አሜሪካ የሰባ ሁለት ሰዓት ጊዜ ገደብ ሰጠች የሚባለውን መንግስት አያውቀውም

NEWS

ትህነግ ከፍተኛ ሃብት ያፈስላቸዋል የሚባሉት ነጭ የሚዲያ ሰዎች አሜሪካ ለኢትዮጵያ ማስጠንቀቂያ ሰጥች በሚል በስፋት እያሰራጩት ስላለው ዜና ኢትዮጵያ የምታውቀው ነገር እንደሌለ ተገለጸ። ዜናውም ፈጠራ እንደሆነ ተጠቆመ። ይልቁኑም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት መሞከሩ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እነ ማርቲን ፓላውት ” ሰዓቱ ደረሰ” በሚል ኢትዮጵያ የአማራ ላዩ ሃይልና የኤርትራን ወታደሮች ከትግራይ እንድታሰወጣ የአሜሪካ ውጭጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በስልክ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መመሪያ መስጠታቸውንና መመሪያውም ተግባራዊ የሚሆነው ማምሻውን እንደሆነ በቲውተር ገሳጻቸው ሲያሰራጩና ውዳሴ ዚጎርፍላቸው ነበር የዋሉት።
ፋክት ቼክ የአሜሪካን ኤንባሲን፣ የመንግስት ባለስልጣን አነጋግሮ ይፋ እንዳደረገው ዜናው ፈጠራ ወይም ሃሰት መሆኑንን አመልክቷል። ዝርዝሩንም እንደሚከተለው አትሟል። ከታች ይነበባል።

በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች፣ የቀጠናው ተንታኞች እንዲሁም አክቲቪስቶች የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ እለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ አንቶኒ ብሊንከን በስልክ ያረጉትን ውይይት ተከትሎ “አሜሪካ የኤርትራ እና የአማራ ሀይሎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ የ72 ሰአት ግዜ ሰጥታለች” የሚል መረጃ ሲያሰራጩ ነበር።

እነዚህ አካላት ጨምረውም ይህ የ72 ሰአት ግዜ ካልተከበረ ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ እንደሚጣል ሲያትቱ እና ሲገምቱ ነበር። ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ከአሜሪካ እንዲሁም ኢትዮጵያ መንግስታት መረጃ ጠይቋል።

ከአሜሪካ መንግስት በኢሜይል ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው እንዲሁም በተለያዩ ሚድያዎች ባሳለፍነው ሳምንት እንደተዘገበው አንቶኒ ብሊንከን “የውጪ ሀይሎች” ብለው የገለጿቸው የኤርትራ እና የአማራ ሀይሎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል። ያገኘነው መረጃ ግን ከዚህ ውጪ “72 ሰአት” ተብሎ የተቀመጠ ነገር እንዳልነበር ይጠቁማል። ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ያናገርናቸው አንድ ባለስልጣንም “እንዲህ አይነት ነገር እንደተባለ መረጃ የለኝም” ብለው ለኢትዮጵያ ቼክ አጭር መልስ ሰጥተዋል።

ሌላኛው ያናገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ “72 ሰአት ተብሎ በአሜሪካ ተቀምጦ ቢሆን ኖሮ ውጭ ጉዳይ ቢሯቸው ማክሰኞ ያወጣው መግለጫ ላይ እናየው ነበር፣ ያ ግን አልሆነም። ያ ለምን አልሆነም ሲባል መቼም አሜሪካ መግለጫዋ ላይ ለማስፈር ሳትደፍር ቀርታ አይመስለኝም፣ ጭራሽ ያልተባለ ነገር ስለሆነ እንጂ” ብለዋል። የኢትዮጵያ ቼክ ማጣራት እንደሚጠቁመው ይህ ተሰጠ የተባለ የ72 ሰአት ግዜ የተሳሳተ መረጃ ነው።

በተያያዘ ሌላ ዜና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት መሞከሩ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፥ ሱዳን ድንበር ጥሳ መግባቷን ኢትዮጵያ በግልጽ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባሳወቀችበት ወቅት በጉዳዩ ላይ አንድም ነገር አለማለቱን ነው የጠቀሱት፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አሁን ላይ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባትና በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታና የሰብዓዊ ድጋፍ አስመልክቶ ልዩ ትኩረት እንደሰጠው አድርጎ ለማስመሰል የሚጥርበት ሁኔታ ትክክል አይደለም ብለዋል አምባሳደር ዲና፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃም ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ የድንበር ሁኔታውን በመተው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገው ጥረትም በዓለም ላይ ትልቅ ጥያቄ የሚያጭር ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመልክቷል።

Related posts:

"መከላከያ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በሚችልበት አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል" አብይ አህመድ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Leave a Reply