በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ባላፈው ማክሰኞ ከሽንፋ ወደ መተማ (ገንዳ ውሀ) ሲጓዝ በነበረ ተሸከርካሪ ባልታወቁ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 4 ሰዎች መለቀቃቸውን የአካባቢው ነዋሪና እና የዞኑ አስተዳደር አስታውቀዋል፡፡አንድ የሽንፋ ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ ዛሬ በስልክ እንደተናገሩት ግለሰቦቹ ከመንገላታትና ከመጎሳቆል ውጪ በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው ገብተዋል፣ “በህይወት መመለሳቸው ሁሉንም አስደስቷል ፣ የተወሰነ ድብደባ እና ጫና ደርሶባቸዋል።ሰውነታቸው ተጎስቁልቁል” ብሏል።

“የተደበደቡበት እንዳለ ሆኖ በሰላም መምጣታቸው ነው ደስ ያለን እኛን» ሲሉ፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ታጋቾቹ በምን ዓይነት መንገድ እንደተለቀቁ ባያብራሩም አሁን ሁሉም ከእገታ ተለቅቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን አስረድተዋል፡፡

«አሁን ሰዎቹ ተለቀዋል። በጥዋት ነው የተለቀቁት »የችግሩን መፈጠር ምክንያት በማድረግ በአካባቢው ያሉ አሽከርካሪዎች ወደ ገንዳ ውሀ፣ ቋራ እና ሽንፋ የሚሰጡትን የትራንስፖርት አገልግሎት አቋርጠው የሰነበቱ ሲሆን ህብረተሰቡ፣ አስተዳደሩና የፀጥታ አካላት ባደረጉት የጋራ ውይይት አገልግሎቱ ትናነት ከሰዓት በኋላ መጀመሩን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ባለፈው ማክሰኞ አንድ ተሸከርካሪ ከሽንፋ ወደ ገንዳ ውሀ ሲጓዝ ጉባዔ ከተባለ ቦታ ላይ ያልታወቁ ታጣቂዎች 4 ሰዎችን አግተው ወስደው ነበር።

በወቅቱ በነበረው የተኩስ ልውውጥ አንድ የመንግስት የፀጥታ አባልና ከአጋቾቹ ደግሞ አንድ መገደላቸው ተዘግቧል፡፡ቀደም ባሉት ጊዜያት ተመሳሳይ መኪና አስቆሞ ማገት፣ መዝረፍና ማንገላታት በአካባቢው ይታይ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ችግሩ ጋብ ብሎ እንደነበር ጀርመን ድምጽ አስታውቋል። 

ዜናውን የዘገበው ክፍልም ሆነ አስተአደሩ አጋቾቹ ማን እንደሆኑ፣ ለምን እንዳገቱና አግተው ምን ጥያቄ እንዳቀረቡ የተገለጸ ነገር የለም።

Leave a Reply