በለዘብተኛ አቋማቸው የተነሳ – “ሳይደመሰሱ የቆዩት የስግብግብ ጁንታ አመራሮች ነፍስም እንደ ወፏ ሁሉ በእጃችን መዳፍ ውስጥ መሆኑን እኛ እንደ እናት እናውቀዋለን “

” ይገርማል” አሉ  ልብ እያወቀ እንዲሉ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመረጃና የደህንነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ” ይገርማል ” ያሉት ሰሞኑንን የተሰራጨውን ዜና በማስታወስ ነው። ” አንዳንዶችም በለዘብተኛ አቋማቸው ከመሞት መሰንበት ስለሚሻል በነፍስ ብንይዛቸው ይሻላል በሚል መታገሳችንን ልቦናቸው እያወቀ በደሀው ህዝብ የመኖር ዋስትና ላይ አደገኛ ቁማር መጫወት ጀመሩ”  ብለዋል። አክለውም  ” የቀሩት የስግብግብ ጁንታ አመራሮች ነፍስም እንደ ወፏ ሁሉ በእጃችን መዳፍ ውስጥ መሆኑን እኛ እንደ እናት እናውቀዋለን “

” ጭራሽ የካቲት ፩፩ መቀሌ እናከብራለን ብለው ሞኞችን ለማሞኘት ሞከሩ” ሲሉ የሰሞኑንን የትህነግ ሰዎች ዜና ያስታወሱት አቶ ተመስገን፣ ” አንዳንዶች እንደ ቴፕ ሪከርደር የገባላቸውን ካሴት የሚያጫውቱ በመሆናቸው ምክንያት ” ሊሆን የማይችል ጉዳይን በመደጋገም በደሃው ሕዝብ ላይ ቁማር ጨዋታ መጀመሩን ነው ያመለከቱት። ያስታወቁት።

በዚሁ ስብከታቸው ማለታቸው ነው ” ጭራሽ የካቲትት አስራ አንድን መቀሌ ላይ እናከብራለን ብለው ሞኞችን ለማሞኘት ሞከሩ” በማለት ስብከቱን የሞኞች፣ ስብከቱን ተቀብለው ደሃው ህዝብ ላይ የሚጭኑትም ሞኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

” አንዳንዶችም በለዘብተኛ አቋማቸው ከመሞት መሰንበት ስለሚሻል በነፍስ ብንይዛቸው ይሻላል በሚል መታገሳችንን ልቦናቸው እያወቀ በደሀው ህዝብ የመኖር ዋስትና ላይ አደገኛ ቁማር መጫወት ጀመሩ

አማራ ክልልን በማስተንፈስና አንጻራዊ ሰላም በማስፈን የሚታወቁት አቶ ተመስገን በፌስ ቡክ ገጻቸው “ራስ ሳይጠና ጉተና … የማያድግ ልጅ ከእናቱ ጀርባ ላይ ታዝሎ ያፉጫል” በሚል ርዕስ እመዳፍ ውስጥ እንደገባችው ወፍ ምሳሌ ” የቀሩት የስግብግብ ጁንታ አመራሮች ነፍስም እንደ ወፏ ሁሉ በእጃችን መዳፍ ውስጥ መሆኑን እኛ እንደ እናት እናውቀዋለን ” ሲሉ በተፈለገ ሰዓት ልክ እጅ መዳፍ ውስጥ እንዳለች ወፍ መጨፍለቅ እንደሚቻል ተናግረዋል። ይህ ያልሆነው ግን “አንዳንዶች” ያሉዋቸው ከነበራቸው ለዘብተኛ አቋም አንጻር ከመኖር መሰንበት እንዲሉ በህይወት እንዲያዙ ከነበረው ፍላጎት አንጻር መሆኑንን አመልክተዋል።

አቶ ጌታቸው እጉድጓድ ውስጥ ሆነው ድምጻቸውን ካሰሙ በሁዋላ ” የካቲት 11 መቀሌ ላይ ይከበራል” የሚል መፈክር በስፋት ተደምጦ ነበር። አቶ ጌታቸው ራሳቸውም ቢሆኑ እርስ በርስ በሚቃረን መልኩ አንዴ መልሶ ማጥቃት እንደሚጀመሩ፣ ተመልሰው ደግሞ ” አንቸኩልም” ሲሉ ተደምጠው ነበር። አንድ መቶ ሺህ ሰራዊት መደምሰሳቸውን፣ ነገር ግን አንድ መቶ ሺህ ሰራዊት ደምስሰው ዋሻ ውስጥ መሆናቸው ሰሚውን ግራ ባጋባበት ወቅት አቶ ተመስገን ” ለዘበተኛ አቋም ላላቸው ሲባል” ሲሉ ያስነበቡት ጽሁፍ እንደ አንድ ከፍተኛ የደህንነት መሪ ጠንካራና የማያዳግም እርምጃ እንዳለ የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል።

  ” የቀሩት የስግብግብ ጁንታ አመራሮች ነፍስም እንደ ወፏ ሁሉ በእጃችን መዳፍ ውስጥ መሆኑን እኛ እንደ እናት እናውቀዋለን “

” ሁሉንም በንቃት እየተከታተልን ነው” በማለት ስለ ሱዳን ወረራ የከረረ ሃሳብ የሰነዘሩት አቶ ተመስገን ” የአባቶቻችንን ብቻ ሳይሆን የእኛን ክንድም የቀመሱ፣ በለውጥ መሪያችን ድጋፍና ጥረት ከአሸባሪነታቸው ችንካር የተላቀቁ፣ በውስጥ ያልተሳካላቸው፣ በውጭም በሀገራችን ድጋፍ የአይን ጉድፋቸው የተጠረገላቸው ጉዶች…” ነው ያሉዋቸው። አያይዘውም ” ሁሉንም በንቃት እየተከታተልን ነው። ጥንቃቄያችን እና ትዕግስታችን ለንፁሀን ዜጎች ነው። ቀይ መስመሩ ታልፎም የምንታገሰው ከፍርሀትና አቅም እጦት ሳይሆን ለንፁሀን ህዝቦች ካለን ክብር ብቻ ነው። አልያማ እኛ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያውያን ልጆች ነን። መቼ መነሳት እንዳለብን እናውቃለን። ከተነሳን ደግሞ በነቋሪዎች ፍላጎትና ዕቅድ ሳይሆን በራሳችን ነው” ሲሉ እመዳፍ ውስጥ እንዳለችው ወፍ ለቆ የማብረሩም ሆነ የመጨፍለቁ አማራጭ እጃችን ላይ እንደሆነ አምረው አስታውቀዋል።

See also  ትህነግ ከትግራይ አስተዳደር ጋር መሳሪያ አስረክቦና ጦሩን በትኖ እንዲደራደር ታስቧል፤ መንግስ የተረፈውን ሃይል ሊያጸዳ ነው

ሙሉ ሃሳባቸው ከፌስ ቡክ ገጻቸው የተወሰደ

 “ራስ ሳይጠና ጉተና … የማያድግ ልጅ ከእናቱ ጀርባ ላይ ታዝሎ ያፉጫል” ተመስገን ጥሩነህ 

ከላይ የተጠቀሱት አባባሎች የአበው ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ናቸው። ራስ ሳይጠና ጉተና ማለት ራስን መሸከም በማያስችል ሁኔታ ሌሎች ግዝልዛል ጌጣጌጦች በአናት ላይ ደራርቦ ለመሸከም መሞከር ለራስ ህልውና አደገኛ መሆኑን አመላካች ነው። ቅድሚያ የራስን ደህንነት፣ ህልውና፣ የመኖር ዋስትና ሳያረጋግጡ ሌሎች ድሪቶዎችን መከማመር የመኖር ተስፋን እንደማጨለም ይቆጠራል እንደማለት ነው። አንዳንዴ ገደል አፋፍ ላይ ቆሞ ትልቅ ቋጥኝ ከቆምንበት የገደል አፋፍ በላይ ከፍታ ነጥብ ላይ ሆኖ ቋጥኙን ለማንከባለል የሚታገልን አካል እንደ መርዳት ይቆጠራል። የምንረዳው ራሳችንን ለመጥፋት ነው ማለት ነው። እኛ ገደል አፋፍ ላይ ቆመን ትልቁ ቋጥኝ ተንከባሎ እኛንው ወደ ገደል ገፍቶ እንዲያንኮታኩተን ሌት ተቀን መስራት ማለት ነው።

ሁለተኛው አባባል በእግሩ መሄድ የማይችል፣ መሄድ ቢችልም ብዙ እርቀት የማይጓዝ ህፃን በእናቱ ጀርባ ላይ መታዘሉ ግድ ነው። ይሁን እንጅ ታዝሎም የእናቱን ጆሮ የሚያደነቁር ፉጨት መልቀቅ ብቻ ሳይሆን ፋጨቱ ከጨቅላው ህፃን በላይ ሲሆን አስገራሚ ነው። እናቱ እሩህሩህ የእናትነት አንጀት፣ አዝሎ የማሳደግ የተፈጥሮ ግዴታ፣ እስከ ዘጠኝ ወር በውስጥ አቅፎና ተንከባክቦ ራስን የመተካት አስገራሚ የፍጡራን ተግባራዊ ትዕይንት እና ሌሎችም ምክንያቶች የአስገራሚ ልጇን ፉጨት ተቋቁማ ለማሳደግ ጥረቷን አታቋርጥም። እናት በልጇ ድርጊት አንጀቷ እጥፍ፣ ቆሽቷ እርር እና ጨጓረዋ ቅጥል ቢልም ሀዘኗ ቢኖርም ለልጇ ክፉ አትመኝም። ባይሆን እርር ብላም ልቦና ስጠው ልትል ትችላለች። ሆኖም ሌላው ተመልካች የልጁን እናቱ ጀርባ ላይ ሆኖ ማፏጨት የሚያዬው እንደ እናት በትዕግስትና በኃዘኔታ ሳይሆን ይሄ ባለጌ፣ ድኩማን፣ ባጭር ይቅጭህ በሚል መንፈስ ነው።

አንዳንዶችም በለዘብተኛ አቋማቸው ከመሞት መሰንበት ስለሚሻል በነፍስ ንይዛቸው ይሻላል በሚል መታገሳችንን ልቦናቸው እያወቀ በደሀው ህዝብ የመኖር ዋስትና ላይ አደገኛ ቁማር መጫወት ጀመሩ። ጭራሽ የካቲት ፩፩ መቀሌ እናከብራለን ብለው ሞኞችን ለማሞኘት ሞከሩ። ይገርማል።

ትህነግ ከላይ የተገለፁ አባባሎች ተግባራዊ ምሳሌ ነው። የሚገርመው ደግሞ ሁሌም ከስህተቱ የማይማር፣ የማይፀፀት፣ በስህተት ላይ ስህተትን የሚደራርብ ጉድ መሆኑ ነው። ከወደቁ በላይ መንፈራገጥ ትርፉ መላላጥ ነው። ፈላስፋና አዋቂውን አባት ሊገዳደሩ የሞከሩ ግብዞች አንዲትን ወፍ በእጃቸው መዳፍ ውስጥ አስገብተው ይህች ወፍ በህይወት አለች ወይስ ሞታለች? አዋቂ ከሆኑ እስኪ ይንገሩን? ይበሉ? ብለው እንደፈተኗቸው ሁሉ። ፈላስፋው እና አዋቂው ሰውም የወፏ የህይወት ህልውና በእጃችሁ ነው፤ ከፈለጋችሁ ጨፍልቃችሁ መግደል፣ ስትፈልጉም እፉኛችሁን ከፍታችሁ ህይወቷን ማዳን ትችላላችሁ እንዳሉት ሁሉ። የቀሩት የስግብግብ ጁንታ አመራሮች ነፍስም እንደ ወፏ ሁሉ በእጃችን መዳፍ ውስጥ መሆኑን እኛ እንደ እናት እናውቀዋለን።

See also  በወልቃይት መከላከያን በመጎንተል ለቆ እንዲወጣ፣ የአጻፋ ምላሽ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ፤

አንዳንዶች እንደ ቴፕ ሪከርደር የገባላቸውን ካሴት የሚያጫውቱ በመሆናቸው ምክንያት፣ አንዳንዶችም በለዘብተኛ አቋማቸው ከመሞት መሰንበት ስለሚሻል በነፍስ ብንይዛቸው ይሻላል በሚል መታገሳችንን ልቦናቸው እያወቀ በደሀው ህዝብ የመኖር ዋስትና ላይ አደገኛ ቁማር መጫወት ጀመሩ። ጭራሽ የካቲት ፩፩ መቀሌ እናከብራለን ብለው ሞኞችን ለማሞኘት ሞከሩ። ይገርማል።

በለውጥ መሪያችን ድጋፍና ጥረት ከአሸባሪነታቸው ችንካር የተላቀቁ፣ በውስጥ ያልተሳካላቸው፣ በውጭም በሀገራችን ድጋፍ የአይን ጉድፋቸው የተጠረገላቸው ጉዶች፣ ኢትዮጵያ እንኳንስ ለቅርብ ዘራፊና ሙሰኛ መሪዎች ይቅርና ለውጭ ወራሪዎችም እጅ ያልሰጠች፣ ያልተንበረከከች፣ የራሷን ብቻ ሳይሆን አቅም ሳይኖራቸው እና እንደ ወፏ መዳፋችን ውስጥ የሚገኙ ተላላኪዎች ለእነሱ ነፃነት መረጋገጥ ፋና ወጊ ሚና የተጫወተች ሀገራችን መሆኗን የሩቅም የቅርብን ታሪካችን ይመሰክራል።


ይህ አንሶ በእኛው አባይ ፖለቲካ የተጠመዱ ግብዞች መሾፈር የጀመሩ፣ የአባቶቻችንን ብቻ ሳይሆን የእኛን ክንድም የቀመሱ፣ በለውጥ መሪያችን ድጋፍና ጥረት ከአሸባሪነታቸው ችንካር የተላቀቁ፣ በውስጥ ያልተሳካላቸው፣ በውጭም በሀገራችን ድጋፍ የአይን ጉድፋቸው የተጠረገላቸው ጉዶች፣ ኢትዮጵያ እንኳንስ ለቅርብ ዘራፊና ሙሰኛ መሪዎች ይቅርና ለውጭ ወራሪዎችም እጅ ያልሰጠች፣ ያልተንበረከከች፣ የራሷን ብቻ ሳይሆን አቅም ሳይኖራቸው እና እንደ ወፏ መዳፋችን ውስጥ የሚገኙ ተላላኪዎች ለእነሱ ነፃነት መረጋገጥ ፋና ወጊ ሚና የተጫወተች ሀገራችን መሆኗን የሩቅም የቅርብን ታሪካችን ይመሰክራል።

የሚገርመው ደግሞ ማንም ቢመጣ አንንበረከክም፣ አንሸነፍም፣ እኛ ለውጊያ የተፈጠርን ነን የሚለው የታራክ ዝቃጩ ከፋፋይ ስግብግብ ጁንታ በራሱ መሬት፣ ዕቅድና ፍላጎት አከርካሪው ሲሰበር ከቅጥረኛ፣ ሙሰኛና ተላላኪ ጎረቤቶች ጋር ተሰልፎ ዕድሉን ለመሞከር ሽር ጉድ ማለቱ ሌላ የታሪክ ጥቁር ነጥብ እና ጠባሳ ከማስቀመጥ ሌላ የሚያተርፈው ነገር እንደሌለ ልቦናው ያውቀዋል።


ሁሉንም በንቃት እየተከታተልን ነው። ጥንቃቄያችን እና ትዕግስታችን ለንፁሀን ዜጎች ነው። ቀይ መስመሩ ታልፎም የምንታገሰው ከፍርሀትና አቅም እጦት ሳይሆን ለንፁሀን ህዝቦች ካለን ክብር ብቻ ነው። አልያማ እኛ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያውያን ልጆች ነን። መቼ መነሳት እንዳለብን እናውቃለን። ከተነሳን ደግሞ በነቋሪዎች ፍላጎትና ዕቅድ ሳይሆን በራሳችን ነው። ማንም እኛ ዓቅደን የምንሰራውን፣ የእኛ ሀብት የሆነውን ሁሉ የመከልከልና የመዝረፍ ተፈጥሯዊም ህጋዊም ዓቅምም ይሁን ስልጣን እንደሌለው ያውቃል። እናም ነቋሪ ሙሰኛና ዘራፊ የጎረቤቶቻችን መሪዎች ከሌሎችና ከራሳቸው ታሪክ ብቻ ሳይሆን ኮትኩተው ካሳደጉት ስግብግብ ጁንታ አሳፋሪ ታሪክ፣ ስግብግብ ጁንታውም በተመሳሳይ ከውድቀቱ መማር ይገባቸዋል። ካልሆነ እንደለመዱት ከመከራቸው እንዲማሩ ይገደዳሉ። ሁሉ ነገር ለእኛ የእምቧይ ካብ ነው። ይሄው የካቲት ፩፩ በመቀሌ ሳይሆን ገደል ውስጥ ተወሽቀው አሳለፉት። ነገ ደግሞ ልቦና ካልገዙና ከስህተታቸው መማር ካልቻሉ የተወሸቁበት ገደል ውስጥ ይቀበራሉ። ምርጫው ግን በእጃቸው ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

Leave a Reply