የፍትህ ጥያቄው እነማንን አቅፎ እነማንን እንዲገፋቸው ነው የሚፈለገው? ፍትህ ለእገሌ …

ዛሬ ላይ ፍትህ ” ለእገሌ የሚል” እና “እኔም እገሌ ነኝ” የሚሉ ጸረ ፍትህ መፈክሮች በስፋት መስማት ተለምዷል። ፍትህ አንገብጋቢና የህዝብ ሁሉ ምኞት ቢሆንም፣ በአብዛኛው ፍትህ ሲጠየቅ የሚሰማው በጎሳ፣ በዘር፣ በቡድን፣ በትስስር ወይም በተመሳሳይ የፖለቲካ ስሜት ውስጥ በተቋጠረ ውል መነሻነት መሆኑ ያሳዝናል። የሚተየቀውንም ፍትህ ፍትሃዊ አያደርገውም። ፍትህ ፍትሃዊ ጥያቄ የሚሆነው ለሁሉም እኩል ሲሆን ነው። ህግ ለገዳይም፣ ለሟችም እኩል ስትፈርድ ፍትህ ታበራለች። ከዚህ ውጭ ፍትህ አንዱ ወገን ላይ ብቻ እንድታበራ ሲተየቀ፣ ወይም ልከማስገደድ ሲሞከር ፍትህ ሌሎች ላይ ብርሃኗን ታጠፋለች። ይህ ሊደገፍ አይገባም።

ቢቻል ቢቻል አንድም እስረኛ ባይኖር፣ በሰላምን በሃሳ ልዩነት ወደ ምርጫ መግባት ቢቻል ደግ ነበር። መታደል ነበር። ግና በተጠናወተን የጎሳ ፖለቲካ ሳቢያ ሁለት ዓይነት ፍትህ ፈልጊዎች አሉን። አንደናዎቹ የታረዱ፣ የተጨፈጨፉ፣ ንብረታቸው የተዘረፈና የወደመባቸው፣ ሜዳ ላይ የፈሰሱ፤ በሌላ ወገን የገደሉ፣ ያረዱ፣ ይሳገደሉና ያሳረዱ ወይም መዋቅሩን የዘረጉ፣ የዘረፉና ያፈናቀሉ። እንግዲህ ” ፍትህ ለእነ እገሌ ወይም እኔ እነ እገሌን ነኝ ” ሲባል ” የትኞቹን?” የሚል ጥያቄ ሲነሳ “አልሰማሁም” አላየሁም ማለት አይቻልም። ይህ አጠቃላይ ሃሳብ ነው። አራጁን ህግ ሲፈልገው ” እኔ ጌታቸው አሰፋ ነኝ” የሚሉና እነ ዶክተር አምባቸውን ያስበላን እብድ ” እኔ አሳምነው ነኝ” የሚሉ ፍትህ ጠያቂዎች ባሉበት አገር ስለየትኛው ፍትህ እንደሚወራ ማሰብ በራሱ ህመም ይሆናል። የአማራውን ክልል ሾተላዮች ሌላ ጊዜ አነሳለሁ ፤ በዚህ መነሻ እስኪ ወደ ኦሮሚያ እናምራ !!

ኦነግ ምርጫ ኖረም አልኖረም ራሱን ከቀውስ ለይቶ እንደማያውቅ ይነገራል። በርካታ ጊዜ ሲከፋፈል ኖሯል። አሁንም ይህ በሽታው ሳይለቀው እንዲሁ ተከፍሏል። አቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግና ሲረከቡ መሃል ሆነው ምርጫ በማስደረግ ድርጅቱን አንድ ሆኖ በጉባኤ ለሚመረጥ እንዲያስረክቡ ቢሆንምክ ኤርትራ ከገቡ በሁዋላ ሁሉንም ትተውት ቆዩ።

በኤርትራ በረሃ በርካታ የተፈጸሙና አቶ ዳውድን ህግ ፊት ሊያቀርቡ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ቢነገሩም፣ ደርጅርቱን ማቆየታቸው በራሱ እንደ አንድ ጠንካራ ጎን መታየት እንደሚገባው የሚያምኑም አሉ። 

አቶ ዳውድ ኤርትራ በረሃ በነበሩበት ወቅት እንደተባለው ድርጅቱን አስማምቶ ማእከላዊ አመራር በመስጠት አልተሳካላቸውም። ኦነግ አራት ሆነ። ዳውድ፣ ገላሳ ዲልቦ፣ አባ ነጋና ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመሩዋቸው አራት የኦነግ አካላቶች ለየብቻ መዳከር ጀመሩ። ” ኦነግ ” የሚለውን ብራንድና መለያ በመያዝ ከስሙ ጫፍ ላይ ቅጥያ በማድረግ ሁሉም ራሳቸውን የኦነግ ዓላማ አስፈጻሚ አድርገው በየግል ከነፉ።

በመካከሉ መከፋፈሉ አግባብ እንዳልሆነ ታምኖበት ሰፊ ውይይትና ድርደር ከተደረገ በሁዋላ ሁሉእም ወደ አንድ ተመልሰው አብረው እንዲሰሩ የሚያስችል ስምምነት ላይ ከተደረሰና ሰነድ ተዘጋጅቶ ለፊርማ ከቀረበ በሁዋላ የእርቅ ውህደቱን አቶ ዳውድ በመጨረሻ ሰዓት እንደገፉት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገለጽ የኖረ እውነት ነው። እሳቸውም በወጉ ተጠይቀው ይህን ጉዳይ ሲያስተባብሉ አልተሰማም።

በተስፋ መቁረጥ ይመስላል እነ አቶ ሌንጮ ለታና ዶክተር ዲማ ነገዎ ከገላሳ ዲልቦ ኦነግ ራሳቸውን አግልለው ሌላ ድርጅት በምቋቋም  ከሌሎች በተለይም ከግንቦት ሰባት ጋር ለምሰራት ውህደት ፈጸሙ። በዚህ አካሄድ ሲያዘግሙ ከቆዩ በሁዋላ ለውጡ በአዲስ አበባ እውን ሆነ። የእነ አቶ ሌንጮ ድርጅት ግንቦት ሰባትን ዞር በል ብሎ ጥሎት አዲስ አበባ ገባ። ከግንቦት ሰባት ጋር ተፋታ። 

See also  ስለኔ ፀሐይ እየተቃጠለ በጥላ ያሻግረኛል!!

እንደ እነ አቶ ሌንጮ ሁሉ አቶ ዳውድም አዲስ አበባ ገቡ። ሰራዊታቸውን በትግራይ በኩል ቀይ ወጥ ተጋብዞ እንዲገባ ከነ ስብሃት ነጋ ጋር አመቻችተው ነበርና በተያዘው እቅድ መሰረት ሆነ። ህዝብ የኦሮሞ ፓርቲዎች አንድ ሆነው ይታገላሉ የሚል የቆየ ተስፋ ስለነበረው ተስፋውን በየመድረኩ ያስተጋባ ጀመር። ይህንኑ ተከትሎ እቶ ዳውድ የሚመሩት ኦነግ ከኦፌኮና ጀነራል ከማል ከሚመሩት ኦነግ ጋር አብሮ ለመስራት ተስማማ። የቆየም ቢሆን ደግ የተባለ ውሳኔ ቢሆንም ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶችን ማግለሉ ቅሬታን ፈጠረ። ቆይት ብሎ ከማል ገልቾ ተነስተው እነ ጃዋርን ሳይቀር በአምባ ገንነት ከሰሱ።

ዳውድ ኢብሳ ከኦነግ ሸኔ ጋር ተናበው እነደሚሰሩ በገደምዳሜ፣ አንዳንዴም በፓርቲዎች መድረክ በይፋ ይነገር ጀመር። ቆይቶ ግን የአቶ ዳውድ ኢብሳ ምክትል ዳውድ የሚመሩት ድርጅት ከስራ አስፈሳሚውና ምክር ቤቱ ፍላጎት ውጪ ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ይፋ አደረገ። በዚህ የልዩነት ሂሳብ መሰረት በማስጠንቀቂያ ዳውድን አገደ። እሳቸው የሚመሩት ድርጅት ዳውድ ኢብሳ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሶ በውቅቱ ከታች ያለውን መግለጫ አወጣ ሊንኩን ተጭነው የኦሮምኛና አማርኛ ትርጉም መግለጫውን ያንብቡ  ከታች ያለው ከመግለጫው የተወሰደ ነው

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከድርጅቱ እውቅና ውጪ የኦሮሞን ህዝብ ሲወጉ፣ ሲገሉ እንዲሁም ሲያሰቃዩ ሲገሉ ከነበሩ ክፍሎች / ትህነግ/ ጋር የጎንዮሽ ግንኙነት ሲያደርጉ መቆየታቸው የኦሮሞን ህዝብ እንዳስቀየመ ኦነግ አስታወቀ።  በአደራ ለስድስት ወር የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ድርጅቱን ከማይወጣው ቀውስ ውስጥ እንደከተቱ ጠቅሶ ድርጅቱ እዳሰናበታቸው ይፋ አደረገ።

ዳውድ ኢብሳ ስልጣን ከያዙ በሁዋላ ሶስት የድርጅቱ አንኳር ሃይሎች ተለይተው እንዲወጡ ምክንያት መሆናቸው በአሉታዊ መልኩ ታይቶ ለድርጅቱ ” እውር መሆን” እንደ ዋና ምክንያት በመግለጫው ተመልክቷል። እነ አቶ ሌንጮ፣ እነ አቶ ገላሳ ዲልቦ፣ እነ ጀነራል ከማል ገልቹ ድርጅቱን ሲለዩ ዋና ዋና የሚባሉትን መስራቾች ይዘው በመውጣታቸው ድርጅቱ ከቀን ወደ ቀን እየተንኮታኮተ ሄዷል።

ኦነግን ለሁለት አስርት ዓመታት ሲመሩ የነበሩት ዳውድ ኢብሳ የወቅቱ ስራ አስፈሳሚ በአደራ ለስድስት ወር በሰጣቸው ጊዜያዊ ሃላፊነት መሰረት አስፈላጊውን ስብሰባ አካሂደው ድርጅቱ ከገባበት ቀውስ ከማላቀቅ ይልቅ ኤርትራ ውስጥ ከትመው ይህ ነው የማይባል በደል ሲፈጽሙ እንደኖሩ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። በርካታ ወንጀሎች እንደተፈጸመም ሰላባ ነን ያሉ ሲናገሩ ቆይተዋል።

ከሁሉም በላይ ግን በመግለጫው ከተጠቀሰው ሃሳብ ሰፊ መነጋገሪያ የሆነው ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ከገቡ በሁዋላ ጀመሩት የተባለው የጎንዮሽ ግንኙነት ነው። ቃል በቃል አይጠቅስ እንጂ መግለጫው የኦሮሞን ሕዝብና ኦነግን ሲወጉ፣ ሲያሰቃዩ፣ ሲያስሩና ሲገሉ ከነበሩ ወገኖች ጋር አቶ ዳውድ ከስራ አስፈጻሚውም ሆን ከድርጅቱ መርህ ውጪ ግንኙነት መፈጠራቸው ተወግዟል። አቶ ዳውድ ህትህነግ ጋር መገናነታቸውን ስም ጠቅሶ ባይኮንንም መግለቻው ይህ የአቶ ዳውድ ተግባር የኦሮሞን ህዝብ አሳዝኗል። አንገትም አስደፍቷል። 

See also  “ኢትዮጵያውያን ህወሀት ከሚለው ስም ጋር ያለንን ደመኝነት አይሁዳውያኑ ናዚን ለመጥላት የሄዱትን እርቀት ያክል መጓዝ ይገባናል!”

ኦነግ ዳውድ ኢብሳ ከትህነግ ጋር በጎን የመሰረቱት ግንኙነት የኦሮሞን ሕዝብ አሳዝኗል አለ፤ እንዳሰናበታቸው አስታወቀ

የኦነግ ሸኔ ምክትል ሊቀመንበር አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ – የዳውድ ኢብሳ የመሪነት እጣፈንታ ሊያከትም? በሚል ርዕስ ቀደም ሲል አቶ አራርሳ ቢቂላን በመጠቅስ የድርጅቱ መካከል ያለው ግንኙነት አንዱ ሌላውን እስከማባረር የዘለበትን አግባብ ሃላፊኦውችን በመጥቀስ ተዘግቧል። 

እንዲህ ሲነከባለል የቆየው የኦነግ ሸኔ ችግር በርካቶች እንደሚሉት ሚዲያዎችም የሚሸፋፍኑትና አንድ ወገን ደግፈው ሲከላከሉት የቆየ ጉዳይ ነው። አቶ ዳውድ አዲስ አበባ በገቡ ማግስት ጀምሮ ጠቅላላ ጉቤ እንዲያደርጉ የሚወተውቱ የበታች አመራሮች ነበር። ድርጅቱ የኦሮሞን ሕዝብ እወክላለሁ እንደማለቱ የስራ አስፈጻሚው ስብጥር ቅሬታ የሚነሳበትም እንደነበር ቅሬታ አቅራቢዎች ያነሳሉ። አቶ ዳውድ ግን ለዚህ ምላሽ የሰጡ አይመልም። ያም ሆኖ ግን በራሱ ጊዜ ክፍፍሉ ሲፈነዳ ምርጫ ቦርድ ጋር በደረሰ የባለቤትነት ጥያቄ ሳቢያ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ታዟል።

ጉቤውን ለማካሄድ የአቶ አራርሳ ወገን ሲስማማ አቶ ዳውድ ለምን እንዳልተቀበሉት ግልጽ አይደለም። ወይም እሳቸው ራሳቸው ግልጽ አላደረጉትም። አቶ ዳውድ የጤና ችግር ያለባቸው፣ ሰፊ ክልል ላይ የሚነቃነቅ ፓርቲ ለመምራት የድሜም ጫናም ያለባቸውና በአስተዳደርም ክፍተት ስላለባቸው ድርጅቱ አዲስ አበባ ሲገባ በክብር ለተተኪ ወጣቶች አስረክበው ታሪክ ሊሰሩ ይገባ እንደነበር በቅርብ የሚያውቋቸው ምክር እንደለገሱ ሳይቀር ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል።

ሁሉም ሳይሆን በኦሮሚያ ተፎካካሪ ሊሆን ይችላል የተባለው ኦነግ እንደለመደበት ባለመስማማት ቀጥሏል፣ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ ችግሩን ሊፈታ ባለመቻሉ ከምርጫው ለመሰናበት አፋፍ ላይ መሆኑ አንደኛው ክፋይ ሲናገር፣ አቶ ዳውድ አባሎቻቸው በመታሰራቸው ለምርጫ የሚያቀርቡት እጩ እንደሌላቸው መግለጻቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል። የታሰሩት አባላት ጠመንጃ ካነሳው ሃይል ጋር ግንኙነት ያላቸውና የተያዙ ናቸው ስለመባሉ በዜናው የትብራራ ነገር የለም።

አቶ ዳውድ አባሎቻቸው መታሰራቸውን ብልጽግና ላይ ጣታቸውን ቀስረው ሲናገሩ አባላትን ከማስመዘገብና ወደ ውድድር ከመግባታቸው በፊት በድርጅታቸው ውስጥ ያለውን የመከፈል ጣጣ ለምን መፍታት እንዳልተቻለም አላብራሩምልል። ከሳቸው ይልቅ ሌላኛው ወገን   “አቶ ዳውድ መፍትሄ የሚባሉትን ሁሉ ዘግተዋል” ሲል ችግሩን ወደ እሳቸው ያዞራል። እንደውም ጠቅላላ ጉቤኤ አድርጎ ችግሩን ለመፍታት አቶ ዳውድ ፍላጎት እንደሌላቸው የሚጠቁመው ሌላኛው ወገን የምርጫ መሳተፉ ጉዳይ እንዳከተመ ይሰማዋል። ጉባኤ ማካሄድ ለአቶ ዳውድ ለምን ዳገት እንደሆነባችውን ሊገባው እንዳልቻለ ይናገራል። ያም ሆን ይህ የኦነግ ወይም ኦነግ ሸኔ ጉዳይ ለጊዜው እዚህ ላይ ደርሷል።

ኦፌኮ ሌላው የብልጽግና ተፎካካሪ ቢሆንም አባልቱ በተለይም አቶ ጃዋርና አቶ በቀለ ገርባ መታሰራቸው ምርጫውን ለመሳተፍ እንደሚያዳግተው አስታውቋል። ያም ሆኖ ግን ምርጫውን አልሳተፍም አላለም። አባላቱ በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውና ህይወታቸው አንድ ነገር ቢሆን በታሪክ እንደሚያስጠይቅ የገለጸው ኦፌኮ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ አሳስቧል። ይሁን እንጂ ሰዎቹ ስለታሰሩበት ጉዳይና ስለተጎጂዎች የፍትህ መብት በተደጋጋሚ መግለጫ ሲያወጣ ያለው ነገር የለም።

See also  መንግሥታችን ሆይ! ስምህን የተሸከሙ ተቋማትን ፈትሽልን -ዳግላስ ጴጥሮስ

ምዕራብ ሸዋ በተለይም አምቦና አካባቢው ላይ ታላቅ ስም የተለከሉት ፕሮፌሰር መረራ የትንታጉ አርቲስት ሃጫሉ አስከሬን የተንከራተተበትና ከቤተሰቦቹ ፈቃድ ውጪ ተነጥቆ ላለተፈለገ ተግባር እንዲውል ሲደረግ ምንም አለማለታቸው አግባብ እንዳልሆነ በርካቶች ተችተዋቸዋል። ተደጋጋሚ የግድያ ማስፈራሪያ ሲደርሰው የነበረው አርቲስት ሃጫሉ መገደሉን ተከትሎ በሻሸመኔ፣ በመቂ፣ በዝዋይ፣ በአርሲ… የማህበራዊ ሚዲያ ጥሪን ተከትሎ የተፈጸመው ወንጀል ማን ከጀርባ ሆኖ እንዳቀጣጠለው፣ አዲስ አበባ ላይ የተሞከረውና የከሸፈው የርስ በርስ ግጭት የማን ስሌት እንደሆነ ኢፌኮ ዛሬ ድረስ ግልጽ አውጥቶ አቋሙን አላሰማም።

በርካታ የኦሮሞ ልጆችን ጨምሮ የሞቱበት፣ ከሞትም በላይ ገድያው አሰቃቂነቱ አነጋገሪ በሆነበት፣ ነፈሰጡር ጨምሮ ልጅ አባቱ ፊቱ ሲገደል እንዲያይ የተደረገበት አግባ እንደነበር፣ ከፍተኛ ንብረት መውደሙና በርካቶች መፈናቀላቸው እየታወቀ ኦፌኮ ፍትህ ሲጠይቅ ይህንን ጉዳይ እንዴት አይቶት እንደሆነ የጠየቁ ሚዲያዎችም የሉም። ፍትህ ተጓድሎ ሊጠየቅ እንደማይገባ የሚያምኑ እንደሚሉት ያለ አግባብ የታሰሩ ካሉ እንዲፈቱ፣ በጉዳዩ እጃቸው ያለበት ደግሞ በህግ እንዲጠየቁ ማድረግ ህጋዊ አካሄድ በመሆኑ ኦፌኮ እይታውን አጥርቶ ወደ ምርጫ ቢገባ እንደሚሻለው ይመክራሉ።

ሲጀመር ኦፌኮ በምያታወቅበት የማክረር ፖለቲካ ገብቶ እሱ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ” አማራ ያገባችሁ ፍቱ” የሚል መመሪያ ሲሰጥ የሰሙ በርካቶች አዝነዋል። ምን አልባትም ኦፌኮ ከዚያ በሁዋላ ብዙ ነገሩን እንዳጣ ግምታቸውን የሚያስቀምጡ ጥቂት አይደሉም። ይህ ሁሉ ቀርቶ  የታሰሩት ቁልፍ የኦፌኮ አመራሮች ስለምን ፍርድ ቤት እምነት ክህደት ፈጽመው የፍርድ ሂደታቸውን ከማፋጠን ይልቅ እንዲጓተት ያድርጋሉ የሚለው ጥያቄ የህግ ባለሙያዎች ዘንዳ በስፋት መነጋገሪያ ሆኗል። ጉዳዩ ከአገር ውጭም ባሉ ዲፕሎማቶች ዘንድ ተመሳሳይ ሆኗል።

መንግስት የህግ አግባቡ ካላለቀ ጣልቃ መግባት እንደማይችል በግልጽ ተናግሯል። ከዛሬ ወር በፊት በፊት እምነት ክህደት ምህላ ቢያደርጉ ኖሮ ዛሬ በዋስ ወይም በክሱ ጭብጥ ላይ የሚደረገው ክርከር ብዙ ርቀት ሊሄድ ይችል እንደነበር አሁንም ባለሙያዎች ያናገራል። በተደጋጋሚ በማይሆኑ ምክንያቶች ክስን የማዘግየት አካሄድ ሲስተዋል እንደነበር የገለጹት የህግ ባለሙያዎች በዚህ አግባብ ስህተት እንደተሰራ ያምናሉ።

ምንም ተባለ ምን በኦሮሚያ ምርጫውን ከሚገጥሙት ጋር ተፎካክሮ ለማሸነፍ ስራ የጀመረው ብልጽግና ብቁ ተፎካካሪዎች ይኖሩታል አይኖሩትም የሚለው ጉዳይ ውሎ አድሮ የሚታይ ቢሆንም ምርጫው ሊረበሽ ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው ሃይሎች ድምጽ እየተሰማ ነው።

ብልጽግና ግን የምርጫ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መንግስት ያለ ችግር እንዲከናወን ጊዜያዊ የምርቻ ጉዳዮችን የሚያዩ ችሎቶች፣ ፖሊስና ልዩ የጸጥታ መዋቅር፣ ከሁሉም በላይ አስተማማኝ ኔትዎርክ እንዳለው እየገለጸ ነው።

በኦሮሚያ እየቀረበ ያለው የፍትህ ጥያቄ ግልጽና እንደማንን አካቶ እነማንን እንደሚገፋ በውል አይታወቅም። ምርጫው ግን እየደረሰ ነው!!

    Leave a Reply