በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ሆኗል – ጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሣ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 615 ሰዎች በፅኑ ዕሙማን መርጃ ክፍል ውስጥ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የ29 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ማለፉንም አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ የቫይረሱ ስርጭት እየሠፋ፣ በቫይረሱ የመያዝና የመሞት ምጣኔም ከመቸውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በዚህ ሳቢያም በሃገሪቱ ካለው የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ ማሽን ውስንነት ጋር ተያይዞ አሁን ላይ በህክምና ተቋማት ውስጥ የመተንፈሻ መሳሪያዎች ለህሙማን በወረፋ እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
በዋናነት መዘናጋትና ቫይረሱን አቅልሎ ማየት፣ በህብረተሰቡ ውስጥ የቫይረስ መከላከል ትግበራው መቀዛቀዝ እና ፍጹም መዘናጋት ስለሚስተዋል ወረርሽኙ አሁንም ስጋት ሆኖ ቀጥሏልም ነው ያሉት፡፡

ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሕይወቱን መታደግ አለበት ያሉት ዶክተር ተገኔ፥ አመራሩም ርቀትን በመጠበቅ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም እጅን በመታጠብ በዋናነት ለራሱና ለቤተሰቡ እንዲሁም ለሚያገለግለው ህብረተሰብ አርዓያ ሆኖ ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡

መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትም ያለመሠላቸት ለተገልጋዮች አስፈላጊ ግብአቶችን በማቅረብና የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ሊደግፉ እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡

የሚዲያ ተቋማትም ህዝቡን በማስተማር፣ በማስጠንቀቅ፣ በተለያዩ የቫይረሱ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግና በማስተማር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)

Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply