ፈንቅሎች ሲባል አንድ ሰሞን ጮኸው፣ የቢራ ጠርሙስና ፒዛ እየዋጡ በየኮሪዶሩ የሚጋደሙት አይደሉም። የኖርዌይ ፈንቅሎች በዲጂታል ዓለም የሚኖሩ አናሎጎች ናቸው። እንደ ዶቅዶቄ በሄዱበት የሚጮሁ ጸረ ሰላም ሃይሎች ናቸው። ጸረ ሰላም … የኖርዌይ ፈንቅሎች ምርኮ ፈላጊ፣ ማርከው ግን የማያስሩ ናቸው። የኖርዌይ ፈንቅሎች ቤተክርስቲያን የሚስሙ፣ አምላካችን የሚሉትን የሚጠሩ እንደ ኤሊ ልጆች ዓይነት ናቸው። ታሪካቸው አንገት ይቀነጥሳል!! አይጣል!!

ያንን መልከ መልካም ሽበቶ ባርኩት። ድግነቱን እሱ ራሱ የሚያውቀው አይመስልም። የሰው ማኛ፤ የሰው ሰብራዳ … ኖርዌይ ሰላምሽ የበዛ ባይሆን ምን ይኮን ነበር? አንቺ ላይ ሆነን፣ በልመና ነግሰን፣ ብር እያዋጣን አፈናቃይ እንቀልባለን። በቸርች አመስግነን ” በጫካ ላሉ አምስት አምስት ” ብለን ለድጋሚው አስራት ሙዳይ እናዞራለን። ያበደው ብዙ ጉዳዮች ፈሰሱበት። የቱን አንስቶ የቱን እንደሚጥል ጨንቆት ተንጠራወዘ። የኖርዊውይ “ፈንቅሎች” ትዝ አሉት። ፈንቅሎች አበባ በጉንዳን ጠቅልለው ይሰጡሃል። አስቀምጠውት ሲወጡ ጉንዳኑ ይወርሃል። ስለ ራስህ ስትል ልብህን ከፍተህ ሰማ!! ስሚ!! እንደምን ከረማቹህ? ያበደው ከኮሮናም ከፈንቅሎችም ተለይቶ ኳራንቲ ከገባ ቆይቷል። ሁለቱም ይሳላሉ እንጂ አይደርሱበትም፤ ቃፊሮች !!

የፈንቅል ዘመቻ አስቀድሞ የት እንደተጀመረ ያበደው መረጃ የለውም።በየአገሩ መልኩን የቀያየረ የፈንቅል ዓይነት ተግባራት ቢኖሩም ቀደምት ከሚይዙት አገሮች መካከል ኖርዌይ አንዷ እንደምትሆን ግን ያበደው አይጠራጠርም። ቢያንስ በትጋታቸውና በሚያስመዘግቡት ውጤ ግንባር ቀደም ናቸው። ፈንቅሎች አራት ወይም አምስት እንጂ ከዛ በላይ ሆነው አይደራጁም። የፈንቅል አባል ለመሆን ሴት መሆን ግድ ነው። ሴት መሆን ብቻ ሳይሆን ” ፈት ሴት” መሆን የግዳጅ ግዳጅ ነው። የፈንቅል ዓላማ ምርኮ ማብዛት ነው። ከ

ፈንቅሎች ምርኮን ያበዛሉ እንጂ በህገ ደንባቸው ምርኮን አባል አድርጎ ማቆየትን የሚባል ነገር አላካተቱም። ምርኮ አብዝቶ በምርኮ መዝናናት እንጂ ምርኮ አብዝቶ መቆዘም አይመቻቸውም። ምርኮ አባል ከሆነ ነገር ይንዛዛል ብለው ስለሚያምኑ ቁጥራቸውን አያበዙም። በየትኛውም ቦታ እነሱ ባሉበት አያስወሩም። አያውቁም ግን አዋቂዎች ናቸው። አንድ ህግ አይጠቅሱም ይመክራሉ። ጥራሳቸውን በነቀሉበት አገር የሚናገሩት ኖሽክ ” ፈገግታ ነው” ሲጠየቁ የተቀባቡት ምናምኑ ፊታቸው ላይ ቅርፊት ሆኖ ይቆማል። ያበደው ሳቀ። ተገረመና ” ወይ አፈጣጠር” ሲል በልቡናው ገላመጣቸው። አግዳሚ ወንበር ላይ መደርደር … ከልብ ሲታሰብ እንኳና ሰሜን ዋልታ ቡታጅራ ችለው የሚሄዱ አይመስሉም!!

በየቦታው አደረጃጀት ቢኖራቸውም ያበደው የሚያውቃቸው ፈንቅሎች ሰላምታቸው፣ ፈገታቸው፣ ትህትናቸው፣ ሲሽቆጠቆጡ አያድርስ ነው። አዲስ የመጣ የከተማቸውን ነዋሪ አድኖ መያዝ ግንባር ቀደም ተግራቸው ነው። በቀጣይ ከፈንቅል ሂሳብ የሚወራረድ አበባ ይዘው ይመጡና የሚተዋወቁትን ሰው ቤት፣ ማንነት፣ ኑሮ፣ እቃ፣ አልጋ፣ ግብር መክፈያ ቤት፣ አበላል፣ አወራር … ያጠናሉ። ይቀርጻሉ። ይመርዣሉ … ጨዋታቸው ካዛንቺዝ፣ አራት ኪሎ፣ ፒያዛ… እያለ ሲወርድ በትዝታ አሽቅንጥረው የፈለጉበት ቦታ መወረውረ እስኪችሉ … ሲናበቡ …. እየተቀባበሉ ” እንትንዬ” እየተባባሉ ሲስቁ ያስቀናሉ። ቅንንቅናሞች!! አመዳሞች።

ይህን ባደረጉ በሶስትና ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ምርኮ ያገኛሉ። አንድ ፈት አባል መልምለው እቤታቸው ወለል ላይ ያንከባልላሉ። ምርኮ ይዘው ይሰባሰቡና አረቄ እየተጋቱ ያሽካካሉ። የፈንቅል ዘመቻቸውን በድል እየገመገሙ በስኬቱ ደስታ እያጣጣሙ ይጨልጣሉ። ኮረኮንቾች።

ቀልብ ያለው ነዋሪ ስለሚፈራቸው አዲስ ማጥመድ፣ አጥምዶ ማፈናቀል፣ አፈናቅሎ መደሰት፣ ያፈላቅሏትን ካረከሱ በሁዋላ ማባረር … ምን የሚሉት እርካታ ይሆን? ያበደው ሳላቸው። ነገር ፊታቸውን የፈረስ ገጽ ያስመሰላቸው አሉ። ተንኮል ቆሮቆር ሆኖ ያቆሳሰላቸው አሉ። ክፋት ከላይ ወዳች ወርውሮ መሳቂያ ያረጋቸውም አይታጡም። አምኖ አብሯቸው የሚተኛ ስለማያገኙ አንሶላ የሚጋፈፍ ፍለጋ ይኳትናሉ። በብዙ ያባክናሉ… መሰሪዎች … ሴረኞች… ድሮን ቢኖር …

ያበደው እንዲህ ያሉትን ሲያስብ ቀስ እያለ አንጎሉ ይነድበታል። ምራቁ ይለደልዳል። የዚህን ጊዜ መትፋት አለበት። እየቆጠረ በሰልፍ ይተፋባቸዋል። “ልጅ ብቻውን እንዲያድግ የሚፈርዱ እርጉሞች” ሲል ከጥልቁ መናፍስት አለቃ ሽንት እንደተሰሩ አድርጎ ያስባቸዋል። ቀንና ወር ቆጥረው ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ” የጨዋ ዓምድ ያድርጋችሁ” ይላቸዋል ።

አንዴ እንዲህ ሆነ። ያበደው ስልክ ደረሰው። አቤት ብሎ ሰማ። ሲሰማ በሳቅ ያለቅስ ነበር። ሳቁን የውስጥ ጉንጩን ነክሶ ቻለው። እናም አድምጦ ተሰናበተ። ደዋዩ አዲስ ሆኖ ፈንቅሎች እሚኖሩበት ከተማ ተመደበ። ሚሽቱና እሱ መካከል እንኳን ጸብ ኮሽታ የለም ነበር። ጨዋታው በነበረ ነው። አንድ ቀን ፈንቅሎች መጡ። አጠያየቅው ጎበኙት። አስከትለው አበባና እንጀራ ይዘውለት መጡ። ወደዳቸው። በስማቸው መማል ጀመረ።

ከሶስት ሳምንት በሁዋላ ሚሽቱ ያለወትሮዋ ማምሸት ጀመረች። እኩለ ለሊት መጣች። ነገሩ ግራ ገብቶት ለመጠየቅ እድል ሳያገኝ እንደወጣች ቀረች። ፈንቅሎች ምርኮ አገኙ። ሚስቱ ተማረከች። ሚሽቱ እንደ ስብሃት ነጋ ሳትታዘል ወዳ ሄዳ እጅ ሰጠች። ፖሊስ ጠራው ግድያ፣ ድብደባና ዛቻ አድርገህባታል ተባለ። ከቤት እንዳትወጣ … መካሪዎቹ ሰው ከጊዜም በሁዋላ ስህተቱን አይቶ እንዳይታረቅ የሚዘሩት ቂም አሰገኛ ነው… ዓለም ላይ ያሉ ክፉ ስራዎች በዝርዝር ተነበቡለት። ምን እንደመለሰ አያስታውስም። አንድዬ ረዳውና በነጻ ተሰናበተ።

ያበደው ሰምቶ ሲጨርስ ነጯ ቦሰና የምትለው ትዝ አለውና ተረጋጋ። ነጯ ቦሰና ክፉን ነገር ወደ መልካም አጋታሚ ስለመቀየር በስፋት ስልጠና ሰጥታዋለች። ስልጠናው ውብ ነው። ያበደው በዚህ ስልጠና ስለተጠቀመ ላልሰሙ ያሰማል።

ፈንቅሎች ከወያኔዎች ጠላት ጋር ሳይሆን ከራሱ ከወያኔ ጋር ይመሳሰላሉ። የሚግባቡት ምርኮ ለማግኘት በፈንቅል ዘመቻ ላይ ሲሆኑ ብቻ ነው። ለፈንቅል ዘመቻቸው እንቅፋት ካጋጠማቸው አዘውትረው አብረው ያድራሉ፤ አብረው ይውላሉ፤ አብረው ይተኛሉ። ዘመቻቸውን ሲጨርሱ ግን አይፈላለጉም። በግል ግን አደናቸውና አዲስ ቤተሰብ ማባረራቸውን አያቆሙም።

ያበደው በግል ህይወታቸው ያስጠጓቸውን ሰዎች ሳይቀር የሰበሩ የፈንቅል አባላት እንዳሉ ሰምቷል። የአደረጃጀታቸው ስም ባይታወቅም አንሶላ ለመጋፈፍ ሲሉ ልጆችን የሚበትኑ ልበ ድፍን ወንዶች አሉ። ያበደው በጓደኛው ክህደት የተፈጸመበትን ሰው ኦስሎ ቴቫን ላይ ወዳጆች አሳይተውታል። ሌሎችም አሉ።

እናንት ምንም በማያውቁ ልጆች ላይ የምትፈርዱ፣ እናንት በሰው ቤት ውስጥ ጉንዳናቸሁን የምትነሰነሱ ኮብራዎች፣ እናንተ እንደ ከብት የምትነዱና ቤታችሁን የማታፈርሱ ጥንዶች… ያበደው ዘርዘረ … እናንተ የወንድማችሁን፣ የእህታችሁን ቤት አልጋ በመናፈቅ ልጆች ላይ የምትፈርዱ ልበ ደንዳኖች … ያበደው እየተንቆራጠጠ የሚያውቃቸውን ከንቱዎች ባይነ ህሊናው እየሳለ አስጠነቀቃቸው።

ምራቁን ዋጥ አድርጎ ” ብዙ ጉድ አለ” የፈንቅሎቹ ጥቂት እጅግ ትንሽ ናት። የተሳትፎ ደብዳቤ ነጋዴዎች፣ ሴት እህቶቻችንን እንደ መስዋዕት ስትቀበሉ የነበራችሁ ኬዝ ሰሪዎች፣ በጠባብ ቤት ውስጥ … ያበደው የሰማውን እያሰላሰለ ራሱን ያዘ። ሰው እምድር ጫፍም ሆኖ አይተዛዘንም… ልቡ ከመሸቀልና ከመሻፈድ አያርፍም… ነብሳቸውን ይማረውና የኔታ ” ከሽፈናል” ያሉት ወደው አይደለም። “ሰለሞን ለሁሉም ጊዜ አለው ” ብሏል። ተሸፋፍነው ቢተኙ ገላልጦ የሚያይ አለ። የማይገለጥ ምን አለ? ሁሉም በጊዜው ይተረዛል። አይ ኖርዌይ በዴሞክራሲ ውስጥ የጨለመ አስተሳሰብ የነገሰብሽ መሆኑንን ማን ይነገርሽ? ማን ጀግና የምትጠየፊውን ጉድ ዘረጋግፎ ያውራሽ? ያበደው … ቦሰና ጋር ነው። ቦሰና ለሁሉም መልስ አላት። ልምዷ ብቻ ሳይሆን አስተዳደጓ ነገሮችን ወለል አድርጎ ያሳያታል። ምናልባት እሷ ለኖርዌይ በአንድ ሞቃት ምሽት ከርሷ ውስጥ ያለውን የጨለማ አሰራር ትተርከው ይሆናል። ማን ያውቃልልልልልልልልልል?

ነጮ ቦሰና ባትኖር፣ ኤርትራ ባትኖር ምን ይኮን ነበር። አሁን ጊዜው የቦሰና ነው። ቦሰና አንድ ነገር በአንድ ጊዜ ነች። አሁን እረፍት ያስፈልጋል። መቀላቀል አይቻልም። ስለም ሰለም ሻሎም!! ቤት ያላቹህ ግቡ!! የራሳቹህ ቤት ግትቡ። ሸበቶው ወዳጄ ጸጋውን ያብዛልህ!! ስለንተ ብዬ አሜን!!

    Leave a Reply