ኢትዮጵያ በሰባት ውሀማ ስፍራዎች የውሀ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደምታስጀምር አስታወቀች።

ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ዓመታት ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሰባት ውሀማ ስፍራዎች የውሀ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደምታስጀምር አስታወቀች።

ሀገሪቷ አሁን ያሉት እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ይሰራሉ ቀድመው ስራ የጀመሩት ደግሞ በተሻለ ቴክኖሎጂ ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል።

በ10 አመቱ መሪ የትራንስፖርት የልማት እቅድ ውስጥ ከተቀመጡ ጉዳዮች መካከል የውሀ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ይገኝበታል፡፡

በዚህም በጣና ሀይቅ፣ ባሮ ወንዝ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ ተከዜ፣ ህዳሴ ግድብ እና በጊቤ የውሀ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ለማልማት ታቅዶ ስራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጅነር የኋላሸት ጀመረ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በ10 ዓመት የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድ የዉሃ ትራንስፖርት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።

የዉሃ ትራንስፖርት ደህንነቱ የተጠበቀና በሚፈለገዉ ደረጃ በሀገራችን ያለዉን ለዉሃ ትራንስፖርት አገልግሎት አመቺ የሆኑ ወንዞችና ሃይቆች በአግባቡ በመጠቀም ለህዝብና ለጭነት ትራንስፖርት አመቺ ሆነው ይለማሉ ተብሏል፡፡

የውሀ ትራንስፖርት አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ሆኖ እንዲያገለግል እንዲሁም ለመዝናኛና ለቱሪስት መስህብነትም እንዲያገለግሉ መሰረተ ልማቶች በስፋት ይለማሉ ተብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ethio FM 108

You may also like...

Leave a Reply