እነዚህ አካላት ( ስማቸው የተነሳው ኦነግና አብን) ማለታቸው ነው ምን ሲሰሩና ምን ሲሉ እንደነበር ምርጫ ቦርድ መለስ ብሎ መጠየቅና መመርመር እንደነበረበት የኦሮሚያ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ያሳሰቡት። እንደ ተቋም ፓርቲያቸውም ሆነ እርሳቸው በግል ምርጫ ቦርድን እንደሚያከብሩ፣ ከዛም በላይ አገሪቱ ገለልተኛ ተቋም እንዲኖራት ፍላጎት እንዳላቸው የጠቆሙት አቶ ፈቃዱ ቦርዱ በሰጠው ውሳኔ ቅር መሰኘታቸውን አልሸሸጉም። ህዝብ ስማቸው ተነሳ የተባሉትን የድርጅቶቹን የጀርባ ማንነት እንደሚያውቅም ጠቁመዋል።

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች ላይ “በህጋዊነት ተመዝግበን እያለን ስማችን ጠፍቷል፣ ከጁንታው እኩል ተፈርጀናል” በሚል ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገቡት ቅሬታ መሰረት ምርጫ ቦርድ አንቀጽ ጠቅሶ ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም።

በምላሹም ” ለወደፊትም በተመሳሳይ በምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር ህግ 1162/2011 እና ተያያዥ መመሪያዎች መሰረት የፓርቲዎች የቅስቀሳ የንግግር እና ሌሎች ለህዝብ የሚያሰራጯቸውን መልእክቶች ላይ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እስከእጩ መሰረዝ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ያሳውቃል” ነበር ያለው።

ይህንኑ ተንተርሶ ምላሽ የሰጡት አቶ ፈቃዱ “ስማችን ተነሳ” ያሉት ሕዝቡ ማንነታቸውን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ተንጋረዋል። በመግለጫቸው የክልሉ ህዝብ በራሱ ተነሳሽነት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለብልጽግና ፖርቲ ያለውን ድጋፍና ክብር ማሳየቱን አመልክተዋል። “ህዝብ የተሰማውን ስሜት ለመግለጽ ለምን በዚህ ደረጃ ፈንቅሎ ወጣ? የሚለውን ግምት ውስጥ ማስገባት አግባብ እንደሆነ አቶ ፈቃዱ ጠቁመዋል።

“ትችቱን ያነሱ ወንድሞቻችንም በእኛ በኩል ምን ጉድለት አለ? ብለው ራሳቸውን ማየት ያስፈልጋቸዋል” ያሉት አቶ ፈቃዱ “ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ቀስቅሶ የጠራው ሰልፍ እንደመሆኑ የሰልፉን ትርጉም ማክበር መቅደም ነበረበት” ሲሉ አስገንዝበዋል። ምርጫ ቦርድም ሰልፉ ላይ ተነሱ የተባሉትን ጉዳዮች አንስቶ መወቀስ ባቻ ሳይሆን እነዚህ አካላትስ በተለያየ ጊዜ ምን ሲያደርጉ እንደነበር መለስ ብሎ ለመረመር የገባው እንደነበር አቶ ፈቃዱ አስታውሰዋል።

“ህዝብን እንደህዝብ የሚያንኳስሱ፣ የሚያጋጩ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ፣ የጁንታው ተላላኪ በመሆን የሚሰሩ አካላት ህዝቡም ያውቃል እነርሱም ያውቃሉ ብለን እንገምታለን ተጨባጭ ማሳያዎችም አሉ” ሲሉ አቶ ፈቃዱ ተናግረዋል፤ አክለውም “ምርጫ ቦርድንና ህጉን ከማንም በላይ እናከብራለን፤ኢትዮጵያ ጠንካራ ገለልተኛ ተቋም እንዲኖራት ከማንም በላይ እንፈልጋለን” በማለት የድርጅታቸውን አቋም አንጸባርቀዋል።

ሲያጠናክሩም ” ለእዚህም እንሰራለን፣ እንታገላለን፣ እንረባረባለን” ብለው ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰሞኑን ሰልፉ ላይ በምርጫ ቦርድ በህጋዊነት ተመዝግበን እያለን ስማችን ጠፍቷል፣ ከጁንታው እኩል ተፈርጀናል የሚል ቅሬታ ማሰማታቸውና የምርጫ ቦርድ ጉዳዩን አስመልክቶ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ጁንታዉን ለማስወገድ የክልሉ ሕዝብ ሲያደርግ የነበረዉ ተሳትፎም በታሪክ ዉስጥ የማይረሳ ድንቅ ተግባር ነዉ ብለዋል።

ጽንፈኝነት የለዉጡ ዋና እንቅፋት ነዉ ያሉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በመላዉ የክልሉ ሕዝብና የሃገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ትግል የመጣዉ ለዉጥ በጽንፈኞች ምክንያት አይደናቀፍም ብለዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ አቃፊ ነዉ: እዉነተኛ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ለመገንባት እየታገለ ነዉ ያሉት ሐላፊዉ መላዉ የሐገሪቱ ሕዝብ የፌደራሊዝም ስርዓት ተግዳሮት የሆነዉን ጽንፈኝነትን ሊታገል ይገባል ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ላይ ሲካሔዱ የነበሩትን የድጋፍ ሰልፎች ለማጠልሸት ሲሰሙ የነበሩት ጥቃቅን ድምጾች የሕዝብን ክብርና ድጋፍ ካለማወቅና ካለመረዳት የተሰጡ ድምሶች ስለሆኑ በሕዝብ ዘንድ ቦታ የላቸዉም ብለዋል።

” ብርሃኑ ነጋንና አብይን ሱሪ ያስታጠቅን እኛ ነን” በሚል ዘር ላይ ያተኮረ ሰልፍ ባህር ዳር ሲደረግ አብንም ያለው ነገር የለም። ኦነግም ቢሆን ሰዎች በብሄራቸው ምክንያት ሲፈናቀሉና ጉዳት ሲደርስባቸው ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ሲነቅሳቀስ አልታየም። አብን በአቶ በረከት አማካይነት የአማራ ክልል እየገዛ ያለውን አዴፓን እንዲተካ በህወሃት ፈቃድ የተደራጀ ድርጅት እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚገለጽ፣ ከእነ ዶክተር አምባቸው ህይወት ጋር ስሙ የሚነሳ ድርጅት መሆኑ በስፋት ይነሳል።

    Leave a Reply