የተከበበው የትህነግ ሃይል ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፤ ማንነት የመለየት ስራ እየተሰራ ነው

ኢትዮ 12 – በቅርቡ አስራ ስምንት የከዱ ከፍተኛ የመከላከያ ባለ ኮከብና ዘንባባ ምልክት መኮንኖች በአሳሳ ካሉበት ታድነውና በአሰሳ መያዛቸው ይፋ ሲደረግ ቀሪዎቹ በቅርብ ርቀት መከበባቸው መገለጹ ይታወሳል። በዚህ ቀሪዎቹን ከተቻለ በሰላም እጅ እንዲሰጡ፣ ካልሆነም እርምጃ እንዲወሰድባቸው አቅዶ ሲካሄድ የሰነበተው ዘመቻ ታላቅ ድል ማስመዘገቡ ተሰማ። የትህነግ ደጋፊዎችና “ሚዛን የማይጠብቅ ሪፖርት ያቀርባሉ” ሚዲያዎች ትግራይ ወደ ሙሉ ጦርነት እየተቀየረች እንደሆነ እየዘገቡ ነው።

” የህግ ማስከበር ዘመቻ ” የሚል ስያሜ ያለው የመንግስት ዘመቻ በድል መጠናቀቁ ይፋ ከሆነ በሁዋላ የተበታተነውን አመራርና የአመራሩ ጥበቃ የሆነውን ሃይል ለማጽዳት እየተካሄደ ባለው ዘመቻ ዛሬ አፍጋህጋህ በተባለው ተራራማ አካባቢና በራያ መሽጎ የነበረው የትህነግ ሃይል ላይ ሙሉ ድል መመዘገቡን ለማስታወቅ ቅድሚያ የሆነው ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋ ማሪያም ነው።

ከሽሬ ወደ አክሱም በሚወስደው መንገድ በምትገኘው አፍጋህጋህ በተባለች ተራራማ ስፍራ ከተደበቁ የጁንታው ሃይሎች ጋር ትላንት የተጀመረው ውጊያ ዛሬ በመከላከያ ሰራዊታችን በድል መጠናቀቁ ታውቋል፣ በተመሳሳይ በዛሬው እለት በራያ መሽጎ የነበረው ጁንታ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ከታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ ይጠቁማል ” ሲል አርአያ አመልክቷል።

በሁለቱም ቦታ የጁንታው አመራሮች መደምሰሱን በተደጋጋሚ ከታማኝ ወታደራዊ የመረጃ ምንጮች ዜና የሚሰማው አርአያ ካጠቆመ በሁዋላ፣ የአገር መከላከያ ዘመቻውን በድል አጠናቆ በዝመቻው ህይወታቸው ያለፈውን ማንነታቸውን የመለየትና ማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

ሰሞኑንን የቀድሞ የትግራይ ክልል መሪ የነበሩት ዶክተር ደብረጽዮን ተናገሩት ተብሎ የተሰራጨው የድምጽ መልዕክት ” ጦርነቱ ይቀጥላል፤ ቀዬያችንን ጥለን ወደየትም አንሄደም፤ ሁላችሁም ተነሱ” ሲሉ ጥሪ አቅርበው ነበር።

እሳቸውን ብቻ ሳይሆኑ በተለያዩ አውዶች ትግራይ የገባው የመከላከያ ሰራዊት እንደሚደመሰስና የተረፈውም ክልሉን ጥሎ እንደሚወጣ እየተገለጸ ነው። በሌላ በኩል መንግስትና አምነስቲ 2.3 ተረጂዎች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚፈልጉ ሲገልጹ ሌሎች የተረጂዎችን ቁጥር ወደ 4.5 ሚሊዮን በማሳደግ ቀውሱን አግዝፈው የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት እንዲያስገባ ጫና ለማድረግ የሚሰሩ አሉ። ይህ በውጭ አገር ታዋቂ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ጭምር በመናበብ እየተካሄደ የሚነገርለት ዘመቻ በታሰበው መንገድ ውጤት ባያመጣም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ውሸትን ታገሉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የቲውተር ገጽን አጥለቅልቀዋል። ይህ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ሃሰትን የማምከን ስራ እየተሰራ መሆኑንን ለመረዳት ተችሏል።

መንግስትም በአምባሳደሮቹ፣ በመሪዎች ደረጃና በወዳጅ አገሮች አማካይነት ሰፊ የዲፕሎማሲ ስር በመስራቱ በጸጥታው ምክር ቤት ሊወሰን ታስቦ የነበረው ጫና እንዳልተሳካ ለማወቅ ተችሏል። የእርዳታ ማቅረቡ፣ ተጎጂዎችን በመለየት የማገዙ፣ የተፈናቀሉ ወደ ቀዬያቸው እንዲመለሱ ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን የተቋረጡ መሰረተ ልማቶችን የመጠገኑ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው መንግስት እየገለጸ ነው። በተዛማጅ ቀሪዎን ያልተደመሰሰ ሃይል የማሳደዱና ከቦ የመያዙ ዘመቻ ያለ አፍታ እየተከናወነ መሆኑንንም መንግስት በየጊዜው ሲገልጽ ሰንብቷል።

መንግስት ለጊዜው ይፋ ባያደርገውም በዛሬው እለት በሽሬና በራያ የተደበቀው ሃይል መደምሰሱን ሌላ ታማኝ የመረጃ ሰው አረጋግጠዋል። ኢትዮ 12

  • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
    የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
  • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
    “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
  • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
    አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading

Leave a Reply