ሰሜን ሸዋ በ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ወጭ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ሊገነባ ነው፡፡

አክስዮን ማህበሩ በኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና በቻይናው ዌስት ቻይና የሲሚንቶ አምራች ኀላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ሽርክና የተመሰረተ ነው።

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመሥገን ጥሩነህ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ግንባታ በኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

በእንሳሮ ወረዳ በ270 ሄክታር ቦታ ላይ ይገነባል ። በአጠቃላይ 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል ። በመጀመሪያ ዙር አስር ሺህ ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተዉን ፋብሪካ ጨምሮ የመስታዎት፣ የጂፕሰም ቦርድና ሌሎች ምርቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን ያካትታል።

የፋብሪካዎቹ ግንባታ 10 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

ዘጋቢ፡- ጺዮን አበበ – ከእንሳሮ

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2013 ዓ.ም (አብመድ)

See also  " ከሩስያ ጋር በዩክሬን ምድር አንዋጋም፣ የኔቶ አባል አገራትን ግን ኢንች እንዳይነኩ እንከላከላለን " አሜሪካ

Leave a Reply