ጁንታው በዋሻ ውስጥ ሆኖ የትግራይን ህዝብ ለማደናገር የሚያደርገው ጥረት እንደማይሳካ መከላከያ ሰራዊት ገለፀ። የአገር መከላከያ ሰራዊትን ስም በማጥፋት ህዝብን ብዥታ ውስጥ ለመክተት የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃንን በህግ እንደሚጠይቅም አስታውቋል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት ” ህወሓት የተባለ ድርጅት መሬት ላይ የለም ጁንታው መቃብር ፈንቅሎ ሊወጣ አይችልም፤ ራሱ በለኮሰው እሳት ተለብልቦ ጠፍቷል” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተበታትነውና በዋሻ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ የጁንታው ትርፍራፊዎችና ከፍተኛ ተከፋይ አክቲቪስቶቻቸው አሁንም የሐሰት ወሬ እየነዙ ይገኛሉ ነው ያሉት።

Related stories   Sudan official: ‘Mediation between Khartoum and Addis Ababa faces obstacles’Powered by Inline Related Posts

የጁንታው ቃል አቀባይ የነበረው ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑ በስልክ አስተላለፈው ተብሎ የወጣው መልዕክት የትግራይ ወጣቶችን ለማደናገር የተደረገ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በተጨማሪም መከላከያ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር እየሰራ ነው በሚል አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ያሰራጩት ከእውነት የራቀ መረጃ ነው ብለዋል። “የተወሰኑት የመከላከያ ተቋማት የባንክ ሂሳባቸውን ወደ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አዙረዋል” በሚል የተነዛው ወሬ የተሳሳተና እውነትነት የሌለው ነው በማለት ገልፀዋል።

መከላከያና በስሩ ያሉት የልማት ድርጅቶች የሚጠቀሙት የባንክ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነውም ነው ያሉት። ሰራዊቱ ለአገር ሉዓላዊነት ከፍተኛ መስዋትነት ከፍሎ አገር እያስቀጠለ ባላበት ጊዜ እንደዚህ አይነት ወሬ የሚነዙ አካላት ዓላማ ጁንታው እያራመደ ያለውን የዘረኝነት ቅስቀሳ ማስፈፀም ነው ይላሉ ሜጄር ጄኔራል መሐመድ።

Related stories   የፍትህ ጥያቄው እነማንን አቅፎ እነማንን እንዲገፋ ነው የሚፈለገው ? ፍትህ ለእገሌ …Powered by Inline Related Posts

ምንም የተቀየረም ሆነ የተዘዋወረ አካውንት የለም ያሉት ሜጄር ጄኔራል መሐመድ መረጃው የሀሰት ውንጀላ ነው ብለዋል። ይህን የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል በማለትም ሰራዊቱን የማይገልጽ ዘገባ በመሆኑ እነዚህን አካላት በህግ እንጠይቃለን ነው ያሉት።

በመጨረሻም የቀሩትን የጁንታ ቡድን አባላት ከተደበቁበት ጉድጓድ ለማውጣት የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው ያሉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ጁንታውን የማደንና ሰላም የማስከበሩ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

Related stories   የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥብቅ መመሪያ አወጣ – ጥይት መተኮስ ተከለከለ፤ በህግ ያስቀጣልPowered by Inline Related Posts

ዋዜማ ሬዲዮ ነው መከላከያ የሂሳን አካውንቶቹን ወደ ኦሮሚያ ባንክ አዛውሯል ሲል ምንጭ ጠቅሶ ያስታወቀው። ዋዜማ ቀደም ሲልም ኢትዮጵያ አሜሪካ እየተደረገ በነበረው ድርድር የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያሳጣ ስምምነት ተደረሰ በሚል ያወጣው ዘገባ ሃሰት እንደሆነ መንግስት ማስረጃ አቅርቦ ማስተባበሉ አይዘነጋም።

Leave a Reply