ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ስራ የተመደበን ገንዘብ ያለአግባብ ጥቅም ላይ ያዋሉ ግለሰቦች ተቀጡ

NEWS

በምዕራብ ጎንደር ዞን ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ተግባር የተመደበን ገንዘብ ያለአግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረጉ ሶስት የስራ ሀላፊዎች እስከ ስድስት አመት በሚደርስ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አስተባባሪ አቶ አበበ ማስሬ ለኢዜአ እንደገለፁት÷ ግለሰቦቹ ያላቸውን የመንግስት ሃላፊነት በመጠቀም ሙስና በመፈፀማቸው ተቀጥተዋል።

ግለሰቦቹ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከክልል የተመደበ ገንዘብ ያለአግባብ እንዲባክን በማድረጋቸው ፍርድ ቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት ግለሰቦቹ ላይ የቅጣት ወሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል።

የቅጣት ውሳኔው የተላለፈባቸው 1ኛ ተከሳሽ የመተማ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ በቃሉ እውነቱ፣ 2ኛ ተከሳሽ የወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አደና ፀጋና 3ኛ ተከሳሽ አፈርቅ ሞላ የወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽህፈት ቤት የሂሳብ ባለሙያ ናቸው።

አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ሀላፊነታቸውን በመጠቀም ለኮሮና መከላከል ተግባር ለተመደበ ገንዘብ ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት የመንግስት ሰራተኛ ላልሆኑ ሰዎች 448 ሺህ ብር በደመወዝ መልክ እንዲከፈል ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ግለሰቦቹ የፈጸሙት ወንጀል በሰውና በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው በስድስት አመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር እንዲቀጡ መደረጉን አመልክተዋል።

በተመሳሳይ 3ኛው ተከሳሽ የኮሮናቫይረስ መከላከል ግብዓት የግዥ አፈፃፀም ህግ ባልተከተለ መልኩ 230 ሺህ ብር የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረጋቸው በአራት ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራትና በ1 ሺህ ብር እንዲቀጡ መደረጉን አቶ አበበ ገልጸዋል።. Via FBC

Related posts:

አማራ ክልል የሕግ ማከበር ዘመቻውን በሚያስተጓጉሉ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቀ፤ "ዘመቻው በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል"
አብይ አሕመድ "ጠላትም፣ ባንዳም ይወቅ" ሲሉ አስተማማኝ ሰራዊት መግንባቱን አስታወቁ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ

Leave a Reply