1) አልሞትኩም ለማለት በትግራይ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሽብር ድርጊት መፈጸም። ለድርጊቱ ሀላፊነት መውሰድ።

2) የውጭ አገር መገናኛ ብዙሀንን እና ማህበራዊ ትስስር አውታሮችን በመጠቀም “አሁንም አለን” የሚል የፕሮፓጋንዳና የሀሰት መረጃ አጠናክሮ ማሰራጨት። የዓለም አቀፍ ትኩረትን ለማግኘት መጣር።

3) የክልሉን እና በማእከላዊ መንግሥት ሥር የሚተዳደሩትን ሚዲያ በተለየ ስልት በመጠቀም የዓላማቸው ማራመጃ ለማድረግ መሞከር።

4) የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ሴራዎችን በማራመድ ሕዝቡ መንግሥትን እንዲያማርር፣ ሆን ተብሎ እንደተዘመተበት እንዲሰማው ማድረግ፣ “የቀድሞው ይሻለናል” የሚል ስሜት እንዲያድርበት መሥራት። ይህንንም በፕሮፓጋንዳ ማገዝ።

5) የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሥራዎች እንዳይሳኩ ማጣጣል፣ በሕዝብ ተቀባይነት እንዲያጣ መሥራት፣ መልካም ጥረቶቹን ማክሸፍ፣ ስም ማጠልሸት፣ በአስተዳደሩ ውስጥ ሰርጎ ገቦችን በማስግባት ሴራቸውን ማስፋት።

6) በተለያዩ የክልሉ መንግሥታዊ መዋቅሮች እና ሕዝባዊ አደረጃጀቶች ውስጥ ህዋሶችን በማቋቋም የሴራቸው መጠቀሚያ ማድረግ።

7) በጸጥታ መዋቅሮች ውስጥ ሰርጎ በመግባት ዓላማቸውን ለማሳከት የሚረዱ አካላትን መፍጠር።

8) የፋይናንስ አቅማቸውን ለማጎልበት የሚረዱ የተለያዩ ትስስሮችን መፍጠር። በኢኮኖሚው ውስጥ የጎላ ድርሻ ያላቸውን አቅም፣ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና በማሳተፍ አሻጥር መሥራት።

9) የገጽ ለገጽ ግኑኝነቶችን(Face to face)በማስፋት አሉታዊ ፕሮፓጋንዳን ማሰራጨት።በመሆኑም:-እነዚህ ሥራዎች እጅግ ለተዳከመ እና ለተመታ ሀይል ቀላል ባይሆኑም፣ ሙከራው እና ፍላጎቱ መኖሩ አይቀርም። በአመዛኙ ፍላጎቱ እንጂ የተግባራዊነት ደረጃው ያነሰ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህም ሆኖ፣ ለአሉታዊ ነገሮች ምንም ቀዳዳ ላለመስጠት፤ሕዝብን ከጎን ማሰለፍ፣ ለወጡን በቁርጠኝነት፣ በእምነት እና በፍላጎት ለመምራት ዝግጁነት ያላቸውን አመራሮች ማሰባሰብ፣ ከዚህ በፊት ተጎድተናል በሚል ስሜት ብቻ የተሰባሰቡትን አመራሮችን መፈተሽ፣ ቁርጠኝነት የጎደላቸውን፣ በለውጡ ላይ ጠንካራ እምነት የሌላቸውን፣ ስልጣን ብቻ ፈልገው የመጡትን እና ደካሞችን ደረጃ በደረጃ በሌሎች አመራሮች መተካት፤ ውጤታማ የሆኑትን በተለያየ መንገድ እውቅና መስጠት፣የተጠናከረ የሥራ ግምገማ ሥርአት መዘርጋት፣

የደህንነት እና የጸጥታ ስርአቱን ማጠናከር፣ በዚህም የሕዝቡን ተሳትፎ ማሳደግ፤ አለመዘናጋት፣ የሕዝብን መብት መጠበቅ እና ማስጠበቅ፣ የክልሉም ሆኑ የፌደራል የመገናኛ ብዙሀን የተጠናከረ እና አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ፣ አስፈላጊው የሰው ሀይል፣ የመሣሪያ እና የበጀት ድጋፍ እንዲያገኙ ማገዝ። ሕዝቡ ያልተቋረጠ እና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ መርዳት፣ በለውጡ ላይ ተስፋው እንዲጎለብት ማገዝ፣የጁንታውን ኢሰባዊ እና የዝርፊያ ድርጊት ደግሞ ደጋግሞ ለሕዝብ ማሳወቅ፣ ጁንታው ንጹህ፣ ለሕዝብ አሳቢ እና ተበዳይ መስሎ ያለሀፍረት የሚናገረው ይህ ባለመደረጉ መሆኑን በቅጡ ማወቅ ይገባል! እስከታች ያለውን አስተዳደራዊ፣ የጸጥታና የፍትህ ማዋቅር ማሟላት፣ ሕዝብን የማገልገል ዝግጁነቱንና ጥረቱን በየጊዜው ከሕዝብ ጋር በመሆን እየገመገሙ ማስተካከል።የፌደራል መንግሥትን እንዲሁም የክልሎችን ድጋፍ እና ምልከታን ማጠናከር። ይህን አዎንታዊ ድርሻቸውን የሚወጡበትን ጊዚያዊ አደረጃጀት መፍጠር።

የሕዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ለመለወጥ በተለየ ትኩረት መሥራት። በውጭ አገር የሚካሔደውን ባለብዙ ፈርጅ ሥራ ማጠናከር። በውጭ ያሉ ዜጎችን ተሳትፎ ማጠናከር። በርዝራዥ የጁንታው አባላት እና ዋና ደጋፊዎች ላይ የሚወሰደውን ሕጋዊ እርምጃ ያለመዘናጋት መቀጠል፤ አመጽን እና ሽብርን የመረጡትን እና በዚህ ድርጊት የተሰማሩትን ብቻ ለይቶ በአሸባሪነት መፈረጅ ተገቢ ሊሆን ይችላል!!!

አስተያየቱ የጸሃፊው ብቻ ነው via – Berhanu Assefa

Leave a Reply