” እንኳን ሰብዓዊ ቀውስ ተከስቷል፣ ጦርነት ነበረ ብሎ ዜና ለመስራት አይበቃም ” አልጃዚራ መቀለ

የአልጃዚራ ዘገባ !

በመቀለ ከተማ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ የአልጃዚራ አረብኛ ፕሮግራም ” እንኳን ሰብዓዊ_ቀውስ ተከስቷል፣ ጦርነት_ነበረ ብሎ ዜና ለመስራት አይበቃም ” ሲል መዘገቡ ተገለጠ። አልጃዚራ የዘገበውን ወደ አማርኛ የመለሰው ሱሌማን አብደላ እንዳለው ዘገባው አስገራሚ ነው።

ወደ ትግራይ ገብተው በክልሉ ያለውን ሁኔታ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ሚዛናዊ መረጃ እንዲያቀርቡ ከተፈቀደላቸው ሚዲያዎች መካከል አንዱ አልጀዚራ መሆኑ ይታወሳል። አልጀዚራ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ስለ ሱዳን ድንበርና የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ሀገሪቱ የሀገሪቱን አሰላለፍና ወቅታዊ ሁኔታ እንዲህ ሲል ነበር ያቀረበው፤

አሁን የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ላይ እንገኛለን። በመቀሌ ቆይታችን ሁሉንም ነገር አይተናል። መቀሌ በኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት ስር ትገኛለች። ከተማዋን ተዟዙርን ባየንበት ጊዜ ምንም ጦርነት አላየንም። “ለህዝቡ ህወሓት ወደየት ነው?” ብለን ጠየቅናቸው “ህወሓት የለም ሸሽቶ እጋራ ስር ነው ያለው አሉን ” ተመልሰው ይመጣሉ እንዴ?” አልናቸው “እሱን አናውቅም አሉን አለ” ይላል ጋዜጠኛው፦

” …, ህወሓት ለ27 ዓመት ኢትዮጵያን የመራና የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሁኔታ ጠንቅቆ የሚያውቅ በተንኮል ተወዳዳሪ የሌለው ድርጅቱ ነው። ምናልባት አሁን ጫካ ሊሆን ይችላል እንጅ ወደፊት ምን ሊያመጣና ምን ሊያደርግ እንደሚችል አይታወቅም” በማለት ዘጋቢው መናገሩን ተርጓሚው አስፍሯል።

በመቀሌ ቅይታችን ላይ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው መጠለያ ያሉ ሰዎችን አይተናል። ትንሽ የሚባል የምግብ አቅርቦት ችግር ቢኖርም የሀገሪቱ መንግስት ከረጅ ድርጀቶች ጋር በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራ መሆን አረጋግጠናል። በመጠለያ ካምፑ ውስጥ መንግስትና ረጅ ድርጅቶች ያከማቹትን አስቤዛ ተመልክተናል። በእርግጥ ህዝቡ አሁን ስላለው ብቻ ሳይሆን ወደፊት ስለሚመጣው ነገር ይጨነቃሉ።

“ጦርነት ይኖር ይሆን ወይ ሰላም ይሰፍናል ወይ!” የሚለው ጥያቄ በመቀሌ ህዝብ ውስጥ ይብሰለሰላል። ወደ መቀሌ እየገባን እያለ የተወሰኑ የተደራጁ የሚመስል ወጣቶች አልጀዚራ ሚዲያ መሆኑን ሲያውቁ ተገደልን_ተደፈርን_ተረሸን_ተጨቁነናል አሉ። ሁኔታቸውን ስንመለከት ከውስጣቸው እጃቸውን እንዲያጣምሩና “ተገልን ተደበደብን ተደፈርን” እንዲሉ የሚያዛቸው ሰው መኖሩን ስናይ ነገሩ የፕሮፓጋንዳ ፍለጋ መሆን አመንን ብሏል ጋዜጠኛው።

See also  Putin Warns of Possible Military Response over ‘Aggressive’ NATO

በመቀሌ ከተማ ዞር ዞር እያልን በቦንብ የተጎዱ ተቋማትን ለማየት መኮርን። እንደሚባለው አይደለም፣ “ጦርነትን ለሚያውቀውና በጦርነት የተጎዱ ከተሞችን ላየ ጋዜጠኛ መቀሌ ተጎድታለች ብሎ ዜና ለመስራት አይበቃም፤ በከተማዋ የንግድና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች አሉ። ብዙ ሁሉም በሚባል መልኩ ግን ጠቅላላ ወደ ስራ አልገቡም”

ጦርነቱ ከተጀመረ ቀን ጀምሮ ምንም ስራ ያልሰሩ ወጣቶች አነጋግሬያለሁ። አሁንም ሌላ ተጨማሪ ጦርነት ይፈጠራል የሚል ስጋት አላቸው ።

የአልጃዚራ ዘጋቢ ከመቀለ

ትርጉም በሱሌማን አብደላ

Leave a Reply