“የጸጥታ አባላት ከህወሓት የዓመታት የሀሰት ትርክት ወጥተው ህዝቡን በእኩልነት ማገልገል አለባቸው” አሻድሊ ሀሰን

የልዩ ሃይልና የመደበኛ ፖሊስ አባላት ህወሓት ለዓመታት ከዘራባቸው የሀሰት ትርክት ወጥተው ህዝቡን በእኩልነት ማገልገል እንዳለባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተቋቋመው የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሃይል የጸጥታና ህግ ማስከበር ሥራውን ከተረከበ በኋላ በመንግስት መዋቅር ስር ያለውን ጉድለት እየፈተሸ የማስተካከል ሥራ እየሰራ ይገኛል።

በዚህም ለዓመታት ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች ጉዳያቸው ታይቶ በዋስ እንዲለቀቁ ተደርጓል፤ የፈራረሱ የቀበሌ የመንግስት አደረጃጀቶችም እንደገና ተዋቅረዋል፤ በግጭቱ ተሳትፎ ያላቸው አካላትንም በህግ መጠየቅ ተጀምሯል።

የጸጥታ መዋቅሩ ተገምግሞ በግጭቱ የተሳተፉና በግዴለሽነት ያለፉ የጸጥታ ኃይሎችን በህግ መጠየቅ፣ የአቅም ክፍተትና የግንዛቤ ችግር ያለባቸውም ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገም ይገኛል።

በዚህም ከጋንታ መሪ እስከ ብርጌድ አዛዥ የሆኑ 116 የልዩ ኃይልና 41 የመደበኛ ፖሊስ አመራሮች የ10 ቀን የአሰልጣኞች ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።

በስልጠናው ተገኝተው መመሪያ ያስተላለፉት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን የጸጥታ ኃይሉ ለ27 ዓመታት ህወሓት በዘራበት የሀሰት ትርክት ተመርዞ ቆይቷል።

“የክልሉ ልዩ ኃይልና መደበኛ ፖሊስ አባላት ለህዝብና ለህገ መንግስቱ ታማኝ በመሆን ‘ብልፅግና አሀዳዊ ስርዓት ነው፤ ቤንሻንጉልን ሊያጠፋ ነው’ እያሉ የሀሰት ወሬ ከሚነዙ የጁንታው ተላላኪዎች ተጽዕኖ መውጣት አለባቸው” ብለዋል።

“በመተከል ለተከሰተው ግጭትና የጸጥታ መደፍረስ መንስኤው ይሄው መሆኑንም በውል ልትገነዘቡ ይገባል” ብለዋል።

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደጫካ የገቡ አካላት በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ፤ የማይሰጡ ከሆነም ካሉበት እንዲደመሰሱ በማድረግ ህዝቡን በእኩልነት ሊያገለግሉ እንደሚገባ ነው ርዕሰ መስተዳደሩ ያሳሰቡት።

በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ “ከክልሉ ልዩ ኃይልና መደበኛ ፖሊስ መተከል፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሎም ኢትዮጵያ ብዙ ትጠብቃለች” ብለዋል።

በመሆኑም የጸጥታ ኃይሉ ዘር፣ ቀለምና ጎሳ ሳይለይ ህዝቡን በእኩልነት በማገልገልና ከግብረ ሃይሉ ጋር በመተባበር መተከልን ከገባበት ችግር ማውጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የተመከል የተቀናጀ ግብረ ሃይልን የሚመሩት ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ የክልሉ የጸጥ ኃይል አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና ህዝቡን ከጥቃት እንዲከላከል አስፈላጊውን ትጥቅ እንዲታጠቅ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል።

“ህወሓት ልዩ ኃይሉን ታንክና መድፍ ለማስታጠቅ እንደሞከረው ሳይሆን በህጉ በተቀመጠው አግባብ መሰረት የክልል ጸጥታ ሃይሎች መታጠቅ ያለባቸውን ትጥቅ እንዲያገኙ ይደረጋል” ብለዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጸረ ሽምቅና ልዩ ጥበቃ አድማ ብተና መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ዶሳ ጎሹ በበኩላቸው የክልሉ ልዩ ሃይል በመተከል የደረሰው ዘግናኝ እልቂት ጸጽቶት ህዝቡን ለመካስ መዘጋጅቱን ገልጸዋል።

ENA

  • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
    የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
  • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
    “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
  • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
    አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading

Leave a Reply