የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽነሮች ያወጡትን መግለጫ መንግስት አወገዘው፤ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ይዘሉታል ብሏል

የዚህ ሁሉ ችግር መሰረታዊ ምክንያቱን ማንሳት የማይፈለገው የአውሮፓ ሕብረት ኢቶጵያን የሚጫንበት ምክንያት ለበርካቶች እንግዳ ነው። እንግዳነቱ ብቻ ሳይሆን በዚህ የተሳሳተ አቋም ውስጥ ህብረቱ የሚጠቀመው ጉዳይ ምን እንደሆነ የሚመለሱ የሉም።

በኢርትራ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ መገኘት መንግስት ባይናገርም የሚሰጠውን አሳማኝ ምክንያት ኢትዮጵያ ላይ ሁሉንም ጉዳይ የሚደፈድፉት ሃይሎች አያስተባበሉትም። የመከላከያ ሰራዊት በተኛበት መረሸኑን፣ መታረዱንና ኢሰብአዊ ድርጊት ስለተፈጸመበት ርምጃ መውሰዱን አውሮፓዊያኑ ባያስተባበሉም ጭራሽ ማንሳት የማይፈልጉት ለምን እንደሆነ ያልተረዳው የኢትዮጵያ መንግስት ለመግለጫው ምላሽ ሰጥቷል። የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነሮች የሚከተለውን ነው ያሉት።

ሦስት የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽነሮች ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ፦ ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት እያባባሱ የሚገኙ ያሏቸው የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ።ዩናይትድ ስቴትስ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ከዚሕ ቀደም ያደረገችዉን ጥሪ ሕብረቱ እንደሚደግፍ ኮሚሽነሮቹ አስታዉቀዋል።

የኤርትራ ወታደሮች ግፍ ይፈጽማሉ፣ ግጭት እና ኹከት እንዲባባስም ሰበብ ሆነዋል ሲል የኅብረቱ ሦስት ኮሚሽነሮች የጋራ መግለጫ ያትታል። መግለጫውን የሰጡት የኅብረቱ የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦሬል፤ የአስቸኳይ ርዳታ ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች እና የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነሯ ጁታ ኡርፒላይነን ናቸው።

ትግራይ ክልል ውስጥ እየታየ ያለው «አስከፊ» የሰብአዊ ቀውስ እና በአካባቢው ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ያሳሰባቸው መሆኑን አክለው ገልጠዋል። የሰብአዊ ርዳታው መዳረስ በትግራይ ክልል እና በአጎራባች አካባቢዎች የአፋር እና የአማራ ክልሎችም የሰብአዊነት መርኆችን፣ ገለልተኝነትን፣ ሰብአዊነትን፣ ለማንም ባልወገነ እና ነጻ በሆነ መልኩ ሊረጋገጥ እና ሊፈቀድ ይገባል ብለዋል።

ለአውሮፓ ኮሚሽነሮች አቤቱታ የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ነው የሰጠው። በምላሹም ቅድሚያ ያነሳውና የአውሮፓ ህብረት ከጅምሩ አንስቶ የተንሸዋረረ አቋም እንዳለው ነው። የአገር መከለካያ ሰራዊት በራሱ ወገኖች የተፈጸመበትን ጭፍጨፋና ክህደት ህብረቱ ቸላ ማለቱንም ኮንኗል። ከመግለሻው የተወሰደውን ዜና ፋና እንደሚከተለው ዘግቦታል።

የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ክልል እየቀረበ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ከግንዛቤ ያላስገባ እና ተጨባጭ ዕውነታን ያልተረዳ መረጃ ማውጣቱ አግባብነት የሌለው መሆኑን መንግስት ገለጸ።

See also  አብነት ጥይት የማይበሳው መኪና ለማስገባት መንግስትን ጠየቁ

ህብረቱ ያወጣው መረጃ መንግስት በክልሉ እያቀረበ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ከግንዛቤ ያላስገባ እና በመረጃ ያልተደገፈ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምሽቱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መንግስት በአካባቢው የህግ ማስከበር ስራን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ህብረቱ የሚያወጣው መረጃ ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ እና ተገቢነት የሌለው ነውም ብሏል።

በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከተፈጸመበት እለት አንስቶ በወንጀለኞች ላይ የተወሰደውን የህግ ማስከበር ስራ እና ወንጀለኞቹን አድኖ ህግ ፊት የማቅረብ ስራውንም ችላ ብሎ ቆይቷል ብሏል።

መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን ካጠናቀቀ በሗላ የመሰረተ ልማት ጥገና ስራዎችን መስራቱን እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን ማጠናከሩንም አስታውቋል።

የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱም በበርከታ የትግራይ ክልል ተደራሽ እንዲሆን መንግስት እየሰራ መሆኑንም ገልጿል። ይህ ተግባርም በተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች እንዲጎበኝ ተደርጓል ነው ያለው።

የህወሓት ቡድን የጥፋት እና የወንጀል ድርጊቶች በገልተኛ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሸን ተጠንቶ ግኝቱም ይፋ መደረጉን መግለጫው አንስቷል። በዚህም መሰረት የጥፋት ቡድኑን ለህግ የማቅረብ ስራ እየተሰራ እንዳለ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ከ27 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ1 ሚሊየን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች መሆኗን እና ኤርትራውያን ስደተኞችንም ዓለም አቀፍ መብታቸው ተከብሮ በተመሳሳይ እየኖሩ እንዳለም ነው የገለጸው።

የአውሮፓ ህብረት እንደ ቀደምት መልካም አጋርነቱ ልማትና ሰላም በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ድጋፉን መቀጠል ይኖርበታል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

    Leave a Reply