በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበሩ ጤና ተቋማት ወደ መውደበኛ አገልግሎት እየተመለሱ መሆኑን የጤና ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡ ዜናው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በትግራይ ከ80 በመቶ የሚሆነውን ስፍራ ማዳረስም ሆነ እርድታ መስጠት አልተቻለም ሲል የዓለም ዓቀፉን ቀይ መስቀል ጠቅሶ በዘገበበት ወቅት ነው።

የዓለም አረፉ ቀይ መስቀል የኤፒን ዘገባ ትክክል እንዳልሆነ ጠቁሞ ማስተባበያ ለመንግስት ሚዲያ መስጠቱን ተከትሎ ይፋ እንደሆነው የትግራይን 80 ከመቶ የሚያዳርስ የጤና ጣቢያዎች ወደ አግለግሎት መመለሳቸውን ሚንስትሯ ናቸው ይፋ ያደረጉት።

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት የጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት አሰጣጥ ለመመለስ የጤና ሚንስቴር እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች እና ከሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመሆን የቀን ተቀን ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ላይ ናቸው።

በተደረገው ድጋፍ እና ክትትል የመድሀኒትና ግብአት ስርጭት ተደርጎ ወደ ስራ የገቡ ጤና ተቋማት 88 ሲሆኑ፣ በአምስቱም ዞኖች በአጠቃላይ ካሉት 40 ሆስፒታሎች ውስጥ 15 ሆስፒታሎች ሙሉ በሙሉ እና 5 ሆስፒታሎች በከፊል አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ሚኒስትሯ አመልክተዋል።

በትግራይ ከሚገኙት 224 ጤና ጣቢያዎች 68 ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጡ ናቸው፡ ሌሎች ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች በአጭር ጊዜ ወደ አገልግሎት ለመመለስ እና የጤና አገልግሎቶችን ለሕዝቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ሚንስቴር፤ ኤጀንሲዎቹ እና የጤና ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየሰሩ እንደሚገኙ ከሚኒስትሯ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

ተቋማቱን ወደ አገልግሎት ለመመለስ የሚያስችሉ መድሀኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎችን በማሰራጨት ረገድ የመቀሌ እና የሽሬ የመድሀኒት አቅርቦት ቅርንጫፎች የግብዐት ስርጭት እንዲፋጠን በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ እንደሚገኙ አክለው ገልጸዋል።

Leave a Reply