“ … ከገዛ ሀገሩ ለተባረረው ሰራዊታችን ከለላ የሆነው ፣ ዛሬ ህወሃታዊያን ባዕድ ሃገር የሚሏት ኤርትራ አልነበረችምን ?”

በዲጅታል ወያኔዎች ጫጫታ እውነት አትደበዝዝም !

“ከሰማይ በታች እኛን የሚያሸንፍ ምድራዊ ሃይል የለም” በሚል እብሪት ልባቸው ያበጠው ህወሃታዊያን የራሳቸው ና የህዝቡ የዘመናት አጋራቸውን የሰሜን ዕዝ የሰራዊት አባላትን የወለደችውን እንደምትበላ ድመት በተኛበት በአሰቃቂ ሁኔታ ረሸኑ ፡፡

የሀገርን ክብር በሚያዋርድ መልኩ የክብር ልብሱን አስወልቀው ከክልላችን ውጡ ብለው ወደ ባዕድ ሃገር አሰደዱት ፣ ሴት ወታደሮችን ጡት እንዳልቆረጡና ከሰብዓዊ ፍጡር የማይጠበቅ የማይጠበቅ እየፈጸሙባቸውና እያሰቃዩ እንዳልገደሉ ፣ ሬሳቸው ላይ እምበር ተጋዳላይ እንዳልጨፋሩ ፣ በተኙበት አፍነው ይዘው አሰልፈው በሲኖትራክ እንዳልጨፈለቁ ፣ ከፍተኛ ጀነራል መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ አባላትን አግተው ያለ ምግብ ውሃ በእግር እያሰጓዙ እንዳላሰቃዩ በዚህም በርሃብና በጥም በርካቶች እንዲሞቱ እንዳላደረጉ ፣ ማይካድራ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው የዘር ማጥፋት እንዳልፋፀሙ ሁሉ ፣ በንቀትና በትዕቢት ተነፋፍተው በደንጎላ ኮሎኔል ማራኪ የውሸትና ባረጀ ባፋጀ ስልት የጀመሩት ጦርነት ፣ በቆራጥ ኢትዮጵያዊያን መስዋዕትነት ድባቅ ሲመቱ ፣ የጦርነት ሊቆች ነን ባዮች ግብዞቹም በለኮሱት እሳት ሲፈጁ ዲጅታል ወያኔዎች ሌላ ዘፋን ይዘው ብቅ አሉና አለምን ማደናገር ጀመሩ።

ትግራይ ውስጥ ሰብአዊ መብት እየተጣሰ ነው ፣ ሴቶች እየተደፈሩ ነው ፣ ንብረት በኤርትራ ወታደሮች እየተዘረፈ ነው ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይ ህዝብን በርሃብ እየቀጣ ነው ፣ የሃገር ሉአላዊነት ተደፍሯል… የሚሉና ፣ ምድር ላይ ካለው እውነት የሚጣረሱ ክሶችን በሶሻል ሚዲያና በውጭ ሃገር የመገናኛ አውታሮች የሃሰት ፕሮፖጋንዳቸውን ማናፋሱን ተያይዘውታል።

ምክኒያቱም ዛሬ ትግራይ ውስጥ ስለተፈፀመውና መቸም ከልባችን ከማይጠፋው ግፍና መከራ ከጨፈጨፋቸው ወታደሮች ህይወት ይልቅ ጦርነቱ ያስከተለው ማህበራዊ ቀውስ እንጅ ፣ የቀውሱ ጠንሳሽና ፈፃሚ የሆነውን ህወሃት የፈፀመው አሰቃቂ ግፍ በህወሃት ጀሌዎች ዘንድ ይሁን በአለም አቀፍ ሚዲያዎችም ሲወገዝም ሲወቀስም አንሰማም።

ትግራይ ውስጥ በግፍ የተጨፈጨፉትን የሰሜን ዕዝ አባላትን ክብር የጠበቁት ልብስና የእግዜር ውሃ ያቀመሱት ኤርትራዊያን ወታደሮችና እናቶች ናቸው ወይስ… ?

የህወሃታዊያን ሌላው ድንቁርና የባዕድ ሃገር ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ተዳፍራ ወታደሮቿን ትግራይ ውስጥ አስገብታለች የሚል ክስ ነው አስገብታለች አላስገባችም የሚለውን እውነት ለመንግስት እንተወውና ፣ አስገብታ ቢሆንስ እንደ ህወሃትና ባንዳዎች ክህደትና ሴራ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ኢትዮጵያ ከሶሪያም የባሰች የፈረሰ ሃገር ትሆን እንደነበር ግልፅ ነው ፡፡

ከራሱ ሃገር እንደባዕድ ተቆጥሮ የሗሊት ታስሮ ከተገደለው ፣ ጡታቸው ተቆርጦ ተሰቃይተው ከሞቱት ፣ በድንጋይ እየተወገረ ልብሱ ሳይቀር እየተዘረፈ ከገዛ ሀገሩ ለተባረረው ሰራዊታችን ከለላ የሆነው ፣ ዛሬ ህወሃታዊያን ባዕድ ሃገር የሚሏት ኤርትራ አልነበረችምን ?

እውነት እንነጋገር ከተባለ በወቅቱ ጁንታዎቹ ሰራዊታችንን ከሃገራችን ውጡ ብለው ሲያባርሩ የተቀበለው የኤርትራ ህዝብ ነው ባዕድ ወይስ ህወሃታዊያን?

ትግራይ ውስጥ በግፍ የተጨፈጨፉትን የሰሜን ዕዝ አባላትን ክብር የጠበቁት ልብስና የእግዜር ውሃ ያቀመሱት ኤርትራዊያን ወታደሮችና እናቶች ናቸው ወይስ… ?

እኔም ይሄን እላለሁ ፣ ህወሃታውያን ሆይ በጦር ሜዳ ላይ ያጣችሁትን ድልና ላይመለሱ ያሸለቡትን አለቆቻችሁን በፌስቡክና በዮቲዮብ ጋጋታ ላትመልሱት ፣ በውሸት ጫጫታና አስፖልት ላይ በመንከባለል የሚፈታ የትግራይ ህዝብ ችግር የለም ፡፡

መጀመሪያ አጎቶቻቹሁ የፈፀሙትን ወራዳ ተግባር አውግዙ ፡፡ በናንተ ዘመዶችና ሃሺሻም ታጣቂዎች የተጨፈጨፉ ወታደሮችን ህይወት አስቡ ፡፡ ሃገራችን የገባችበት ቅርቃር የሽማግሌ ህወሃታዊያን ሴራ መሆኑን እመኑ ፡፡

የኤርትራ ወታደሮች ሉአላዊነትን ተዳፍረው ትግራይ ውስጥ ገብተዋል ከማለታችሁ በፊት ዳር ድንበር ጠባቂ ወታደሮችን ከጀርባቸው የወጋውን ከሃዲ በአደባባይ ባንዳ በሉት፡፡

ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን የካደውን የበደለውን የህወሃት የጥፋት ሃይል እናንተን እንደማይወክል በተግባር አሳዩ ፡፡ ያኔ የናንተ ህመም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ህመም ይሆናል።

ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰራዊታችንን በመደገፍ የጁንታውን ግብአተ መሬት እንዳፋጠነው ሁሉ ፣ አሁን ደግሞ የዲጅታል ወያኔን የውሽት ፕሮፖጋንዳ በሃገራችንና በሰራዊታችን ላይ የተከፈተውን ዘመቻ እያጋለጥን በጁንታው የተፈፀሙ ግፎችን አጉልቶ ማውጣት ይጠበቅበናል።

የህወሃት ጄሌ ሲመራው ህዝባዊ የሚሆን ፣ ሌላው ሲመራው ደግሞ ፀረ ህዝብ የሚሆን ሰራዊት የለንም። ሠራዊታችን የኢትዮጵያ ሠራዊት ነውና !

ዳንኤል አወል. Defense minister Fb

You may also like...

Leave a Reply