እናት ፓርቲ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ከ50 በላይ ሴት እጩዎች ማቅረቡን አስታወቀ

ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን የሚፈልጉ ብቃት ያላቸው ሴቶችም እንዲቀላቀሏቸው ፓርቲው ጥሪ አቀርቧል።

የእናት ተፎካካሪ ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው የፓርቲያቸውን አላማዎችንና ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የሚደገውን ዝግጅት በተመለተ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም:- ለመሆኑ እናት ተፎካካሪ ፓርቲ ፓርቲ ሆኖ ሲመሰረት፤ በሀገራችን ከሚገኙት በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩ የሚያደርገው ምን ምን አላማዎችን ይዟል?

ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው :- “ድምጽ ያላገኙ ወገኖችን ወደ ፖለቲካው መድረክ በማምጣት በሀገራችን በተመራጭነትም በድምጽ ሰጭነትም የነቃ ተሳትፎ እንዲኖረው በማስቸቻና የራሱን እጣ ፈንታ በራሱ እንዲወስን የሚችልበትን እድል ያመቻቻል፡፡”

ኢትዮ ኤፍ ኤም :- ተፎካካሪ ፓርቲው ስያሜው ወይም ተመሳሌት ያደረገው እናትን ወይም ሴትን እንደመሆኑ መጠን በፓርቲው አወቀቃር የሴቶች ተሳትፎ ምን ያክል ይሆን?

ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው:- ”አሁንም ፓርቲያንን ልትመራ የምትችል ከዛም አልፎ ለሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የምትችል ሴት እጩ ተወዳዳሪ ማግኘት ከቻልን በእጩነት ማሳታፍ እንፈልጋለን፡፡ ምንም እንኳን በሀገራችን የሴቶች ብቻም ሳይሆን በሁሉም ጾታዎች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ውስንነቶች ቢኖርም ሴት እጩዎችን ለማቅረብ እየሰራን እንገኛለን፡፡”

ኢትዮ ኤፍ ኤም :- ፓርቲያቸው አዲስ አበባን በተመለከት ምን አቋም ይዟል ?

ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው :- ”አዲስ አበባ የከተማ መንግስት እንደመሆኗ መጠን፤ አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የራሱን መሪ ከንቲባ እራሱ በቀጥታ በመረጠው ሃላፊ መመራት አለባት፡፡ ይህም ደግሞ ህገ መንግስታዊ መብቱ ሊሆን ይገባል፡፡”

ኢትዮ ኤፍ ኤም :- ፓርቲው ለቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ለመወዳደር የአሁን ዝግጅቱ ምን ይመስላል?

ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው :- “የክልልና የፌደራል ምክር ቤቶችን መቀመጫዎችን ለማግኘት አስፋለጊ የሚባሉ ነገሮችን እያደረግን እንገኛለን፡፡ቀሪ ስራዎች ቢኖሩንም አብዛኛዎችን ስራዎቻችንን አጠናቀናል፡፡ በቻልነው አቅም በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ለመወዳደር እየሠራን ነው ያለነው፡፡”

ኢትዮ ኤፍ ኤም :- ምርጫ ቦርድ ያወጣው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን እንዴት አያችሁት?

ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው:- የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ በምርጫ ቦርድ የተሰጣቸው የጊዜ ሰሌዳ በቂ ነው ብለን እናምናለን።

See also  ኢትዮጵያ የ "50 ሚሊዮን የአፍሪካ ሴቶች ይናገሩ" ፕሮጀክትን ውጤታማ በማድረግ የመሪነት ሚናዋን ትወጣለች

ኢትዮ ኤፍ ኤም :- በዘንድሮው ምርጫ ከሌሎች አቻ ፓርቲዎች ጋር በጋራ የመወዳደር እቅድ አላችሁ?

ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው:- ከሌሎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በውህደት የመስራት ፍላጎት አለን፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም :- የእናት ተፎካካሪ ፓርቲን ለመደገፍ ወይም አባል መሆን ለሚፈልጉ ሰዎች፤ አድራሻችሁ የት ነው?

ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው:- የፓርቲያችን ዋና ቢሮ አዲስ አበባ 4 ኪሎ ሲሆን በክፍለ ሀገር ደግሞ ቅርንጫፍ ቢሮዎች አሉን ማንኛውም ለአገር የሚጠቅም ሀሳብ ያለው/ያላት ሁሉ ፓርቲያችንን መቀላቀል ይቻላል፡፡

በጅብሪል ሙሐመድ
የካቲት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

Leave a Reply