ኦነግ በምርጫው ለመሳተፍ አቶ ዳውድ ኢብሳን ልመና ላይነው

NEWS

. ኦነግ በምርጫው ለመሳተፍ እየተፍጨርጨርኩ ነው አለ::

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በውስጣዊ የፖርቲ ቀውስ የተነሳ በ6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ አጣብቂኝ ውስጥ መውደቁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አሳውቋል፡፡

የፖርቲው ቃላቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ምርጫ ቦርድ ፖርቲው የገጠመውን ችግር ለመቅረፍ አሰቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያደርግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ቢሰጥም በተቀዳሚ ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እንቢተኛነት ማድረግ እንዳልቻለና እና ልመና ላይ መሆኑን ነግረውናል፡፡

ውዝግቡ ከተፈጠረ ወዲህም ምርጫ ቦርድ ጋር በስመ ሊቀመንበርነት የግንባሩ ተወካይ ናቸው በሚል ግንኙነት ስላላቸው ፈጽሞ የጋራ ውሳኔና መመሪያ እየሰጡም ፤እየተቀበልንም አይደለም ነው የሚሉት አቶ ቀጀላ፡፡

እኛ ምርጫ ቦርድ ችግሮን ተገንዝቦ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን እና ወደ ምርጫ ዝግጅቱ እንድንገባ እየጠየቅን ነው ይላሉ፡፡
አሊያም ግን ምርጫ ውስጥ የማይሳተፍ ፖርቲ ጥቅሙ ምን ሊሆን ይችላል ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡

በዚህ አይነት ከሄድንም የእርሳቸው ስብስብ በምርጫው ለመሳተፍ አይችልም ምክንያቱም ህጋዊ አይደለም ባይ ናቸው ፡፡

የእኛ ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ከእርሳቸው ጋር የሚያደርገውን ግንኙንት እንዲያጤነውና መፍትሔ እንዲሰጠን ነው ምክንያቱም ይህ ነገር አግባብነትም ሆነ ፍትሐዊ አይደለም ነው የሚሉት አቶ ቀጀላ፡፡

ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሄድ የግድ መሆኑን የሚያነሱት አቶ ቀጀላ አሁን ድርጅታዊ ቀውስ ውስጥ ስላለን ወደ ምርጫው መግባት አንችልም ከባድ ብለው፡፡

ችግሮ እስኪፈታ ምርጫ ቦርድ በልዩ ሆኔታ ቀናትን ገፋ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን ፡፡ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ምርጫውን መካፈል ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው ያነሱት፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 2 ቀን 2013 ዓ.ም

Related posts:

"መከላከያ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በሚችልበት አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል" አብይ አህመድ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Leave a Reply