ፈረሱላ ቡና – (Cup of Excellence – Ethiopia)

ፈረሱላ ወይም ፈረሲላ ሲነሳ ቅድሚያ የሚታወሰን አንድ ጉዳይ ነው። ይህም ጉዳይ አረንጓዴ ወርቃችን ነው። አረንጓዴው ወርቃችን ደግሞ ቡናችን ነው። ይህ የአገራችን ማሕጸን አስቀድሞ የወለደው ቡና ዛሬ ዓለማችን ሳያዛንፍ ይጎነጨዋል። ቡና!!

ዛሬ ዓለም ላይ የቡና ንግድ ስም የተከሉ እንደ ስታርባክስ አይነት ተቋማት ቡናን ከወከድነው ከእኛ በላይ ከቡና ጋር ስማቸው ይነሳል። ዛሬ ከሰላሳ ሺህ በላይ አድራሻዎችን ከሰባ በላይ አገሮች ላይ የተከለው ስታርባክስ ዋና ቢሮው ሲያትል አሜሪካ ያደረገ የንግድ ተቋም ነው። ዛሬ ዓለም ላይ “ ስትራ ባክስ” ቡናን ተንተርሶ የቆመ የንግድ ቡራኬ በመሆኑ ስሙ ብቻ ገበያ ነው። ብር ነው። ሃብት ነው።

በኢትዮጵያ የቡና ታሪክ ባለቤትነት ፣ በኢትዮጵያ ቡና ልዩ ጣዕም፣ በኢትዮጵያ ቡና ተፈላጊነት የቡና ብራንድ አለመኖሩ ከቆረቆራቸው ዜጎች መካከል የሙለጌ ቡና ላኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር ቤተሰብ የ “ኩራዙን” ፋና በመከተል አዲስ ሩጫ ከጀመረች ሰነባብታለች።

የዘመቻዋና የሃሳብ ለዕልናዋ መነሻ “ ፈረሱላ” ቡና “FERESULLA COFEE”  በሚል ስያሜ ቡናችንን ማቅረብ ነው። “ብናችን እፊታችን እንዳሻችን” ይላል የዓይን ምስክር። ያሻውን ቡና ፉት ብሎ እርካታውን ሲገልጽ ቃል የለውም። በሁሉም ነገር ረክቷል።

ሳሪስ መንገድ ሙለጌ ሕንጻ “ ፈርሱላ ቡና ” ሲገቡ የቡና ላቦራቶሪ ያገኛሉ። በግድግዳዎቹ ላይ በተሰየሙት ምስሎች ትርጉም እየተደመሙ ቡናዎት እፊትዎ ተቀምሞ፣ እፊትዎ ነጥሮ፣ እፊትዎ ኮለል ብሎ ይቀርባል። እንደ ምስክሩ ከሆነ ፈረሱላ ቡና አገራዊ ብራንድ ሊሆን ይግባል። የቡና መጎንጫ ብራንድ ቡናው ወደተፈጠረበት መመለስ አለበት።

ከአሜሪካ ወደ ፈርሱላ ብቅ ብለው የነበሩ ውቤ አያልነህ ለልጃቸው ግብዣዋን ሲያመስግኑ “ የኢትዮጵያን ልዩ ጣዕም ቡና  (Cup of Excellence – Ethiopia) አጣጣምኩ” ብለው እንደነበር ልጃቸው ነግራናለች። የዚህ ካፊቴሪያ ወይም የቡና ላቦራቶሪ መሐንዲስ ዓላማዋም ፈረሱላን የኢትዮጵያ ቡና ብራንድ ማድረግ ይመስላል። ፈረሱላ ቡና!!

ፈረሱላ አስራ ሰባት ኪሎ ማለት ነው። ስሙ ኢትዮጵያዊ ነው። ቡና የሚመዘነው በፈረሱላ ነው። ቡና ሲጠጣ ይህን ስም እንዲይዝ የታሰበው ቡናን ለዓመታት በፈረሱላ ሲያቀርቡ ከነበሩ ቤተሰብ ነው።

በፈረሱላ ቡና ላቦራቶሪ ውስጥ ቡና ሲጠጡ አንድ አስገራሚ ሰዕል ያያሉ። ላምባ – ኩራዝ ላይ ጀምሮ በኢንዘስትመንት ያንቆጠቆጠ ቅብ!! የግድግዳው ታሪክ የላቦራቶሪው ሌላ ገጽ ነው።

ምስጋና – የፈረሱላ ቡና ላቦራቶሪን አይተው ምስክርነታቸውን ላጋሩን ምስጋናችን ትልቅ ነው።

Related posts:

ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”

Leave a Reply