ከትህነግ ፍጻሜ በሁዋላ የሚጠበቀው ኤርትራን ዴሞክራሲ አገር የሚይደርገውን እቅድ ኢሳያስ በቅርቡ ይፋ ሊያደርጉ ነው

ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ ኤርትራን ዴሞክራሲያዊ አገር የሚያደርግ እቅድ አዘጋጅተው ማጠናቀቃቸው ተሰማ። እቅዱን ለህዝባቸው በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የአውሮፓ ዲፕሎማት የኢትዮ 12 መረጃ አጋሪ ኢሳያስ አፉወርቂ ከውስን ታማኞቻቸው ጋር በመሆን ኤርትራን ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ የሚያችል እቅድና የቅዱ አተገባበር የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀታቸውን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አገራቸውን መምራት ቢፈልጉም ይህን ያህል ዓመታት በስልጣን የመቆየት እቅድ እንዳልነበራቸው ከታማኞቻቸው እንደሰሙ ያስታወቁት ዲፕሎማት፣ አሁን ግን የቀድሞው አካሄድ እንደማይቀጥል መስማታቸውን ገልጸዋል።

የህገ መንግስት ማሻሻያ እንደሚደረገና፣ የምርጫ ጊዜ በይፋ እንደሚቆረጥ ያመለክቱት ምንጩ “ የጎሳና የብሄር አደረጃጀትት የሚከለክል ህግ በዋናነት ይደነገጋል” ብለዋል።

ከትህነግ መክሰም በሁዋላ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኤርትራን በቀድሞ መንገድ ሊመምራት ምክንያት እንደሌላቸው በተደጋጋሚ እየተደመጠ ነው። በርካታ የኤርትራ ተወላጆች እንደሚሉት እስካሁን ኢሳያስ ዝም የተባሉት በትህነግ ምክንያት ነው። አሁን ግን በቀድሞ መልኩ የሚቀጥል ነገር አይኖርም።

አገር ወዳድ ለመሆናቸው በየትኛውም መስፈርት ጥያቄ የማይቀርብባቸው ወዲ አፎም እድሚያቸውም እየሄደ በመሆኑ አገሪቱን ለተተኪ የሚያስረክቡበትና ፈጣሪ እስከፈቀደላቸው ድረስ በሰላም ቀሪ ጊዜያቸውን ለመኖር ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው አስተያየት ይሰነዘራል።

ኢሳያስ ኤርትራን ፍጹም ዴሞክራሲያዊ አገር በማድረግ የማያልፍ ስም ተክለው ሊያልፉ እንደሚገባ የተቆመው የዘወትር አስተያየት ሰጪ ግርማይ ሳምሶን “ ብዙ ጥፋት ጠፍቷል። እንደ አገር መቆየታችን ያኮራናል። አሁን በቂ ነው። በትክክል አስበው ከሆነ ድንቅ ሃሳብ ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

Read this ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ በዶላር ሳይሆን በብር የኪራይ ውል የምትጠቀምበት ስምምነት ጫፍ እየደረሰ ነው

ፕሬዚዳን ኢሳያስ በኤርትራ የነጻ ፕሬስና የመስብሰና የመናገር መብትን ለህዝባቸው ክፍት እንደሚሆን መቼ ለህዝባቸውና ለዓለም በገሃድ እንደሚናገሩ አልተተቆመም። ይሁን እንጂ ስራው የተጠናቀቀ በመሆኑ በቅርቡ ፍንጭ እንደሚሰጡ ይጠበቃል ሲሉ የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ተጠቅመው ያገኙትን መረጃ ምንጫችን ነግረውናል።

ኤርትራ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የተዘጋች፣ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምባት አገር በመባል የምትወቀስ አገር ናት። የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ከሰሜን ኮሪያ ጋር እያገናኟት ወቀሳቸውን ቢያሰሙም ፕሬዜዳንት ኢሳያስ በሚወራባቸው ደረጃ ዜጎቻቸው የማይተሏቸው መሪ እንደሆነም ምስክርነት ይሰጣል። በኢኮኖሚ የደቀቀች አገር በመሆኗ አብዛኞች በኤርትራ ነገ ዛሬ ሳይባል ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያምናሉ። ኤርትራ ከኢጋድ፣ ከአፍሪካ ህብረትና ከዓለም እንድትገለል ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ከፍተኛ ዘመቻ ማደርጋቸው አይዘነጋም። በኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኤርትራ ሄደው ሰላም ካወረዱ በሁዋላ በኤርትራ ተጥሎ የነበረው የተባበሩት መንግስታት ማእቀብ እንዲነሳላት በምስራቅ አፍሪቃም የመሪነት ሚና እንድትጫወት የረዱ መሆናቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያና ኤርትራ በመከላከያን በደህንነት ጉዳዮችም አብረው ለመስራት መስማማታቸው አይዘነጋም

የአሰብ ወደብን ኢትዮጵያ የራስዋን ብር እየከፈለች እንድትጠቀምና ኤርትራም ከኢትዮጵያ የምትፈልገውን ምርት ከኢትዮጵያ በምታገኘው ብር መግዛት እንምድትችል የሚፈቅደውን ስምምነት ይፋ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንና የአሰብ መንገድ ግንባታ የዚሁ ውል ማስፈጸሚያ አካል እንደሆነ አስቀድመን እኚሁን የዲፕሎማቲክ ምንጭ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

  • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
    የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
  • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
    “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
  • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
    አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading

Leave a Reply