግቡም ተናግረዋል። ችግሮች እርምጃ በመውሰድ ብቻ ስለማይፈቱ ተቀራርቦ በመስራትና በመደጋገፍ ለማስተካከል መስራት ይገባል ብለዋል።

ዶክተር አንዱዓለም ተቋማቱ ከሕገወጥ እንቅስቃሴ ተቆጥበው ወደ ትክክለኛው መስመር መግባት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። ከዚህ በኋላ እውቅና የሚሰጣቸው ተቋማት ተመዝነው የጥራት መስፈርት የሚያሟሉበት ስርዓት እንደሚዘረጋ አስታውቀዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ተቋማቱ የትምህርት ጥራት ችግር ተብለው ከተለዩት መካከል መምህራንን በጥራት በማቅረብ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። መንግስትና የግሉ ዘርፍ በመቀናጀት ችግሮችን ለማቃለል ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ሚኒስቴሩ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ በፖሊሲና ስትራቴጂዎች እንደሚያግዛቸውም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ሞላ ጸጋዬም ተቋማቱ ጥራታቸውን እንዲያሻሽሉ ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰጠው ድጋፍ ይጠናከር ብለዋል።

በተለይም የመምህራን ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ይደረግልን ሲሉ የጠየቁት ፕሬዚዳንቱ ተቋማቱም ራሳቸውን ለማብቃት ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

 • በትግራይ ያሉ የዪኒቨርሲ ተማሪዎች ወደ ሰመራ እየገቡ ነው
  በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች አፋር ክልል ሰመራ ከተማ መግባት መጀመራቸው አል ዐይን አማርኛ ያነጋገራቸው የሰመራ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡የተማሪዎች ወላጆች ከሰሞኑ ልጆቻቸው ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመለሱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል መውጣት ከጀመረ እና የተናጠል ተኩስ አቁም ከታወጀ በኋላ ትግራይ ክልል ባሉ ዮኒቨርሲቲዎች ልጆች ያሏቸውንContinue Reading
 • “አደንዛዥ ዕጽ የሚሰጧቸው በበርሜል ሻይ አፍልተው ነው”
  አሸባሪው ትህነግ (የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ዜጎችን ወደ ውትድርና ተመልምለው ለውጊያ የሚያደርሰው በሁለት መንገድ ነው፤ አንዱ ምንም የጦር ዕውቀትና ልምምድ ሳይኖራቸው በግድ ከሽፍታው ቡድን ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አደንዛዠ ዕፅ አፍልተው ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ትህነግ ህጻናት ልጆችን ለጦርነት እየመለመለ እንደሚሰማራ በማስረጃ ተረጋግጦበታል።Continue Reading
 • 47 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቀሌ ነገ እንደሚጓዙ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
  ለትግራይ ክልል የሚውል ሰባዓዊ ድጋፍ የጫኑ 47 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቀሌ ነገ እንደሚጓዙ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በተለይ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ በዓለም ምግብ ፕሮግራምና ሌሎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የእርዳታ አቅርቦቶች በተገቢውContinue Reading
 • በእርግዝና ወቅት የማይመከሩ ምግቦች
  1. ጥሬ ወይም በከፊል የበሰለ እንቁላል እርጉዝ ሴቶች በፍጽም ጥሬ ወይም በከፊል የበሰለ እንቁላል መመገብ የለባቸውም። ጥሬ እንቁላል ለሳልሞኔላ ኢንፌክሽን አይነተኛ መነሻ ሲሆን፤ ኢንፌክሽኑ ማስመለስና ተቅማጥ ያስከትላል። ይህም የልጅዎን ጤንነት ይጐዳል። እንቁላል የፕሮቲን፣ ቫይታሚንና ሚኔራሎች ጥሩ መገኛ ነው። ስለዚህ እንቁላል ሲመገቡ በሚገባ መብሰሉን ያረጋግጡ። 2. አልኮል መጠጦች እርጉዝ ሴቶች በሚያስከትለውContinue Reading

Leave a Reply