ቤኒሻንጉል- 34 ሺህ የሸፈቱ ጉምዞች ወደ መኖሪያቸው ተመለሱ፤ 151 ቀበሌውች አዲስ አመራር ሰየሙ፤ 50 ሽፍታው የያዛቸው ቀበሌዎች ተመለሱ …

ግብረ ሃይሉ በመተከል ዞን ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ማምጣት የሚያስችል ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ሲናገር ከዚህ በፊት ተደብቆ የነበሩ የአሃዝ መረጃዎችን በማጣቀስ ነው። አሃዞቹ እንደሚያሳዩት 151 ቀበሌውች አዲስ አመራር ሰይመዋል። 32 ቀበሌዎች ይቀራሉ። 50 ሽፍታው ይዟቸው የነበሩ ቀበሌዎች በግብረሃይሉ አማካይነት መንግስት ተቆጣጥሯቸዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሰ ድርጅት ይፋ ያደረገው ከታች ያለው ዜና እንደሚያሳየው ክልሉ መንግስት እጅ ነበር ማለት አይቻልም። ለዚህ ይመስላላ 10 ሺህ ሚሊሻዎች እንዲሰለጥኑ እየተደረገ ነው። ሙሉ ዜናውን ከስር ያንብቡ

(ኢ ፕ ድ ) የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሀይል የፀጥታና ህግ ማስከበር ስራውን ከተረከበ በኋላ በዞኑ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ማምጣት የሚያስችል ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ተገለጸ፡፡ግብረ ሃይሉ ቀሪ ሽፍታውን የማፅዳት ስራ ለማከናወንና ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የ15 ቀናት ዕቅድ አስቀምጧል፡፡

በመተከል በለስ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ከወረዳ እስከ ዞን ያሉ የግብረ ሃይሉ አመራሮችና አባላት ግምገማ ተጠናቋል፡፡ሽፍታው ከሚንቀሳቀስባቸው 32 ቀበሌዎች ውጭ በሚገኙ 151 ቀበሌዎች የመንግሥት መዋቅር በአዲስ መልክ እንዲደራጅ መደረጉ ተገልጿል፡፡በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ግብረ ሃይሉ መተከልን ከተረከበ በኋላ ከህዝቡ ጋር ባካሄደው ውይይት ሽፍታው የማንንም ብሄር እንደማይወክል መግባባት ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

ግብረ ኃይሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ያደረገው ውይይትና ተጨማሪ ስራዎች ውጤት በማስመዝገባቸው ጫካ ገብተው የነበሩ 34 ሺህ የጉምዝ ማኅበረሰቦችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡ታስበው የነበሩ ግጭቶችም ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገው ወይይት መክሸፋቸውን ነው አቶ ተስፋዬ የተናገሩት፡፡በዚህም ሽፍታውን ከህበረተሰቡ በመነጠል በጋራ በተወሰደው እርምጃ በሽፍታው ስር የነበሩ 50 ቀበሌዎችን ወደ ሠላም ቀጣና መመለስ ተችሏል ብለዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የመተከል ጉዳይ የህዝብ ለህዝብ ግጭት ሳይሆን ፖለቲከኞች ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ የፈጠሩት ሽኩቻ ነው ብለዋል፡፡በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ በተለይ በዞንና በክልል ደረጃ ያሉ የስራ ሃላፊዎች ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡የግብረ ሃይሉ መሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ከቀበሌ እሰከ ዞን ያለውን አደረጃጀት ለውጥ ማምጣት በሚችል መንገድ ማደራጀት ጀምረናል ብለዋል።

“ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሲመለሱ አስተማማኝ ሠላም እንዲሰፍን የአካባቢውን ህዝብ የሚመስል የሚሊሻ አደረጃጀት ተፈጥሯል፤ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ የሚሊሻ አባላትም ከዛሬ ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ይወስዳሉ” ብለዋል፡፡ሽፍታው የሚንቀሳቀስባቸውና የጸጥታ ስጋት ያለባቸው 32 ቀበሌዎች በሚቀጥሉት 15 ቀናት ሙሉ በሙሉ ከሽፍታው እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆኑ አመራሩ ታች ድረስ ወርዶ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ከመመለሳቸው በፊት የአካባቢው ሠላም አስተማማኝ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡ተፈናቃዮች በሚቋቋሙበት ጊዜ የሚፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት አስቀድሞ ትክክለኛ ቁጥራቸውን መለየት እንደሚገባ ገልጸው፤ለዚህ ደግሞ የሠላም ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ጋር ይሰራል ብለዋል። በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌም ተፈናቃዮችን ለመመለስ ማወያየት፣ የዕርቀ ሠላም ስራና ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች እንደሚሟሉና ያ ሳይሆን የመመለሱ ስራ እንደማይሰራ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply