ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት ለትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪነት ጄነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል መሾማቸውን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ዛሬ ከክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ግበረሃይልና አስተዳደር ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ ስለተነሱት ጉዳዮች ዝርዝር ባይጠቅሱም በክልሉ ስለተሰሩ ስራዎችና ቀጣይ ተጋባራት ውይይት መደረጉን በማህበራዊ ገጻቸው አመላክተዋል። ይህን በጠቀሱበት ወቅት ነው ጀነራሉ መሾማቸውን ያመለከቱት።
“… ከዛሬ የካቲት 24፣ 2013 ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይሉ በጄኔራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል ተስፋ ማርያም አመራር በመታገዝ የማረጋጋት እና መልሶ የመገንባት ሥራውን ይቀጥላል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ” የተደረገው ውይይት ጠንካራና በርካታ ጉዳዮችን በደካማ አፈጻጸም ገምግሟል” የሚል መረጃ አግኝተናል።
የአገር መከላከያ ኤታምዦር ሹም ብርሃኑ ጁላንና ምክትላቸው ሌ/ጀኔራል አበበው ታደሰ፣ ዶክተር አብረሃ በላይና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ዶክተር ሙሉ በሚታዩበት ፎቶ ታግዞ የቀረበው ዜና ውስንማ ቁልፍ ሰዎች የተገኙበት ከመሆኑም በላይ፣ ለነራል ዮሐንስ ወደ ሃላፊነት እንደመጡ መገለጹ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካሄድ ደካማ መሆኑንን አመላካች ሆኗል።
- ከአምስት አመት በፊት በእንጀራ እናቷ ተገደለች የተባለችው ግለሰብ በህይወት ተገኘች
by topzena1
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ ከአምስት ዓመት በፊት በእንጀራ እናቷ ተገደለች የተባለችው ግለሰብ በህይወት መገኘቷ ታወቀ። ግለሰቧ መሞቷ በሀሰተኛ ምስክሮች ተረጋግጦ የእንጀራ እናቷ የ20 ዓመት እስር ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር። ሞታለች የተባለችው ግለሰብ እና ከሳሽ የነበሩት በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዞኑ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኮማንደር ደበበ […]
- “ሌሎች ህወሃቶችና ኦነግ ሸኔ ጨረሱን” የአጣዬ ነዋሪዎች ” ጅብ የሚነክሰው አናክሶ ነው ” የአቶ ምግባሩ ትንቢት
by topzena1
በክፉዎች ሴራ ቤተሰቦቻቸው፣ የአማራ ክልል፣ ኢትዮጵያና ወዳጆቻቸው ያጡዋቸው አቶ ምግባሩ ከበደና ባልደረቦቻቸው የሚረሱ እንዳልሆኑ በሁሉም ዘንድ እምነት አለ። ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የአቶ ምግባሩ ከበደና የርዕሰ መስተዳደሩ አማካሪ የአቶ እዘዝ ዋሴ በጁን 25 ቀን 2019 የቀብር ስነስርዓታቸው የተከናወነው በክፉዎች ሴራ መሆኑንን መላው የአማራ ሕዝብ ጠንቅቆ […]
- የአማራ ሕዝብ ከፖለቲካ ነጋዴዎች ራሱን አግልሎ በአንድነት ይቁም!! ሰሜን ሸዋ፣ ጭልጋ፣ ፍኖተ ሰላም አማራ እየተወጋ ነው
by topzena1
የክልሉ የሰላምና ሕዝብ ደኀንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ ሲናገሩ እንደተሰማው በሰሜን ሸዋ ያለው ሁኔታ የከፋ ነው። አማራ አንድ ሆኖ መነሳት አለበት። የአካባቢውን አመራሮች የጠቀሱ የሌሎች ሚዲያዎች እንዳሉት ወራሪው ሃይል እጅግ ብዙ ነው። አሁን ስፍራው ላይ ያለው ሊቋቋመው አይችልም። አቶ ሲሳይ ” አማራ በአንድ ይቁም” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። […]
- “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”
by topzena1
በኢትዮጵያ እውነተኛ ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያሲዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ አሁን ያሉትንና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ የአገሪቱን ችግሮች ለመፍታት ከባድ ሊሆን እንደሚችል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደረጉ ምሁራን ገለጹ። ‘ኢትዮጵያዊነት’ በተሰኘ የሲቪክ ማኅበር አዘጋጅነት ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያያዙትን የተሳሳተ አቋም በተመለከተ በአለም አቀፍ ደረጃ የዌቢናር ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ […]
- ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አባረረች-አሜሪካ ለጣለችባት ማዕቀብ አፀፋዊ ምላሽ ነው ተብሏል
by topzena1
ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን ያባረረች ሲሆን፣ ሌሎች ስምንት ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ደግሞ ወደ አገሯ እንዳይገቡ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ማስገባቷ ተገለፀ። ሩሲያ ይህን ያደረገችው ማክሰኞ ዕለት አሜሪካ ለጣለችባት ማዕቀብ አፀፋዊ ምላሽ ነው ተብሏል።በመሆኑም የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ (ኤፍቢአይ) አባላትና የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለሥልጣናት ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ ታግደዋል። የአሜሪካ ጠቅላይ […]
Like this:
Like Loading...
Related