የመከላከያ ሰራዊት አባል መሆን አገርንና ሕዝብን ማገልገል ነው … ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ

የአገር መከላከያ ሰራዊት አባል መሆን አገርንና ሕዝብን ማገልገልና ጀግኖችን መቀላቀል ነው ሲሉ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ።

ወጣቶች ወደ ውትድርና ሙያ በመግባት ለአገርና ለሕዝብ ክብር መቆም አለባቸው ብለዋል።

ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ከመከላከያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የአገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ ተጋድሎ በመፈጸም አገራዊ ተልዕኮውን መወጣቱን ገልጸዋል።

ሰራዊቱ በሕግ ማስከበር እርምጃው የተሰጠውን ተልዕኮ በስኬት በማጠናቀቅ የአገር አለኝታነቱን ማሳየቱንም ተናግረዋል።

“ሰራዊቱ በጀግኖች የተሞላ ነው፤ የዚህ ሰራዊት አባል መሆን የጀግኖች አባልና መሪ ከመሆን ባለፈ ክብር የሚያጎናጽፍ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

ማንኛውም ሰው በየትኛውም መስክ ጀግና መሆን ይፈልጋል ያሉት ሌተናል ጄኔራሉ የመከላከያ ሰራዊት አባል መሆን ደግሞ ጀግንነትን የሚያላብስ እንደሆነ አመልክተዋል።

በሰራዊቱ አባል ሆኖ ሕዝብን ማገለግል ትልቅ ክብር መሆኑን በመግለጽ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች የውትድር ሙያ ዋና ተግባር አገርና ሕዝብን ማገልገል መሆኑን አውቀው ሙያውን እንዲቀላቀሉና የኢትዮጵያ ወታደር የመሆን እድልን እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት ራሱን ለማዘመን የማሻሻያ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም መግለጻቸውን ከመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር እርምጃ በራያ በኩል ያለውን ግንባር ሲመሩ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የካቲት

Via (ኢዜአ)

Categories: SOCIETY

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s