በመተከል ዞን የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ የልዩ ኃይልና የመደበኛ ፖሊስ አመራሮች ተመረቁ

NEWS

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞንን ጸጥታ በተሻለ መልኩ ለማስጠበቅ በሁለተኛ ዙር የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ 460 የዞኑ ልዩ ኃይልና መደበኛ ፖሊስ አመራሮች ተመረቁ።

በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮን ጨምሮ የመከላከያና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፤ የጸጥታ ኃይሉ የውስጥ አንድነቱን አጠናክሮ ለተልዕኮ መዘጋጀት አለበት።

“በዞኑ የሚገኙ የመደበኛ ፖሊስም ይሁን የልዩ ኃይል፤ አመራርና አባል የማይናድ አንድነት ሲገነቡ የህዝቡም አንድነት ይጠነክራል” ያሉት ሌተናል ጄኔራል አስራት፤ የጸጥታ ኃይሉ በማንነትም ይሁን በብሔር አድሎ ማሳየት እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

የጸጥታ ኃይሉ ከህዝብ በፊት አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ከሁሉም በላይ መዘጋጀትና ሕዝባዊ አስተሳሰብ መገንባት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

የጸጥታ ሀይሉ አርዓያ በመሆንና በመልካም ስነ ምግባር መቆም እንዳለበት ሌተናል ጄነራል አስራት አሳስበዋል።

የምዕራብ ዕዝ የስልጠና ኃላፊ ኮሎኔል ሰይፈ ኤንጊ በበኩላቸው የስልጠና ማዕከሉ በዞኑ ፓዌ፣ ቡለንና ጉባ ወረዳዎችን ማዕከል አድርጎ በሁለት ዙር ተሃድሶው መስጠቱን ጠቁመዋል።

ስልጠናው የጸጥታ ሀይሉ ህዝቡን በመልካም ስነ ምግባር በታማኝነት ማገልገል እንዲያስችል በማሰብ ወታደራዊ ባህልና ጨዋነት፣ የህገ መንግስቱ መሰረታዊ መርሆችና የጸጥታ ሀይል ደህንነት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።

“በዚህም 237 የጸረ ሽምቅ አድማ ብተና ወይም ልዩ ሀይል እና 222 መደበኛ ወይም ሕዝባዊ ፖሊሶች የአምስት ቀናት ሁለተኛ ዙር ስልጠናቸውን አጠናቀዋል” ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የጸረ ሽምቅ አድማ ብተና ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር ኢዶሳ ጎሹ የተሀድሶ ስልጠናው የጸጥታ ሀይሉ ያለበትን ክፍተት ለመፍታት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የካቲት 17 ቀን 2013(ኢዜአ)


Related posts:

ዋር ኮሌጅ ከፍተኛ መኮንኖችን አበቃ፤ መከላከያ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በቁ አቋም አለው
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Leave a Reply