ጎንደር- የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት በመጪው ነሃሴ ይጠናቀቃል

የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክትን በመጪው ነሃሴ ወር ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አስታወቁ። 6 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት የተመደበለትን የግድብ ግንባታ እንቅስቃሴ የፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ዛሬ ጎብኝተውታል፡፡

ስራ እስኪያጁ ኢንጂነር ጸጋዬ መኮንን በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት የግድቡ ግንባታ 69 በመቶ ደርሷል፡፡ባለፉት አመታት ፕሮጀክቱ ገጥሞት የቆየው የግንባታ ቁሳቁሶች እጥረት አሁን ላይ በመፈታቱ የግንባታ ስራው 24 ሰአት በመከናወን ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡ ግድቡ 77 ነጥብ አንድ ሜትር ከፍታና 890 ሜትር ደግሞ እርዝመት ሲኖረው 187 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

ግድቡ ከሚይዘው ውሃ 30 በመቶው ለጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት እንደሚውል የተናገሩት ኢንጅነሩ 17ሺ ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት 45ሺህ አባወራ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ፕሮጀክቱን በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ ወደ ስራ ቢገባም በግንባታ ሂደት ተጨማሪ ስራዎች በማጋጠማቸው ግንባታው 7 አመት እንደፈጀም ተናግረዋል፡፡

May be an image of 2 people

በጉብኝቱ ወቅት የከተማው ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ እንደገለጹት ግድቡ ሲጠናቀቅ ለከተማው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውለውን 30 በመቶ የውሃ ድርሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ነው፡፡አዲስ የውሃ ማጣሪያ ለመገንባትና የከተማውን የውስጥ መስመሮች ለማሻሻልም ከኢትዮጵያ ዲዛይንና ጥናት ድርጅት ጋር የ21 ሚሊዮን ብር የዲዛይን ጥናት ስምምነት መፈረሙንም ተናግረዋል፡፡

የግድቡን ውሃ ለከተማው ነዋሪዎች ለመጠጥነት ለማዋል በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊ የውሃ ማጣሪያ ለመገንባት አለም አቀፍ ጨረታ በቅርቡ እንደሚወጣም አስረድተዋል፡፡ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተደረገ ያለውን ርብርብ ሚኒስትሯን ጨምሮ የፌደራል የክልልና የከተማው አመራሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

(ኤዜአ)

  • ትህነግ ቅድመ ሁኔታ አንስቶ ድርድር ጠየቀ፤ “ክተቱ ለትህነግና ለኢትዮጵያ ጠላቶች እንጂ ለትግራይ ሕዝብ አይደለም”
    አዲስ አበባ በሁለት ሳምንት ለመግባት የሚያግደው አንዳችም ሃይል እንደሌለ በይፋ ያስታወቀውና በቃል አቀባዩ ጌታቸው አማካይነት ትናንት ጎንደርና ወልቃይት በአሸባሪው ትህነግ እጅ መውደቁን ያወጀው ቡድን ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ትቶ ድርድር እንደሚፈልግ ማስታወቁ ተሰማ። ለዚሁ ተግባር አዲስ አበባ የገቡ አሜሪካዊ አማላጆች መኖራቸውን ታውቋል። ቀደም ሲል ስምንት ቅደመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ የነበረው የትግራይ ሕዝብContinue Reading
  • ትህነግ ሲዘጋ፤ ኢትዮጵያ ትወቀሳለች- እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል?
    ኢትዮጵያዊያን ላለፉት 50 ዓመታት ስለምን በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ይሰቃያሉ? በረሃ ሆኖ ስቃይ፣ መንግስት ሆኖ መከራ፣ ሲባረር ደግሞ ” እኔ የማልመራት አገር ትፍረስ” ብሎ ዘመቻ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የድሮው ሳይቆጠር ስለምን ግማሽ መዕተ ዓመት በትህነግ ሲጠበስ ይኖራል? መቼ ነው ይህን ሕዝብ ትህነግ የሚተወው? የሰሞኑ ክተት የሳምንቱ ኩርፊያ ውጤት አይደለም። የተጠራቀመContinue Reading
  • የተመድ የሚል ጽሁፍ ያለበት ኣወሮፕላነ ምስራቅ ሃረርጌ ወደቀ
    ዛሬ አመሻሽ ላይ በምስራቅ ሀረርጌ ስለወደቀው አውሮፕላን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ የሰጠው ምላሽ! ዛሬ አመሻሽ 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ አንድ አነስተኛ አዉሮፕላን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ መዉደቁን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። የኮምቦልቻ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ አራት ሰዎችን የጫነዉContinue Reading

Leave a Reply