ትራምፕ የካፒቶሉን ነውጥ አነሳስተዋል መባሉን ጠበቆቻቸው ካዱ

የካፒቶሉን ሂል ነውጥ አነሳስተዋል በሚል ክስ የቀረበባቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አስመልክቶ ምላሽ የሰጡት ጠበቆቻቸው ደጋፊዎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ነው ሁከቱን ያስነሱት በማለት ትራምፕ ተሳትፎ የላቸውም ሲሉ ክደዋል።

በትናንትናው ዕለት በነበረው ቅድመ- የፍርድ ሂደት የትራምፕ ጠበቆች ነውጡ ከቀናት በፊት ታቅዶና በደንብ ተደራጅተውበት እንደነበር የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) መረጃዎችን በመጥቀስ አስረድተዋል።

ይህም ማለት ትራምፕ ነውጡን አላነሳሱም በማለት ይከራከራሉ።

ከዚህም በተጨማሪ የፍርድ ሂደቱ ኢ-ህገ መንግሥታዊ ነው በማለት የጠቀሱ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚያነሱት ከስልጣን ተነስተው እንደ ማንኛውም ዜጋ እየኖሩ ያሉ ናቸው ጉዳያቸው በምክር ቤቱ እንዴት ይታያል ሲሉ ይጠይቃሉ።

ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም የትራምፕ ደጋፊዎች የህግ መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ውይይት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ሰብረው በመግባት ነውጥ አስነስተዋል ተብሏል።

ዶናልድ ትራምፕ ሁከቱና ነውጡ ከተነሳ ከሳምንት በኋላ በስልጣን ላይ እያሉ ሁለት ጊዜ እንዲከሰሱ የተወሰነባቸው ወይም ኮንግረሱ በወንጀሎች የጠየቃቸው የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሆኑ

የትራምፕ በምክር ቤቱ የሚኖራቸው የፍርድ ሂደት በዛሬው ዕለት ይጀመራል።

ጠበቆቻቸው የፍርድ ሂደቱን “ፖለቲካዊ ቲያትር” በማለት የጠሩት ሲሆን ይህ “አሳፋሪ የፖለቲካ ድርጊት” ተቃዋሚዎችን ዝም ለማሰኘትና ፓርቲው ላይ ያነጣጠረ የዲሞክራቶች ሴራ ነው ይላሉ።

“የክሱ ሂደት በጭራሽ ከፍትህ ጋር የተያያዘ አይደለም” በማለት በመግለጫቸው አስፍረዋል።

ዲሞክራቶች በበኩላቸው ለጆ ባይደን ስልጣን እንደማያስረክቡና ለህዝቡ መታገል አለባችሁ በማለት ያስተላለፉት ቃል ለነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው መነሳሳትን ፈጥሮላቸዋል በማለት ይከራከራሉ።

ጠበቆቻቸው በበኩላቸው የመናገር ነፃነታቸውን ከማስጠበቅ ባለፈ ምንም አላደረጉም ቢልም ክሳቸውን በበላይነት እያየ ያለው የምክር ቤቱ አካል በበኩሉ “የአሜሪካን ህዝብ ክደዋል። ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዳይኖር እክል ፈጥረዋል። ይህ ደግሞ በመሪዎች ታሪክ ተፈፅሞ የማያውቅ ህገ መንግሥቱን የሸረሸረ ወንጀል ነው” ብሏል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከወር በፊት ነበር በዋይት ሃውስ አቅራቢያ ለነበሩ ሰልፈኞች “በሰላማዊና በአርበኝነት” ድምፃቸው እንዲሰማ እንዲያደርጉ ጥሪ ያስተላለፉት።

ነውጠኛ ሰልፈኞቹ ወደ አሜሪካው ካፒቶል ህንፃ እየተቃረቡ ነበር ተብሏል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት አክለውም “በእልህ እንዲታገሉም” ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።

በዚህም የተነሳ ነውጡን አነሳስተዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ትራምፕ የምስክርነት ቃሌን አልሰጥም ብለዋል።

በወቅቱ በተነሳው ሁከት አራት ተቃዋሚዎች ሲገደሉ በቦታው የነበረ የካፒቶል ፖሊስም ተገድሏል። ፖለቲከኞቹም ተደብቀው ነበር።

bbc Amharic

  Related posts:

  125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
  «በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
  በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
  የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
  «ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
  ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
  የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
  "እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
  "አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
  አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
  መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
  በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
  የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
  ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
  "ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

  Leave a Reply