በአዲስ አበባ በቡድን በመደራጀት የዘረፋ እና የግድያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 53 ተጠርጣሪዎች ተያዙ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በቡድን በመደራጀት የዘረፋ እና የግድያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 53 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ነጋሽ ÷ በከተማዋ የሚፈፀሙ የዘረፋ እና የግድያ ወንጀሎችን መነሻ በማድረግ እና የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማቋቋም   በተደረገ እልህ አስጨራሽ እና አድካሚ ክትትል ወንጀሎቹን ሲፈፅሙ የነበሩ 53 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር  መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ እጅግ አደገኛ እና ደጋጋሚ ወንጀል ፈፃሚዎች መሆናቸውን ከጣት አሻራ ሪከርዳቸው ማረጋገጥ እንደተቻለ ያስታወሱት ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ከእነዚህም መካከል ለ55 ፣ ለ30 እና ለ10 ጊዜ የወንጀል የጣት አሻራ ሪከርድ የተመዘገበባቸው መገኘታቸውን ተናግረዋል ፡፡Related stories   በለዘብተኛ አቋማቸው የተነሳ – “ሳይደመሰሱ የቆዩት የስግብግብ ጁንታ አመራሮች ነፍስም እንደ ወፏ ሁሉ በእጃችን መዳፍ ውስጥ መሆኑን እኛ እንደ እናት እናውቀዋለን “Powered by Inline Related Posts

በአራት ቡድን የተደራጁ 36 ተጠርጣሪዎች በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች ባንክ ቤትን ጨምሮ በተለያዩ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥናት በማድረግ  እና በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ ቆይተዋልም ነው ያሉት፡፡

እነዚህ የወንጀል ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው 4 ሽጉጦች ፣ የካዝና መሰርሰሪያ  እና ለወንጀል ተግባራቸው የሚገለገሉባቸው ሌሎች ቁሳቁሶች እና ተሽከርካሪዎች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ሙሉ በሙሉ ሊያዙ መቻላቸውን እና 14 የምርመራ መዝገብ እንደተደራጀባቸው ምክትል ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል ወርቅ ቤቶች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው በተለይም ፒያሳ አካባቢ የዘረፋ ወንጀል የሚፈፅሙ በሁለት ቡድን የተደራጁ 9 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋልም ነው ያሉት፡፡Related stories   Sudan official: ‘Mediation between Khartoum and Addis Ababa faces obstacles’Powered by Inline Related Posts

እንደ ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ገለፃ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ለመፈፀም የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ታጥቀው በተሽከርካሪ እየታገዙ የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ በክትትል የፖሊስ አባላት ብርቱ ጥረት ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከዘረፉት በርካታ ወርቅ፣ ለወንጀል ተግባራቸው ከሚገለገሉባቸው ተሽከርካሪ፣ሽጉጥ እና የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመላክተዋል፡፡

See also  አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአግዋ ተጠቃሚነት የማስወጣት እንቅስቃሴ ከአሜሪካውያን ባለሀብቶች ትችት ገጠመው

በተጨማሪም ፌሮ ብረት ፣ዱላ፣ ድንጋይ እና ስለት በመጠቀም ንብረት ለመውሰድ በሰው አካል ላይ ጉዳት ሲያደርሱ እና የግድያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ በሁለት ቡድን የተደራጁ 8 ተጠርጣሪዎችም በከፍተኛ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡Related stories   ኢሳያስ አፉወርቂ – የትልቁ ስዕል ቅኔ፣ የቅዠቱ መነሻ፣ የቀጣናው ባዶ የፖለቲካ ጉሊትPowered by Inline Related Posts

ተጠርጣሪዎቹ በተለይም በየካ ክፍለ ከተማ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በለሊቱ ክፍለ ጊዜ አሳቻ ሰዓት እና ቦታ እየመረጡ ወንጀሉን ሲፈፅሙ ነበር፡፡

ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው አምነው የት እና እንዴት እንደፈፀሙም ለፖሊስ መርተው አሳይተዋል፡፡

ለዚህ ውጤት መገኘት የኮሚሽኑ የምርመራ እና የክትትል አባላት ከከፈሉት መስዋዕትነት በተጨማሪ ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ላደረገው ትብብር  ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ምስጋናቸውን አቅርበው የከተማዋን ሠላም ይበልጥ አስተማማኝ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

  • የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ለኢንቨስተሮች መሰጠቱን የተቃወሙ ሦስት ምሁራን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጻፉ
    “እሳቸው ይሄንን ነገር ሰምተውታል ብዬ አላስብም። ከሰሙ እንደሚያስቆሙት እርግጠኛ ነኝ”  ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከፊል ስፍራ ተቆርሶ ለግብርና ኢንቨስተሮች መሰጠቱ ያስቆጣቸው ሦስት ምሁራን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደብዳቤ ጻፉ። የባቢሌ ፓርክ ደን ተመንጥሮ ለኢንቨስተሮች መሰጠቱ ከፍተኛ የድርቅ አደጋ እንደሚጋርጥ በመግለጽም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጣልቃ እንዲገቡ ምሁራኑ በደብዳቤያቸው … Read moreContinue Reading
  • የበርሊን ማራቶን ባለማዕረግ ትግስት እነ ዱቤ ጂሎ ቢሳተፉ ታዝረከርካቸው ነበር
    በማራቶን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሻል እጅግ የሚደነቅና ያልተለመደ ነው። ባለሙያዎቹ ወይም አሰልጣኞቹ የሮጠችበትን ፍጥነት በሰዓትና ርቀት ከፋፍለው ቢያቀርቡት ምን አልባትም ወንዶችን የሚገዳደር ፍጥነት ተጠቅማ ሮጣለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቴክኒክ ዳይሬክተርና የአትሌቶች ኮሚሽን ሰብሳቢ የነበሩት የዛሬው የተከበሩ ዱቤ ጅሎ አይነቱን ሯጮችን አዝረክርኮ ማሸነፍ የሚያስችላትን ሃይል አሳይታለች። የበርሊና ባለ ማዕረግ ትዕግስት!! ተግስት … Read moreContinue Reading
  • የባህር ዳር ነዋሪዎች- ኢትዮጵያን ዜጎች በሁሉም ቦታ እኩል የሚስተናገዱባት ሀገር ማድረግ ይገባል
    የባህር ዳር ነዋሪዎች የሕዝብን ጥያቄ የመፍታት አቅም፣ ፍላጎት እና ቅንነት ያለው አመራር በመፍጠር ሕዝብን መካስ እንደሚያስፈልግ፣ ኢትዮጵያ በዘር ከመገፋፋት እና ከመጠቃቃት ነጻ የኾነች ፣ዜጎች በሁሉም ቦታ እኩል የሚስተናገዱባት ሀገር እንድትኾን ማድረግና የፌዴራል መንግሥት የአማራ ሕዝብ ኅብረ ብሔራዊ እና ልማት ወዳድ እንጅ ጦርነትን የማይፈልግ መኾኑን በውል በመገንዘብ የሕዝቡን ተዘዋውሮ የመሥራት እና … Read moreContinue Reading

Leave a Reply