… ኘሮጀክቱ የግብፅን ፍላጎት ለማሳካት በሰብአዊ ድጋፍ ስም የሚካሄድ ሴራ ሊሆንም ይችላል። ግብፅ ደግሞ ከኢትዮጵያ የተሻለች የአሜሪካ ስትራቴጂክ ወዳጅ መሆኗንም መርሳት አያስፈልግም። ሱዳንም በኢትዮጵያ ላይ የታቀደውን እቅድ ማስፈፀምያ መሳርያ ነች። ህውሃትም ነብሷን አይማራትና በመጨረሻ አጣብቂኝ ውስጥ ስትገባ ከግብፅና ከሱዳን ጋር በህቡዕ ያልተቀደሰ ጋብቻም ፈፅማ እንደ ነበር ይታወሳል። ስለሆነም ይህ ጉዳይ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋም ሃላፊነት ይሆናል ማለት ነው።የሃገር ሉዓላዊነት ከፓለቲካ ርዕዮት የላቀ ነውና!
በላይ ባይሳ